ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ የፓስፖርት ጥንካሬ መመዘኛ 185ኛ ደረጃ ላይ ስትገኝ አየርላንድ ቀዳሚ ሆናለች።
ኢትዮጵያ ትላንት በዓለም አቀፍ አማካሪ ድርጅት ኖማድ ካፒታሊስት ይፋ በሆነው የ2024 የኖማድ ፓስፖርት መመዘኛ ከ199 ሀገራት ተወዳድራ 185ኛ ደረጃን ይዛለች።
አየር ላንድ አንደኛ ደረጃ ላይ ስትገኝ በፓስፖርቷ 176 ሀገር ያለ ቪዛ ያስገባሉ፤ የኢትዮጵያ ፓስፖርት 57 ሀገራት ያለ ቪዛ ወይንም በደረሱበት ሀገር አየር ማረፊያ ላይ ቪዛ ይመታለታል፤ ጎረቤት ሀገር ደበቡ ሱዳን 184ኛ ኬንያ 134ኛ ኤርትራ ደግሞ 197ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን አፍጋኒታስታን 199ኛ ደረጃ መጨረሻ ላይ ተቀምጣለች።
መመዘኛው ከቪዛ ነፃ የመጓዝ እድልን ብቻ ሳይሆን እንደ ግብር፣ ዓለም አቀፋዊ ገጽታ እና የግል ነፃነቶችን የመሳሰሉ ነገሮችን ከግምት ውስጥ በማስገባት በዓለም ዙሪያ ያሉ 199 ፓስፖርቶችን ጥንካሬ ገምግሟል።
ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት የአውሮፓ ያልሆኑ ፓስፖርቶች የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና ኒውዚላንድ ሲሆኑ ሁለቱም በ10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
Via @mussesolomon