𝑚𝑢𝑠𝑡𝑒𝑓𝑎 A𝑝𝑜𝑙𝑜𝖌𝑒𝑡𝑖𝑐𝑠 🥷


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Inglizcha
Toifa: Bloglar


እዚህ ቻናል ላይ እስልምና ላይ ለሚነሱ እያንዳንዱ ጥያቄዎች እና ብዥታዎች በማምጣት በጠንካራ ማስረጃ መልስ እንሰጥበታለን ኢንሻ አላህ☪️
አጠር አጠር ያሉ አስተማሪ ነገር የምለቅበት ትንሹ ቻናሌ ነው ጎራ በሉ➾https://t.me/mustefa_Notes

Bog‘liq kanallar

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Inglizcha
Toifa
Bloglar
Statistika
Postlar filtri


ፈጅር እየሰገዳችሁ ነው


ሰዎች ያሰቡልኝን አይነት አወዳደቅ
ያልወደኩት አላህን ስለተደገፍኩ
ነው❤️‍🩹


​ያ አርሃመ-ራሂሚን! ይቅርታህ ከኃጢአታችን ይበልጣል፤ በምህረትህ ላይ ያለን ተስፋም በመልካም ስራችን ላይ ካለን ተስፋ ይበልጣል። ያ ረብ! እኛ ወጣቶች ነን፣ ወንጀለኞች ነን፣ አንተ ደግሞ የምህረት ባለቤት ነህና ማረን... እዘንልንም።

​ያ ረቢ! 🤲🏽
ለእኛ ለወጣቶች ያልታሰበ ሪዝቅህን፣ የማያልቅ ምህረትህን፣ የማይዋዥቅ ዓፊያህንና የተደላደለ ኑሮ ስጠን። ያሰብነውንም ሆነ ያላሰብነውን ጉዳያችንን ሁሉ አንተ ፈጽምልን። በልባችን ያለውን ከባድነት አንሳልን፤ ከአቅማችን በላይ የሆነብንን ነገር ሁሉ አቅልልን።

​ያ መውላና! 🤲🏼
ከጭንቀት በኋላ የሚመጣውን ደስታና እረፍት አሳየን። በራህመትህ ጥላ ስር አድርገን። ለችግሮቻችን ሁሉ ቅርብ የሆነ መውጫ መንገድን ስጠን። በዱንያም በአኺራም የሚበጀውን ሰላም ለግሰን። የልባችንን ስብራት ጠግንልን፤ በምንፈራው ነገር ላይ ብርታትን፣ በምንጠብቀው ነገር ላይ ደግሞ ስኬትን ስጠን።

​ያ ጀባር! 🤲🏽
ወንጀልን በእኛ ዘንድ የተጠላ አድርገው፤ ለኸይር ስራም መንገዱን አግራራልን። ልባችንን፣ አይናችንን፣ ጆሮአችንንና ምላሳችንን ከሀራም ጠብቅልን። ከምላስ ወለምታና ከከንቱ ንግግር ሰውረን። ሀሲድና ምቀኛን ከእኛ አርቅልን፤ ከጥሩዎቹና ካንተ ወዳጆች ጋር ብቻ አወዳጀን።

​ያ ወዱድ! 🤲🏼
አንተ ዘንድ ተወዳጅ ባሮችህ አድርገን፤ ሰዎች ዘንድም አስወድደን። ለቅጽበትም ቢሆን ጥበቃህን አትንፈገን። ቀጥተኛውን መንገድ ምራን፣ ኻቲማችንንም አሳምርልን። ለአይናችን ማረፊያ ለልባችንም መርጊያ የሚሆን

​ያ ሰታር! 🤲🏽
ውስጥ ውጫችንን፣ ግራ ቀኛችንን፣ ፊት ኋላችንን በኑር አስጊጠው። ሀያእና ተቅዋን አላብሰን። በዱንያም በአኺራም አክብረን እንጂ አታዋርደን። አይባችንን ሰትርልን። ከኩራትና ከምቀኝነት ጠብቀን። አመስጋኝ፣ ባለው ተብቃቂ፣ ለጋስ፣ ቸርና አዛኝ አድርገን።

​ኢላሂ! 🤲🏼
የሰውን እጅ ከማየት አንተ ጠብቀን፤ እዳችንን ክፈልልን። የልባችንን መሻት አንተ ታውቃለህና የሚፈልገውን ሙላው፤ ምናልባት ያ የተመኘነው ነገር ለእኛ መጥፎ ከሆነ ያን ነገር ከእኛ አርቀህ ኸይር የሆነውን አሳካልን።

​ያ አላህ! 🤲🏽
ጠቃሚ እውቀትንና ተቀባይነት ያለው ስራ ወፍቀን። ህይወታችንን ረጅም፣ ዓፊያችንን ካሚል፣ ሪዝቃችንን ሰፊ አድርገው። ቁርዓንን የልባችን መርጊያ፣ ሰላትን የአይናችን ማረፊያ አድርግልን። ትንሹንም ትልቁንም፣ በግልጽም ሆነ በድብቅ የሰራነውን ወንጀል ማረን።

​ያ ረብ! 🤲🏽
ከቀብርና ከትንሳኤ ቀን ቅጣት ጠብቀን። ኪታባቸውን በቀኝ እጃቸው ከሚቀበሉት፣ ከዓርሽ ጥላ ስር ከሚሰበሰቡት አድርገን። ሲሯጥ ላይ እግራችንን አፅናልን። ከጀሀነም እሳት ነጃ በለን። የረሱለላህን (ሰ.ዐ.ወ) ሀውድ በእጃቸው ከሚጠጡትና ጀነተል ፊርደውስ ውስጥ ከሳቸው ጋር የቅርብ ጎረቤት ከሚሆኑት አድርገን።

ያረብ ይህን ውንድሜን ካለበት ጭንቀት ሁሉ ነጃ በለው በደስታ ብዛት የሚያለቅስበትን እርዚቅ ይስጥህ
​አሚን አላሁመ አሚን! 🤲🏽


ትላንትና ሞተው የቀበርናቸው ሰዎች ሁሉም ትላንት እንደሚምቱ አያውቁም ነበር
እኔና አናንተም ልክ እንደዚሁ አናውቅም‼


እስቲ ሁላችሁም ከልባችሁ ዱዓ አርጉልኝ ውዶቼ🥰


ጁማአ ሰገዳችሁ?👍👎


ልጆች ደና አደራችሁ


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
አንድቀንም ቢሆን በቅናት ምትደርሰኝ ትሮረኛለች ብዬ አስቤ አላቅም ነበር subhank ልዩነታችን እሷ ያገባች መሆንዋ ነው🤭

ቴበርቼ ሰላም🙄😁


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
እዚ video ውስጥ ራሴን አየሁት እና የሆነ ቦታ ለመድረስ አልሚያለሁ ግና መድረስ ምችል አይመስለኝም ልክ እንደልጁ ከኔሰባራ ልብጋ የምትሮጥ እናት አለችኝ ሱብሀነላህ አለምላይ ያልህ ቢያገል እናት እናት ናት አላህ አፊያዋንም ብዙ እድሜዋን ረጅም ያድርግልን የሁላችንንም

harmeko..እንቅፍት አይንካሽ


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
እኔ እኔ እኔ አትበል ማን ነህ አንተ?


