የያዕቆብ ኹለት ምዕራፎች
የዐዲስ ኪዳን ጸሓፍት በእምነትም ኾነ በተፈጥሮ ምክንያት የሚመጣን መከራ አስመልክቶ በቂ የኾነ ነገረ መለኮታዊ አስተንትኖ አስፍረውልናል። በተለይ በቤተ ክርስቲያን ላይ በደረሰው መከራ ምክንያት ወደ ተለያዩ የሮም ግዛቶች ተበትነው አሁንም ከመከራ ዳፋ ሊያመልጡ ላልቻሉት አይሁድ አማኞች መጋቢያዊ መልእክቱን የጻፈው ጻድቁ ያዕቆብ (James the Just)፣ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባቸው እንደ ሙሉ ደስታ እንዲቈጥሩት ሲያሳስብ እንመለከታለን። እንዲህ እንዲያስቡ የሚለምናቸውም፣ የሚደርስባቸው ፈተና ምሉእና ፍጹም እንዲሆኑ ወይም ክርስቶስን ወደ መምሰል እንዲያድጉ ስለሚረዳቸው መሆኑን ጨምሮ ያስረዳል።
እንዲህ የሚለው የያዕቆብ መልእክት ከሌሎች ሐዋርያት ትምህርት ጋራ ስምሙ ነው። ጳውሎስም ይሁን ጴጥሮስ ስለዚሁ ጕዳይ ሲጽፉ፣ የመከራ የመጨረሻ ዓላማ የክርስቶስን መልክ መጐናጸፍ መሆኑን አጽንኦት በመስጠት ቅዱሳን እንዲታገሡና ደስ እንዲሰኙ ያሳስባሉ። ያዕቆብ ግን ከዚህ በተጨማሪ አንድ የሚያነሣው ጕዳይ አለ፤ በምዕራፍ አንድ ውስጥ መከራን እንዲታገሡ ካሳሰበ በኋላ፣ በምዕራፍ ዐምስት ውስጥ ግን፣ በአማኞቹ ላይ የግፍ ጽዋ ለሚያፈሱ ባለ ጠጎች የእግዚአብሔር ፍርድ እንደ ተቃረበ ያመላክታል።
ያዕቆብ እንደ ብሉይ ነቢያት፣ በአማኞች ላይ የሚደርሰው የመከራ ሒሳብ በእግዚአብሔር ሳይወራረድ እንደማይቀር ይናገራል። በርግጥ ቅዱሳን እምነታቸው እየተሠራበት ይሆናል፤ እግዚአብሔርም እየተጠቀመበት ይሆናል፤ መከራ አድራሺዎቹ ላይ ግን የእግዚአብሔር ቍጣ መገለጡ አይቀሬ ነው። ይህን የያዕቆብን ሐሳብ ሳነብ፣ ቤተ ክርስቲያን አንድም በአማኞች ላይ ስለሚደርሰው መከራ ጤነኛ የኾነ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ለምዕመኗ መስጠት እንዳለባት የመልእክቱ የመጀመሪያው ምዕራፍ ሲያመላክተኝ፣ ዐምስተኛው ምዕራፍ ደግሞ፣ መከራ አድራሺዎቹ ላይ የእግዚአብሔር ፍርድ እንደሚገለጥ ነቢያዊ ድምፅ ማሰማት እንዳለባት እረዳለሁ።
የሚያሳዝነው እውነታ ግን፣ በዚህ በምንኖርበት ዘመን ኹለቱም አለመሆናቸው ነው። ቤተ ክርስቲያን በምድራችን ላይ እንደ አሸን ስለ ፈላው መከራ ነገረ መለኮታዊ አስተንትኖ በመስጠት የምዕመናንን እምነት ከመፈራረስ ስትጠብቅ አትታይም፤ ያለ አግባብ በሕዝቡ ላይ የመከራን ውሃ የሚግቱት አካላት ላይም እግዚአብሔር ፍርዱን እንደሚገልጥ ነቢያዊ ድምፅዋን አታሰማም፤ መጋቢያዊም ኾነ ነቢያዊ ሚናዋ የሳሳ ይመስላል። ያዕቆብ መጋቢያዊውንም ነቢያዊውንም ሚና ምሳሌያዊ በኾነ መንገድ አስቀምጦልናል፤ ፈለጉን እየተከተልን ያለን ምን ያኽሎቻችን እንሆን?
✍fanuel brhane
@nazrawi_tube