🔺አላህ የከለከለው ትልቁ በደል #ክፍል9
~~~
በሙስሊሞች መካከል እየተፈፀሙ ካሉ የሽርክ ተግባራቶች መካከል፡
12 ﺍﻟﺘﻌﻠﻖ ﺑﺎﻷﺳﺒﺎﺏ ﻣﻦ ﺩﻭﻥ ﺍﻟﻠﻪ ﺗﺒﺎﺭﻙ ﻭﺗﻌﺎﻟﻰ،
12/ ሰበብ አድራጊ/ፈጣሪ የሆነውን ጌታ በመርሳት ሰበቦች ላይ ብቻ መንጠልጠል፡
ﻭﺍﻟﻮﺍﺟﺐ ﺍﻟﺘﻮﻛﻞ ﻋﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻭﺣﺪﻩ، ﻓﻴﺘﻌﻠﻖ ﺍﻟﻘﻠﺐ ﺑﺎﻟﻠﻪ ﻭﺣﺪﻩ ﻣﻊ ﺍﻷﺧﺬ ﺑﺎﻷﺳﺒﺎﺏ ﺍﻟﺸﺮﻋﻴﺔ ﴿ ﻭَﻋَﻠَﻰ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻓَﺘَﻮَﻛَّﻠُﻮﺍ ﺇِﻥْ ﻛُﻨْﺘُﻢْ ﻣُﺆْﻣِﻨِﻴﻦَ ﴾ .
በአማኞች ላይ ግድ የሚሆነው በአሏህ መመካትና ጉዳይን ሁሉ ወደ እርሱ ማስጠጋት ነው።
  የሰው ልጅ ቀልብ በጌታው ላይ ብቻ መንጠልጠል ይኖርባታል ይህም ሲባል ሸሪአ የፈቀዳቸው የሆኑ ሰበቦችን ከማድረስ ጋ መሆን አለበት።ጌታችንም በእርሱ ብቻ እንድንመካና ጉዳያችንን ወደ እርሱ እንዲናስጠጋ እንድህ ሲል ተናገረ"‼️በአሏህ ላይ ብቻ ተመኩ እናንተ አማኒያኖች/ ሙእሚኖች ከሆናችሁ‼️"።
‼️ማስታወሻ‼️
የሚንጠለጠልባቸው ሰበቦች ሸሪአዊ ሰበቦች ከሆኑና አድራጊው አሏህ ሱብሀነሁ ወተአላ ነው ካለ ችግር የለም።ነገር ግን ሰበቧ ራሷን ችላ ነገሩን ማስገኘት ትችላለች ብሎ ካመነ ሸሪአዊ ሰበብ ብትሆንም ከኢስላም የሚያስወጣ ትልቅ ሽርክ ይሆናል።
ሌላኛው በሙስሊሞች መካከል እየተፈፀሙ ካሉ የሽርክ ተግባራቶች መካከል፡
ﺍﺗﺨﺎﺫ ﺣﻠﻘﺔ ﺃﻭ ﺧﺎﺗﻢ ﺃﻭ ﺣﺒﻞ ﺃﻭ ﺃﻱ ﺣﺮﺯ ﻟﺠﻠﺐ ﺍﻟﺨﻴﺮ ﺃﻭ ﺩﻓﻊ ﺍﻟﺸﺮ
ቀለበት፣ክር/ገመድ፣ሂርዝና መሰል ነገሮችን እግር፣እጅ፣አንገትና መሰል ቦታወች ላይ መጥፎ ነገርን ሳይመጣ ለመከላከልና ከመጣ ብኋላ ለማንሳት በሚል ሙግት ማንጠልጠል።
👌ﻓﻌﻦ ﺍﺑﻦ ﻣﺴﻌﻮﺩ ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻪ ﻗﺎﻝ : ﺳﻤﻌﺖ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﺻَﻠَّﻰ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﻭَﺳَﻠَّﻢَ ﻳﻘﻮﻝ : ‏( ﺇﻥ ﺍﻟﺮﻗﻰ ﻭﺍﻟﺘﻤﺎﺋﻢ ﻭﺍﻟﺘِﻮَﻟﺔ ﺷﺮﻙ ‏) ﺭﻭﺍﻩ ﺃﺣﻤﺪ ﻭﺃﺑﻮ ﺩﺍﻭﺩ ﻭﺻﺤﺤﻪ ﺍﻷﻟﺒﺎﻧﻲ،
የአሏህ መልዕክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ኢብኑ መስኡድ ረደየሏሁ አንሁ በዘገቡት ሀድስ እንድህ አሉ" ሩቃ፣ሂርዝና መስተፋቅር ማጋራት ናቸው"። አህመድ እና አቡ ዳውድ ዘግበውታል፡ሸይኹል አልባኒ ሶሂህ ብለውታል።
ﻭﺍﻟﺘﻮﻟﺔ ﺷﻲﺀ ﺗﺼﻨﻌﻪ ﺑﻌﺾ ﺍﻟﻨﺴﺎﺀ ﻷﺯﻭﺍﺟﻬﻦ ﻟﺘﺰﺩﺍﺩ ﻣﺤﺒﺘﻪ ﻟﻬﺎ .
መስተፋቅር ማለት አንዳንድ ሴቶች ባላቸው ለእነርሱ ያለው ውደታ እንድጨመር ሲሉ የሚሰሩት ነው።
‼️ማስታወሻ‼️
👉ሩቃ በሌላ ቦታ ላይ መፈቀዱ መጥቷል ነገር ግን ሁለቱ ሀራምነታቸው ይቀጥላል።
እዲሁም በሙስሊሞች መካከል እየተፈፀሙ ካሉ የሽርክ ተግባራቶች መካከል፡
ﻗﻮﻝ : ‏( ﻣُﻄِﺮْﻧَﺎ ﺑِﻨَﻮْﺀِ ﻛَﺬَﺍ ﻭَﻛَﺬَﺍ ‏)

ዝናብ በተዘነቡ ጊዜ "እገሌ በተባለው ኮኮብ አዘነበንል" ማለታቸው፡
ﻭﺇذا ﺃﺭﺍﺩ ﺑﺬﻟﻚ ﺃﻥ ﺍﻟﻨﻮﺀ ﻫﻮ ﺍﻟﺬﻱ ﺃﺣﺪﺙ ﺍﻟﻤﻄﺮ ﻭﻫﻮ ﺍﻟﻤﺘﺼﺮﻑ ﻓﻲ ﺍﻟﻜﻮﻥ ﻓﻬﺬﺍ ﺷﺮﻙ ﺃﻛﺒﺮ،
የሰው ልጅ ይህንን በሚል ጊዜ ኮኮቡ ራሱን ችሎ  ነው ያዘነበልን፣ፍጥረተ አለሙን የማገላበጥ አቅም አለው ብሎ ካመነ ከኢስላም የሚያስወጣ ትልቅ ሽርክ ፈፅሟል።
👌 ﻭﺇﻥ ﻛﺎﻥ ﻗﺼﺪﻩ ﺃﻥ ﺍﻟﻨﻮﺀ ﺳﺒﺐ ﻓﻬﺬﺍ ﺷﺮﻙ ﺃﺻﻐﺮ،
ነገር ግን ኮኮቡ ለዝናቡ መዝነብ ሰበብ ብቻ ነው ብሎ ካሰበ ይሄ ትንሹ ሽርክ ይሆናል።
ﻓﻠﻴﺲ ﻟﻠﻨﻮﺀ ﺗﺴﺒﺐ ﺑﻞ ﻛﻠﻪ ﻣﻦ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﺰ ﻭﺟﻞ،
ለክዋክብቶች ዝናብ ለመዝነቡ ሰበብነት የላቸውም እንደውም ሁሉም ከአሏህ ሱብሀነሁ ወተአላ ነው።
ﻭﺍﻟﻤﺸﺮﻭﻉ ﺃﻥ ﻳﻘﺎﻝ : ﻣﻄﺮﻧﺎ ﺑﻔﻀﻞ ﺍﻟﻠﻪ ﻭﺭﺣﻤﺘﻪ .
የሚፈቀደው በአሏህ ቱርፋትና በእዝነቱ ተዘነብን ማለት ነው።
ማስታወሻ‼️
①ከአሏህ ውጭ ያለ አካል ሊሰራው የማይችልን ነገር ወደ ሌላ አካል ማስጠጋት ትልቅ ሽርክ ሲሆን፡
②በማንኛውንም የአሏህ ፀጋ ሸሪአ ሰበብ ያላደረገውን እኛ ሰበብ ካደረግን ትንሹ ሽርክ ይሆናል።

ክፍል 10 ይቀጥላል....
ቻናሉ➥ t.me/mustefa_Apologetics


🔺አላህ የከለከለው ትልቁ በደል #ክፍል8
~~~
በሙስሊሞች መካከል እየተፈፀሙ ካሉ የሽርክ ተግባራቶች መካከል፡
11 ﻗﻮﻝ ﺍﻹﻧﺴﺎﻥ ﺑﻌﺪ ﺣﺪﻭﺙ ﺃﻣﺮ ﻳﻜﺮﻫﻪ
: ﻟﻮ ﺃﻧﻨﻲ ﻓﻌﻠﺖ ﻛﺬﺍ ﻟﻜﺎﻥ ﻛﺬﺍ ﻭﻛﺬﺍ .
11/አንድ ሰው የሚጠላው ነገር በተከሰተ ጊዜ ይሄን ይሄን አድርጌ ቢሆን ኖሮ ይህ ይህ ባልተከሰተ ነበር ማለት‼️።
👌ﻓﻬﺬﺍ ﺍﻻﻋﺘﺮﺍﺽ ﻣﺤﺮﻡ؛ ﻷﻧﻪ ﺍﻋﺘﺮﺍﺽ ﻋﻠﻰ ﺍﻟﻘﺪﺭ،
✅ይህ ሀራም የሆነ ቀድርን( የአሏህን ውሳኔ) መፃረር ነው።
👌ﻭﺍﻟﻨﺒﻲ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﻳﻘﻮﻝ : " ﺍﺣﺮﺹ ﻋﻠﻰ ﻣﺎ ﻳﻨﻔﻌﻚ، ﻭﺍﺳﺘﻌﻦ ﺑﺎﻟﻠﻪ، ﻭﻻ ﺗﻌﺠﺰ، ﻓﺈﻥ ﺃﺻﺎﺑﻚ ﺷﻲﺀ ﻓﻼ ﺗﻘﻞ : ﻟﻮ ﺃﻧﻲ ﻓﻌﻠﺖ ﻛﺬﺍ ﻟﻜﺎﻥ ﻛﺬﺍ ﻭﻛﺬﺍ، ﻭﻟﻜﻦ ﻗﻞ : ﻗﺪّﺭ ﺍﻟﻠﻪ ﻭﻣﺎ ﺷﺎﺀ ﻓﻌﻞ، ﻓﺈﻥ ﻟﻮ ﺗﻔﺘﺢ ﻋﻤﻞ ﺍﻟﺸﻴﻄﺎﻥ " ﺭﻭﺍﻩ ﻣﺴﻠﻢ .
✅የአሏህ መልዕክተኛም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለመ ኢማሙ ሙስሊ በዘገቡት ሀድስ " በሚጠቅምህ ነገር ላይ ትጋ(በርታ)በጌታህም ታገዝ ፣አትድከም፣አንዳች ነገር ( የምትጠላው) ቢያጋጥምህ ይሄን ይሄን ባደርግ ኖሮ ይህ ይህ አይከሰትም ነበር አትበል። ነገር ግን አሏህ ሱብሀነሁ ወተአላ የወሰነውንና የፈቀደውን አደረገ በል፡👉ባደርግ ኖሮ የምትለው ቃል ለሸይጧን ተግባር  በር ትከፍታለችና"።

👉ማስታወሻ‼️
አንድ ነገር ከመከሰቱ በፊት ያለንን ሀይልና ጊዜ ተጠቅመን አማራጮችን አሟጠን መጠቀም እንዳለብን ሸሪአችን አስተሞሮናል ‼️ለነገሮች ሰበብ ማድረስ በቀደር   ከማመን ይቆጠራል።
12 ﺍﻟﺘﻌﻠﻖ ﺑﺎﻷﺳﺒﺎﺏ ﻣﻦ ﺩﻭﻥ ﺍﻟﻠﻪ ﺗﺒﺎﺭﻙ ﻭﺗﻌﺎﻟﻰ،
12/ ሰበብ አድራጊ/ፈጣሪ የሆነውን ጌታ በመርሳት ሰበቦች ላይ ብቻ መንጠልጠል፡
👌ﻭﺍﻟﻮﺍﺟﺐ ﺍﻟﺘﻮﻛﻞ ﻋﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻭﺣﺪﻩ، ﻓﻴﺘﻌﻠﻖ ﺍﻟﻘﻠﺐ ﺑﺎﻟﻠﻪ ﻭﺣﺪﻩ ﻣﻊ ﺍﻷﺧﺬ ﺑﺎﻷﺳﺒﺎﺏ ﺍﻟﺸﺮﻋﻴﺔ ﴿ ﻭَﻋَﻠَﻰ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻓَﺘَﻮَﻛَّﻠُﻮﺍ ﺇِﻥْ ﻛُﻨْﺘُﻢْ ﻣُﺆْﻣِﻨِﻴﻦَ ﴾ .
በአማኞች ላይ ግድ የሚሆነው በአሏህ መመካትና ጉዳይን ሁሉ ወደ እርሱ ማስጠጋት ነው።
  የሰው ልጅ ቀልብ በጌታው ላይ ብቻ መንጠልጠል ይኖርባታል ይህም ሲባል ሸሪአ የፈቀዳቸው የሆኑ ሰበቦችን ከማድረስ ጋ መሆን አለበት።ጌታችንም በእርሱ ብቻ እንድንመካና ጉዳያችንን ወደ እርሱ እንዲናስጠጋ እንድህ ሲል ተናገረ"‼️በአሏህ ላይ ብቻ ተመኩ እናንተ አማኒያኖች/ ሙእሚኖች ከሆናች‼️"።
ማስታወሻ‼️
የሚንጠለጠልባቸው ሰበቦች ሸሪአዊ ሰበቦች ከሆኑና አድራጊው አሏህ ሱብሀነሁ ወተአላ ነው ካለ ችግር የለም።ነገር ግን ሰበቧ ራሷን ችላ ነገሩን ማስገኘት ትችላለች ብሎ ካመነ ሸሪአዊ ሰበብ ብትሆንም ከኢስላም የሚያስወጣ ትልቅ ሽርክ ይሆናል።

ክፍል 9 ይቀጥላል....
ቻናሉ➥ t.me/mustefa_Apologetics


🔺አላህ የከለከለው ትልቁ በደል #ክፍል7
~~~
በሙስሊሞች መካከል እየተፈፀሙ ካሉ የሽርክ ተግባራቶች መካከል፡
-9 ﺍﻟﻨﺬﺭ ﻟﻐﻴﺮ ﺍﻟﻠﻪ،
⑨ከአሏህ ውጭ ላለ አካል ስለት መግባት ነው።
👌 ﻓﺎﻟﻨﺬﺭ ﻋﺒﺎﺩﺓ ﻟﻠﻪ ﻻ ﺗﺼﺮﻑ ﺇﻟﻰ ﺇﻻ ﺍﻟﻠﻪ ﻭﺣﺪﻩ ﻛﺎﻟﻘﻴﺎﻡ ﻣﻊ ﺍﻟﺨﺸﻮﻉ ﻭﺍﻟﺮﻛﻮﻉ ﻭﺍﻟﺴﺠﻮﺩ، ﻭﺻﺮﻑ ﺃﻱ ﻋﺒﺎﺩﺓ ﻟﻐﻴﺮ ﺍﻟﻠﻪ ﺷﺮﻙ .
ስለት አምልኮ ነው ይህ አምልኮ ደግሞ ከአሏህ ውጭ ላለ አካል ተሸርፎ መሰጠት አይችልም።ከእነኝህ ስለቶች መካከል በኹሹእ መስገድ፣ማጎንበስ፣ስጁድ መደፋትና መሰል ተግባራቶች ሲሆኑ አንዷንም ለሌላ አካል አዙሮ መስጠት ማጋራት ነው።
‼️ልብበሉ
👉ነዝር )የሚለው እንደ ኦለማዎች ተፍሲር አንዳንዶቹ ሁሉም የአምልኮ አይነቶች መጠርያ ነው።ስለዚህ እነዚህን አምልኮዎች ከአሏህ ውጭ ማድረግ ሽርክ ነው አሉ።
ሌሎች👉 ነዝር ማለት አንድ አካል አንድ ሀጃው እንድወጣለት ሲፈልግ አሏህ ሆይ ይሄንን ሀጃየን ካወጣህልኝ ይሄንን ላደርግ ብሎ የሚሳለው ሲሆን ይህ ስለት ከአሏህ ውጭ ላለ አካል ከተገባ ሽርክ ነው አሉ።
ማስታወሻ
ለአሏህም ቢሆን ስለት መግባት አይበረታታም ምክንያቱም አሏህ ሱብሀነሁ ወተአላ የባሪያዎቹን ሀጃ በለመኑት ጊዜ ያለ ልዋጭ አያሳካም የሚል ፈህም ያስይዛልና።ግን ለአሏህ ስለት ከተገባ መሙላቱ ዋጅብ ነው።ስለትመግባት ሀራም ነው ያሉም ኦለማዎች አሉ።
ጭብጥ
ስለት አንግባ አጋጣሚ ከገባን ለአሏህ ብቻ ሲሆን መሙላት ዋጅብ ነው።ከአሏህ ውጭ ላለ አካል ከሆነ ትልቅ ሽርክ ነው።
10 ﺍﻻﺳﺘﻬﺰﺍﺀ ﺑﺎﻟﺪﻳﻦ ﻭﺑﺎﻟﺼﺎﻟﺤﻴﻦ ﻭﺑﺸﻌﺎﺋﺮ ﺍﻹﺳﻼﻡ،

10/በሀይማኖት፣በሀይማኖተኞችና በሀይማኖት መገለጫወች ማቾፍ
👌ﻛﺎﻟﺼﻼﺓ ﺃﻭ ﺍﻟﻠﺤﻴﺔ أوالنقاب أو تقصر الثوب ﺃﻭ ﻏﻴﺮ ﺫﻟﻚ ﻣﻤﺎ ﻭﺭﺩ ﻓﻲ ﺍﻟﻘﺮﺁﻥ ﺃﻭ ﺍﻟﺴﻨﺔ،
✅በሶላትና መሰል ኢባዳወች፣በፂም፣በኒቃብ ፣ሱሪን በማሳጠርና መሰል የሀይማኖት መገለጫወች በቁርአንና በሀድስ የመጡ በሆኑት ማሾፍ።
👌 ﻗﺎﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﺗﻌﺎﻟﻰ : ﴿ ﻭَﻟَﺌِﻦْ ﺳَﺄَﻟْﺘَﻬُﻢْ ﻟَﻴَﻘُﻮﻟُﻦَّ ﺇِﻧَّﻤَﺎ ﻛُﻨَّﺎ ﻧَﺨُﻮﺽُ ﻭَﻧَﻠْﻌَﺐُ ﻗُﻞْ ﺃَﺑِﺎﻟﻠَّﻪِ ﻭَﺁﻳَﺎﺗِﻪِ ﻭَﺭَﺳُﻮﻟِﻪِ ﻛُﻨْﺘُﻢْ ﺗَﺴْﺘَﻬْﺰِﺋُﻮﻥَ * ﻟَﺎ ﺗَﻌْﺘَﺬِﺭُﻭﺍ ﻗَﺪْ ﻛَﻔَﺮْﺗُﻢْ ﺑَﻌْﺪَ ﺇِﻳﻤَﺎﻧِﻜُﻢْ‏[ ﺍﻟﺘﻮﺑﺔ : 65 ، 66 ‏] ،
አሏሁ ሱብሀነሁ ወተአላ በመልዕክተኛው እና በሰሀብዮች ሲያላግጡና ሲያቾፉ የነበሩት ሙናፊቆች ምንም እንኳ እየቀለድን ነው፣የመንገድ መቁረጫ ንግግር ነው ቢሉም እንኳ ከኢስላም እንደወጡና ምክንያታቸው ተቀባይነት እንደለለው እንድህ ሲል ተናገረ ።" ብትጠይቃቸው እኛማ በንግግር ውስጥ እየዋኘንና እየተጫወትን ነው ይሉሀል፡በአሏህ፣በታአምራቶቹ( በሰሀባዎቹ)፣ በመልዕክተኛው ነውን የምታላግጡት!!? አታመካኙ በእርግጥም ካመናችሁ ብኋላ ክዳችኋል"።
ማስታወሻ‼️
ከሀይማኖት መገለጫወች አንዱን መጥላትና ማቾፍ ከኢስላም የሚያስወጣ ተግባር ነው።የሚጠላውና የሚያቾፈው አካል ቢሰራበትም እንኳ።ለምሳሌ ሱሪን ማሳጠር፣ፂምን ማሳደግ፣ኒቃብ መልበስ መሰል ነገሮችን መጥላት ከኢስላም የሚያስወጣ ተግባር ነው።ሰውየው ራሱ ቢተገብረውም።
#ጥቆማ‼️
አንድ ሰው በራሱ ድክመት እነዚህንና መሰል የሀይማኖት መገለጫወች መስራት ቢያቅተው ሊወዳቸው ይገባል።ያኔ ባለ መስራቱ ወንጀለኛ እንጅ ከኢስላም ይወጣል የሚል ብይን አይሰጠውም

ክፍል 8 ይቀጥላል....
ቻናሉ➥ t.me/mustefa_Apologetics

┎┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┒
  ይቀጥላል  ከ50 ላይክ ቡሀላ
┖┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┚


🔺አላህ የከለከለው ትልቁ በደል ክፍል6
~~~
በሙስሊሞች መካከል እየተፈፀሙ ካላ የሽርክ ተግባራቶች መካከል፡
6 ﺍﻟﺴﺤﺮ ﻭﺍﻟﻜﻬﺎﻧﺔ ﻭﺍﻟﺬﻫﺎﺏ إلى ﺍﻟﻤﺸﻌﻮﺫﻳﻦ ﻭﺍﻟﻤﻨﺠﻤﻴﻦ
⑥ አስማትና ጥንቆላ እንደዚሁም ወደ አጭበርባሪዎችና ኮኮብ ቆጣሪዎች መሄድ።
👌ﺭﻭﻯ ﺃﺣﻤﺪ ﻭﺍﻟﺤﺎﻛﻢ ﻭﺻﺤﺤﻪ ﺍﻷﻟﺒﺎﻧﻲ ﻣﻦ ﺣﺪﻳﺚ ﺃﺑﻲ ﻫﺮﻳﺮﺓ ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻪ ﺃﻥ ﺍﻟﻨﺒﻲ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﻗﺎﻝ : ‏« ﻣﻦ ﺃﺗﻰ ﻋﺮﺍﻓﺎً ﺃﻭ ﻛﺎﻫﻨﺎً ﻓﺼﺪﻗﻪ ﺑﻤﺎ ﻳﻘﻮﻝ ﻓﻘﺪ ﻛﻔﺮ ﺑﻤﺎ ﺃﻧﺰﻝ ﻋﻠﻰ ﻣﺤﻤﺪ ‏» .
✅ኢማሙ አህመድና ኢማሙ አልሀኪም የዘገቡትና ኢማሙ አል አልባኒይ ሶሂህ ያሉት ሀድስ አባ ሁረይራ ነብዩ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ እንድህ አሉ አለ" አዋቂ ወይም ጠንቋይ ዘንድ የሄደና የሚናገረውን ሀቅ ብሎ የተቀበለው  በእርግጥ በሙሀመድ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ላይ በወረደው ( በቁርአን) ክዷል"።

‼️ማስጨበጫ〰
ሲህር ወይም አስማት የሚባለው አደገኛ በሽታ ስለሆነ አሏሁ ሱብሀነሁ ወተአላ ቁርአን ላይ እሱን ያስተማረና በሱ የሰራ በጌታው የካደና በአኼራ ምንም ድርሻ የሌለው መሆኑን ገልፅዋል።ሲህር የሰራም ፣ያሰራም፣የተማረም፣ያስተማረም፣በድርጊቱ የወደደም ከኢስላም እንደሚወጣ ኦለማዎች ያስቀምጣሉ።
7 ﺍﻟﺤﻠﻒ ﺑﻐﻴﺮ ﺍﻟﻠﻪ تعلى
⑦ከአሏህ ውጭ ባሉ አካላቶች መማል፡
👌 ﺭﻭﻯ ﺃﺣﻤﺪ ﻭﺍﻟﺘﺮﻣﺬﻱ ﻭﺍﻟﺤﺎﻛﻢ ﻭﺻﺤﺤﻪ ﺍﻷﻟﺒﺎﻧﻲ ﻋﻦ ﺍﺑﻦ ﻋﻤﺮ ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻬﻤﺎ ﺃﻥ ﺍﻟﻨﺒﻲ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﻗﺎﻝ : ‏« ﻣﻦ ﺣﻠﻒ ﺑﻐﻴﺮ ﺍﻟﻠﻪ ﻓﻘﺪ ﺃﺷﺮﻙ ‏» ،
✅ኢማሙ አህመድ፣ኢማሙ አቲርሚዚይና ኢማሙ አል ሀኪም እንደዘገቡትና ኢማሙ አል አልባኒይ ሶሂህ እንዳሉት ኢብኑ ኡመር ረደየሏሁ አንሁ እንድህ አሉ" የአሏህ መልእክተኛ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ እንድህ አሉ" ከአሏህ ሱብሀነሁ ወተአላ ውጭ ባለ ነገር የማለ በእርግጥም አጋርቷል"።  
‼️ልብ በሉ〰
ከአሏህ ውጭ ባለ ነገር መማል ከከባኢር ወንጀሎች ሁሉ የሚበልጥ ታላቅ ወንጀል ነው።በአሏህ ምሎ ውሸት ማውራት ከአሏህ ውጭ ባለ አካል ምሎ እውነት ከማውራት ይሻላል።
-8 ﺍﻟﺬﺑﺢ ﻟﻐﻴﺮ ﺍﻟﻠﻪ ﺗﻌﺎﻟﻰ،
⑧ ከአሏህ ውጭ ላለ አካል ማረድ
👌ﻭﻫﻮ ﻣﻦ ﺍﻟﺸﺮﻙ ﺍﻷﻛﺒﺮ ﻷﻥ ﺍﻟﺬﺑﺢ  ﻋﺒﺎﺩﺓ ﻭﺻﺮﻓﻬﺎ ﻟﻐﻴﺮ ﺍﻟﻠﻪ ﺗﻌﺎﻟﻰ ﺷﺮﻙ، ﻛﺎﻟﺬﺑﺢ ﻟﻠﻘﺒﻮﺭ ﻭﺍﻷﻭﻟﻴﺎﺀ ﻭﺍﻟﺘﻘﺮﺏ ﺇﻟﻴﻬﻢ ﺑﻬﺎ' ﻭﺍﻟﺬﺑﺢ ﻟﻠﺠﻦ ﺗﻘﺮﺑﺎً ﺇﻟﻴﻬﻢ ﻣﻦ ﻗﺒﻞ ﺍﻟﺴﺤﺮﺓ ﺃﻭ ﻣﻦ ﻳﻄﻴﻌﻬﻢ ﻣﻦ ﺍﻟﺠﻬﺎﻝ ﺍﻟﺬﻳﻦ ﻳﺄﺗﻮﻥ ﺇﻟﻴﻬﻢ ﻃﻠﺒﺎً ﻟﻠﺸﻔﺎﺀ، ﻭﺍﻟﺬﺑﺢ ﻋﻨﺪ ﺑﻨﺎﺀ ﺍﻟﺒﻴﺖ ﻭﺗﻠﻄﻴﺦ ﺩﻡ ﺍﻟﺬﺑﻴﺤﺔ ﻋﻠﻰ ﻗﻮﺍﻋﺪ ﺍﻟﺒﻨﺎﺀ ﻋﻨﺪ ﺗﺄﺳﻴﺴﻪ، ﺃﻭ ﺍﻟﺬﺑﺢ ﻋﻨﺪ ﺳﻜﻦ ﺍﻟﺒﻴﺖ ﺍﻟﺠﺪﻳﺪ ﻭﺗﻠﻄﻴﺦ ﺩﻣﻪ ﻋﻞ ﺟﺪﺭﺍﻧﻪ ﻣﻦ ﺃﺟﻞ ﺣﻤﺎﻳﺘﻪ ﻣﻦ ﺍﻟﺠﻦ، ﻭﻫﺬﺍ ﻛﻠﻪ ﺷﺮﻙ ﻻ ﻳﺠﻮﺯ
✅እሱም ደግሞ ከትልልቅ የሽርክ አይነቶች ይመደባል ምክንያቱም እርድ ከአምልኮ አይነቶች ሲሆን ከአሏህ ውጭ ላለ አካል ሸርፎ ከተሰጠ ማጋራት ይሆናል።ለመቃብር ናለአውሊያዎች ማረድ፣በሷም ወደነሱ መቃረብ፣ለጅን መቃረቢያነት ማረድ ከአስማተኞች በኩል ወይም አስማተኞችን የሚታዘዝና ወደነሱ ፈውስን ፈልጎ ከሚመጣ  አላዋቂያን አካል፣አድስ ቤት ሲሰሩ ማረድና ምሰሶወቹን በደም መለወስ፣አድስ ቤት ለመኖር ሲገቡ ከጅን ለመጠበቅ በሚል አርዶ ግርግዳውን በደም መለወስ ወዘተ የሽርክ ተግባራቶች ናቸው ሁሉም አይቻሉም።

ክፍል 7 ይቀጥላል....
ቻናሉ➥ t.me/mustefa_Apologetics

┎┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┒
  ይቀጥላል  ከ50 ላይክ ቡሀላ
┖┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┚


በዚህ ቻናል አብዛኛው ወዶች ነው ወይስ ሴቶች ነው ያሉት?

ወዶች👍 vs ሴቶች🥰


🔺አላህ የከለከለው ትልቁ በደል ክፍል5
~~~
በሙስሊሞች መካከል እየተፈፀሙ ካሉ የሽርክ ተግባራቶች መካከል፡

5 ﺍﻟﺘﺒﺮﻙ ﺑﻘﺒﺮ ﺍﻟﻨﺒﻲ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﺃﻭ ﺍﻟﺘﻤﺴﺢ ﺑﻪ ﺃﻭ ﺍﻟﺴﺆﺍﻝ ﻋﻨﺪﻩ، ﻭﻛﺬﺍ ﻏﻴﺮﻩ ﻣﻦ ﻗﺒﻮﺭ ﺍﻟﺼﺤﺎﺑﺔ ﻭﺍﻵﻝ ﻭﺍﻷﻭﻟﻴﺎﺀ ﺍﻟﺼﺎﻟﺤﻴﻦ، ﻭﻛﺬﺍ ﺍﻟﺘﺒﺮﻙ ﺑﺎﻟﺸﺠﺮ ﻭﺍﻟﺤﺠﺮ ﻭﻧﺤﻮﻫﻤﺎ
በነብዩ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ መቃብር ተበሩክን/ ረድኢትን መፈለግ ወይም ሂዶ መተሻሸት / መንከባለል ወይም ሀጃው እንድፈፀምለት ሂዶ መጠየቅ እንደዚሁም ከነብዩ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ውጭ ያሉ እሰሀብዮች (ሪዷኑሏሂ አለይሂም)  ቀብር ላይ ይመስል፣የአሏህ ደጋግ ባሪያዎች ቀብር ብሎም በተለያዩ ዛፎች ፣ድንጋይና መሰል ነገሮች ተበሩክ ማድረግ/ ረድኤትን መሻት።ሁሉም የሽርክ ተግባር ናቸው።

ክፍል 6 ይቀጥላል....
ቻናሉ➥ t.me/mustefa_Apologetics

┎┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┒
  ይቀጥላል  ከ50 ላይክ ቡሀላ
┖┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┚


🔺አላህ የከለከለው ትልቁ በደል ክፍል4
~~~
በሙስሊሞች መካከል እየተፈፀሙ ካሉ የሽርክ ተግባራቶች መካከል፡
📌 ﻧﺴﺒﺔ ﺍﻟﻨﻌﻤﺔ ﺇﻟﻰ ﺇﻧﺴﺎﻥ، ﺃﻭ ﺇﻟﻰ ﺑﻘﻌﺔ، ﺃﻭ ﺇﻟﻰ ﻓﻌﻞ ﻓﺎﻋﻞ، ﺃﻭ ﺇﻟﻰ ﺻﻨﻌﺔ، ﺃﻭ ﺇﻟﻰ ﻣﺨﻠﻮﻕ، ﻛﻞ ﺫﻟﻚ ﻣﻦ ﻧﺴﺒﺔ ﺍﻟﻨﻌﻢ ﺇﻟﻰ ﻏﻴﺮ ﺍﻟﻠﻪ، ﻭﻫﻮ ﻧﻮﻉ ﻣﻦ ﺃﻧﻮﺍﻉ ﺍﻟﺸﺮﻙ ﺍﻷﺻﻐﺮ ﺑﺎﻟﻠﻪ،
አሏሁ ሱብሀነሁ የዋለልንን ፀጋ ወደ ሰዎች ወይም ቦታወች ወይም አንድ አካል ወደተገበረው ተግባር ወይም ወደ ፋብሪካ ወይም ወደ ፉጡራኖች ማስጠጋት። ይህ ሁሉ ፀጋን ከአሏህ ውጭ ለሆነ አካል ማስጠጋት ይባላል እሱም ከትንንሽ የሽርክ አይነቶች ይመደባል።
👌ﻓﻌﻦ ﺍﺑﻦ ﻋﺒﺎﺱ ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻪ ﻓﻲ ﻗﻮﻟﻪ ﺗﻌﺎﻟﻰ : ﴿ ﻓَﻠَﺎ ﺗَﺠْﻌَﻠُﻮﺍ ﻟِﻠَّﻪِ ﺃَﻧْﺪَﺍﺩًﺍ ﴾ ‏[ ﺍﻟﺒﻘﺮﺓ : 22 ‏] ﻗﺎﻝ : " ﺍﻷﻧﺪﺍﺩ ﻫﻮ ﺍﻟﺸﺮﻙ  ﻭﺗﻘﻮﻝ : ﻭﻟﻮﻻ ﻛﻠﺒﺔ ﻫﺬﺍ ﻷﺗﺎﻧﺎ ﺍﻟﻠﺼﻮﺹ، ﻭﻟﻮﻻ ﺍﻟﺒﻂ  ﻓﻲ ﺍﻟﺪﺍﺭ ﻷﺗﻰ ﺍﻟﻠﺼﻮﺹ، ﻭﻗﻮﻝ ﺍﻟﺮﺟﻞ ﻟﺼﺎﺣﺒﻪ : ﻣﺎ ﺷﺎﺀ ﺍﻟﻠﻪ ﻭﺷﺌﺖ، ﻭﻗﻮﻝ ﺍﻟﺮﺟﻞ : ﻟﻮﻻ ﺍﻟﻠﻪ ﻭﻓﻼﻥ، ﻻ ﺗﺠﻌﻞ ﻓﻴﻬﺎ " ﻓﻼﻥ " ﻫﺬﺍ ﻛﻠﻪ ﺷﺮﻙ " ﺭﻭﺍﻩ ﺍﺑﻦ ﺃﺑﻲ ﺣﺎﺗﻢ .

✅ኢብኑ አባስ ረደየሏሁ አንሁ ከላይ የተጠቀሰውን የቁርአን አያ ማለትም"ለአሏህ ቢጣቢጤዎችን አታድርጉለት"( አል በቀራ 22) የሚለውን ሲያብራሩ "ቢጣቢጤ" ማለት ሽርክ ነው " ማለትህን ይመስል " ውሻዋ ባትኖር ሌቦች ይመጡን ነበር፣በቤት በቀቀኗ ባትኖር ሌቦች ይመጡ ነበር፣አንድ ሰው ለጓደኛው " የአሏህና ያንተ ፈቃድ ከሆነ" ማለቱ፣ አንድ ሰው ማለቱ " አሏህና እገሌ ባይኖሩ።።።።" እገሌ የሚል አትጨምር ሁሏም ሽርክ ነውና በማለት ኢብኑ አባስ ያስረዳሉ።ኢብኑ አቢ ሀቲም ዘግበውታል።

✅ማስታዎሻ ‼️ወንድሞቸ እና እህቶቸ በደንብ አስተውሉ እዚህ ጋ የማይቻለው ( و)  መጠቀማችን ነው (  ﻣﺎ ﺷﺎﺀ ﺍﻟﻠﻪ ﻭﺷﺌﺖ،) ምክንያቱም ቅደም ተከተልን ሳይሆን እኩልነትን ስለምታስይዝ። ምክንያቱም "እና" የሚል ትርጉም ስለምትሰጥ ነው። በአንፃሩ ግን( ثم) መጠቀም ይቻላል ( ﻣﺎ ﺷﺎﺀ ﺍﻟﻠﻪ ثم شئت) ይህም የሆነበት" ከዚያም" የሚል ትርጉም ስላላት ነው።

✅የአሏህ መልእክተኛም ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለመ  አንድ የገጠር ሰው መጥቶ ﻣﺎ ﺷﺎﺀ ﺍﻟﻠﻪ ﻭﺷﺌت ሲላቸው "ለአሏህ ቢጤ አደረከኝን !!? አሏህ ራሱ ብቻ ካሻ በል" በማለት መልሰዋል።በሌላ ዘገባ ደግሞ " አሏህ ከዚያም ። ካሻ በል" በማለት መልሰዋል። እነዚህና መሰል የሽርክ አይነቶች በንግግር የሚስታዋሉ ናቸው።ሁላችንም እንጠንቀቅ።

ክፍል 5 ይቀጥላል....
ቻናሉ➥ t.me/mustefa_Apologetics

┎┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┒
  ይቀጥላል  ከ50 ላይክ ቡሀላ
┖┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┚


🔺አላህ የከለከለው ትልቁ በደል ክፍል3
~~~
በሙስሊሞች መካከል እየተፈፀሙ ካሉ የሽርክ ተግባራቶች መካከል፡
📌 ﺍﻟﻐﻠﻮ ﻓﻲ ﻗﺒﻮﺭ ﺍﻟﺼﺎﻟﺤﻴﻦ، ﻓﻤﺠﺎﻭﺯﺓ ﺍﻟﺤﺪ ﻓﻲ ﻗﺒﻮﺭ ﺍﻟﺼﺎﻟﺤﻴﻦ ﻫﻲ ﻣﺠﺎﻭﺯﺓ ﻟﻤﺎ ﺃﻣﺮ ﺍﻟﺸﺎﺭﻉ ﺃﻥ ﺗﻜﻮﻥ ﻋﻠﻴﻪ ﺍﻟﻘﺒﻮﺭ؛ ﻷﻥ ﻗﺒﻮﺭ ﺍﻟﺼﺎﻟﺤﻴﻦ ﻻ ﺗﺨﺘﻠﻒ ﻋﻦ ﻗﺒﻮﺭ ﻏﻴﺮ ﺍﻟﺼﺎﻟﺤﻴﻦ،
በደጋግና መልካም የአሏህ ባሪያወች ቀብር ላይ ድንበር ማለፍ።ይህ ሲባል ሸሪአ በደጋጎች  ቀብር ዙርያ  ካስቀመጠው ድንበር መተላለፍ ማለት ነው።ምክንያቱም የደጋጎች ቀብር ከሌሎች አካላቶች ቀብር  የሚለይበት አንድም ነገር የለም።
👌ﻓﺎﻟﻐﻠﻮ ﻓﻴﻬﺎ ﻳﻜﻮﻥ ﺑﺮﻓﻌﻬﺎ، ﺃﻭ ﺑﺎﻟﺒﻨﺎﺀ ﻋﻠﻴﻬﺎ، ﺃﻭ ﺑﺎﺗﺨﺎﺫﻫﺎ ﻣﺴﺎﺟﺪ، ﻭﻛﻞ ﻫﺬﺍ ﻣﻦ ﺍﻟﻮﺳﺎﺋﻞ ﺍﻟﻤﺆﺩﻳﺔ ﺇﻟﻰ ﺍﻟﺸﺮﻙ ﺍﻷﻛﺒﺮ،
✅በሷሊሆች ቀብር ላይ ድንበር ማለፍ ሲባል ወደ ላይ ቀብሩን ከፍ በማድረግ፣እሷ ላይ ዶሪሆችን  በመገንባት፣መስገጃ ቦታ አድርጎ በመያዝ፣እና ሌሎችን ተግባራቶችን መተግበር ሲሆን እነዚህ ሁሉ ወደ ትልቁ ሽርክ የሚያዳርሱ ተግባራቶች ናቸው።
👌ﻭﻣﻦ ﺻﻮﺭ ﺍﻟﻐﻠﻮ ﻓﻲ ﻗﺒﻮﺭ ﺍﻟﺼﺎﻟﺤﻴﻦ ﺃﻥ ﺗُﺠﻌﻞ ﻭﺳﻴﻠﺔ ﻣﻦ ﺍﻟﻮﺳﺎﺋﻞ ﺍﻟﺘﻲ ﺗﻘﺮﺏ ﺇﻟﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﺟﻞ ﻭﻋﻼ ﺃﻭ ﺃﻥ ﻳﺘﺨﺬ ﺍﻟﻘﺒﺮ ﺃﻭ ﻣﻦ ﻓﻲ ﺍﻟﻘﺒﺮ ﺷﻔﻴﻌﺎ ﻟﻬﻢ ﻋﻨﺪ ﺍﻟﻠﻪ ﺟﻞ ﻭﻋﻼ ﺃﻭ ﻳﻨﺬﺭ ﻟﻠﻘﺒﺮ، ﺃﻭ ﻳﺬﺑﺢ ﻟﻪ، ﺃﻭ ﻳﺴﺘﺸﻔﻊ ﺑﺘﺮﺍﺑﻪ ﺍﻋﺘﻘﺎﺩﺍً ﺃﻧﻪ ﻭﺳﻴﻠﺔ ﻋﻨﺪ ﺍﻟﻠﻪ ﺟﻞ ﻭﻋﻼ .
✅ደጋግ ሰዎች መቃብር ላይ ከሚታለፉ ድንበር ማለፎች ወደ አሏህ ከሚያዳርሱ መዳረሻዎች አንዷ ተደርጋ መያዟ ነው።እንደዚሁም ቀብሩ ወይም የተቀበረው አካል አሏህ ዘንድ ያቃርባል/ ያዳርሳል ተብሎ መታሰቡ ወይም ስለት ለመቃብሩ ወይም ለተቀበረው አካል መሳሉ ወይም እርድ መታረዱ፣ በአፈሩ ምልጃ መፈልጉ መንከባለሉ ይህ ሁሉ ወደ አሏህ ያዳርሳል በሚል እምነት  ቢሆንም፡

ክፍል 4 ይቀጥላል....
ቻናሉ➥ t.me/mustefa_Apologetics

┎┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┒
  ይቀጥላል  ከ50 ላይክ ቡሀላ
┖┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┚


🔺አላህ የከለከለው ትልቁ ወንጀል ክፍል2
~~~
✅በሙስሊሞች መካከል እየተፈፀሙ ካሉ የሽርክ ተግባራቶች መካከል፡-
ﺍﻋﺘﻘﺎﺩ ﺃﻥ ﻏﻴﺮ ﺍﻟﻠﻪ ﺑﻴﺪﻩ ﺍﻟﻀﺮ ﺃﻭ ﺍﻟﻨﻔﻊ
#ጥቅምና ጉዳት ከአሏህ ሱብሀነሁ ወተአላ ውጭ ባለ አካል እጅ ይገኛል ብሎ ማመን።አሏሁ ሱብሀነሁ ወተአላ ይህንን የተሳሳተ እምነት እንድህ በማለት መሰረቱን ያሳጣዋል፡
👌﴿ ﻭَﺇِﻥْ ﻳَﻤْﺴَﺴْﻚَ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﺑِﻀُﺮٍّ ﻓَﻠَﺎ ﻛَﺎﺷِﻒَ ﻟَﻪُ ﺇِﻟَّﺎ ﻫُﻮَ ﻭَﺇِﻥْ ﻳَﻤْﺴَﺴْﻚَ ﺑِﺨَﻴْﺮٍ ﻓَﻬُﻮَ ﻋَﻠَﻰ ﻛُﻞِّ ﺷَﻲْﺀٍ ﻗَﺪِﻳﺮٌ ﴾ ‏[ ﺍﻷﻧﻌﺎﻡ 17 ‏] ،
"አሏህ ሱብሀነሁ ወተአላ በጉዳት ቢፈልግህ ጉዳቱን ከሱ ውጭ አንሽ የለም፡በጥሩ ነገር ቢፈልግህም እሱ በሁሉም ነገር ቻይ ነው"።(አል አንአም 17)

ﻗُﻞْ ﺃَﻓَﺮَﺃَﻳْﺘُﻢْ ﻣَﺎ ﺗَﺪْﻋُﻮﻥَ ﻣِﻦْ ﺩُﻭﻥِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺇِﻥْ ﺃَﺭَﺍﺩَﻧِﻲَ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﺑِﻀُﺮٍّ ﻫَﻞْ ﻫُﻦَّ ﻛَﺎﺷِﻔَﺎﺕُ ﺿُﺮِّﻩِ ﺃَﻭْ ﺃَﺭَﺍﺩَﻧِﻲ ﺑِﺮَﺣْﻤَﺔٍ ﻫَﻞْ ﻫُﻦَّ ﻣُﻤْﺴِﻜَﺎﺕُ ﺭَﺣْﻤَﺘِﻪِ ﻗُﻞْ ﺣَﺴْﺒِﻲَ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﻳَﺘَﻮَﻛَّﻞُ ﺍﻟْﻤُﺘَﻮَﻛِّﻠُﻮﻥَ ﴾ ‏[ ﺍﻟﺰﻣﺮ : 38 ‏] .

" በላቸው እስኪ ንገሩኝ እነዚያ ከአሏህ ውጭ የምትጠሯቸው አሏህ በክፉ ነገር ቢፈልገኝ ያንን ጉዳት አስወጋጅ ናቸውን❓ወይም በእዝነቱ ቢፈልገኝ እዝነቱን ያዥ( ከልካይ) ናቸውን❓ በላቸው አሏህ ብቻ በቂየ ነው የሚመኩ በዕርሱ ብቻ ይመኩ "( አዙመር 38)
   
ክፍል 3 ይቀጥላል....
ቻናሉ➥ t.me/mustefa_Apologetics

┎┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┒
  ይቀጥላል  ከ100 ላይክ ቡሀላ
┖┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┚


🔺አላህ የከለከለው ትልቁ በደል #ክፍል1
~~~
الشرك ﻣﻨﺘﺸﺮﺓ
ﺇﻥ ﺃﻋﻈﻢ ﻣﺎ ﺃﻣﺮ ﺍﻟﻠﻪ ﺑﻪ ﺍﻟﺘﻮﺣﻴﺪ، ﻭﺃﻋﻈﻢ ﻣﺎ ﻧﻬﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻪ ﺍﻟﺸﺮﻙ، ﻗﺎﻝ ﺗﻌﺎﻟﻰ : ﴿ ﻭَﺍﻋْﺒُﺪُﻭﺍ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻭَﻟَﺎ ﺗُﺸْﺮِﻛُﻮﺍ ﺑِﻪِ ﺷَﻴْﺌًﺎ ﴾ ‏[
ﺍﻟﻨﺴﺎﺀ : 36 ‏] ،
አሏህ ሱብሀነሁ ወተአላ ካዘዘባቸው ነገሮች ሁሉ ትልቁ ተውሂድ ነው።እንደዚሁም ከከለከላቸው ነገሮች ሁሉ ትልቁ ሽርክ ነው።
አሏሁ ጀለ ወአላ እንድህ ይላል"አሏህን ተገዙ በሱ ቅንጣትን አታጋሩበት።

👌 ﻭﺇﻥ ﺃﻇﻠﻢ ﺍﻟﻈﻠﻢ، ﻭﺃﻋﻈﻢ ﺍﻹﺛﻢ : ﺍﻹﺷﺮﺍﻙ ﺑﺎﻟﻠﻪ، ﻗﺎﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﺗﻌﺎﻟﻰ : ﴿ ﺇِﻥَّ ﺍﻟﺸِّﺮْﻙَ ﻟَﻈُﻠْﻢٌ ﻋَﻈِﻴﻢٌ ﴾ ‏[ ﻟﻘﻤﺎﻥ : 13 ‏] ،
ሽርክ የበደሎች ሁሉ ትልቁ በደል ነው።
👌﴿ ﺇِﻧَّﻪُ ﻣَﻦْ ﻳُﺸْﺮِﻙْ ﺑِﺎﻟﻠَّﻪِ ﻓَﻘَﺪْ ﺣَﺮَّﻡَ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﺍﻟْﺠَﻨَّﺔَ ﻭَﻣَﺄْﻭَﺍﻩُ ﺍﻟﻨَّﺎﺭُ ﻭَﻣَﺎ ﻟِﻠﻈَّﺎﻟِﻤِﻴﻦَ ﻣِﻦْ ﺃَﻧْﺼَﺎﺭٍ ﴾ ‏[ ﺍﻟﻤﺎﺋﺪﺓ : 72 ‏]
እንደዚሁም የአጋሪያኖችን እጣ ፈንታ ሲናገር እንድህ ይላል"እነሆ በአላህ ያጋራ ጀነትን በእሱ ላይ ሀራም አድርጎበታል መኖሪያውም ጀሀነም ነው፡ለነዚያ ለሙሽሪኮች ረዳት የላቸውም"።
ﻭﻗﺎﻝ ﺳﺒﺤﺎﻧﻪ : ﴿ ﺇِﻥَّ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻟَﺎ ﻳَﻐْﻔِﺮُ ﺃَﻥْ ﻳُﺸْﺮَﻙَ ﺑِﻪِ ﻭَﻳَﻐْﻔِﺮُ ﻣَﺎ ﺩُﻭﻥَ ﺫَﻟِﻚَ ﻟِﻤَﻦْ ﻳَﺸَﺎﺀُ ﻭَﻣَﻦْ ﻳُﺸْﺮِﻙْ ﺑِﺎﻟﻠَّﻪِ ﻓَﻘَﺪْ ﺿَﻞَّ ﺿَﻠَﺎﻟًﺎ ﺑَﻌِﻴﺪًﺍ ﴾ ‏[ ﺍﻟﻨﺴﺎﺀ 116 : ‏] ،
አሏህ ሱብሀነሁ ወተአላ አጋሪወችን ፈፅሞ እንደማይምር እንድህ ይላል"አሏህ በእርሱ የሚያጋራበትን ፈፅሞ አይምርም ከዚያ (ከሽርክ)ያነሱ ወንጀሎችን ለፈቀደው አካል መሀርታ ያደርጋል፡፡፡፡
ﻭﻟﻘﺪ ﺣﺬﺭ ﺍﻟﻠﻪ ﻛﻞ ﻧﺒﻲ ﻣﻦ ﺍﻟﺸﺮﻙ ﻛﻤﺎ ﻗﺎﻝ ﺳﺒﺤﺎﻧﻪ : ﴿ ﻭَﻟَﻘَﺪْ ﺃُﻭﺣِﻲَ ﺇِﻟَﻴْﻚَ ﻭَﺇِﻟَﻰ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻣِﻦْ ﻗَﺒْﻠِﻚَ ﻟَﺌِﻦْ ﺃَﺷْﺮَﻛْﺖَ ﻟَﻴَﺤْﺒَﻄَﻦَّ ﻋَﻤَﻠُﻚَ ﻭَﻟَﺘَﻜُﻮﻧَﻦَّ ﻣِﻦَ ﺍﻟْﺨَﺎﺳِﺮِﻳﻦَ * ﺑَﻞِ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻓَﺎﻋْﺒُﺪْ ﻭَﻛُﻦْ ﻣِﻦَ ﺍﻟﺸَّﺎﻛِﺮِﻳﻦَ ﴾ ‏[ ﺍﻟﺰﻣﺮ : 65 ، 66 ‏] .
ሁሉንም ነብያቶች አለይሂሙሰላቱ ወሰላም ከሽርክ አሰጠንቅቋቸዋል።
አሏሁ ሱብሀነሁ ወተአላ እንድህ ሲል ይናገራል"በእርግጥ ወደ አንተና ካንተ በፊት ወደነበሩት ነብያቶች ብታጋራ ስራህ በሙሉ ይበላሽ ነበር የሚል ኢንፎርሜሽን ተላልፎላቸዋል።
ﻭﺃﺧﺒﺮ ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻥ ﺃﻛﺜﺮ ﻣﻦ ﻳﺆﻣﻦ ﺑﻪ ﻳﻘﻊ ﻓﻲ ﺍﻟﺸﺮﻙ ﻓﻘﺎﻝ : ﴿ ﻭَﻣَﺎ ﻳُﺆْﻣِﻦُ ﺃَﻛْﺜَﺮُﻫُﻢْ ﺑِﺎﻟﻠَّﻪِ ﺇِﻟَّﺎ ﻭَﻫُﻢْ ﻣُﺸْﺮِﻛُﻮﻥَ ﴾،
አሏሁ ሱብሀነሁ ወተአላ አብዝሀኛው በእሱ የሚያምን አካል ሽርክ ላይ እንደሚወድቅ እንድህ ሲል ተናገር"  ብዙሀኖች በአሏህ አያምኑም እያጋሩ ቢሆኑ እንጅ"
ﻭﻫﺬﻩ ﺑﻌﺾ ﺻﻮﺭ ﺍﻟﺸﺮﻙ ﺍﻟﻤﻨﺘﺸﺮﺓ ﺑﻴﻦ ﺍﻟﻤﺴﻠﻤﻴﻦ :
እነኝህ የሚከተሉት በሙስሊሞች መካከል የተሰራጩ የተበተኑ የሽርክ አይነቶች ናቸው።

በአሏህ ፈቃድ እያንዳንዱ የሽርክ አይነት ከነ መረጃው እንመለከታለን።

ክፍል 2 ይቀጥላል....
ቻናሉ➥ t.me/mustefa_Apologetics

┎┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┒
  ይቀጥላል  ከ100 ላይክ ቡሀላ
┖┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┚

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.