#በስምህ_ታምኛለው
በስምህ ታምኛለሁ እን ዳትተወኝ
ለሚያሳድደኝ ጠላት ለሞት አትስጠኝ
ፀጥታዬ ነህ ጌታ ሰላም ዕረፍቴ
ጉዞዬን አንተ አቅናልኝ ቅደም ከፊቴ
አዝ
በለስም ባታፈራ ዘይትም ባይኖር
የህሊና ሰላም አለኝ ካንተ ጋር ስኖር
በአባቶቼ በረከት የ ባረከኝ
የእስራኤል ታዳጊያቸው ክበርልኝ
ዘላለም ተመስገን ከፍ በልልኝ
አዝ
የፈተናዬ መውጫ መልሴ ነህ
አንተ ጨለማውን አሻግረኝ እልፍኙን ከፍተህ
ስታፅናናኝ ኖሬአለሁ ለብዙ ዘመን
ተገፍቶ መች ይወድቃል በአንተ የሚታመን
አይሞትም ይኖራል በአንተ የሚታመን
አዝ
ይቅርታና ምህረትህ እነሱ ይምሩኝ
ወጥመድና እንቅፋቱ እንዳያደክሙኝ
በጽድቅህ ሀሴት ላድርግ በአንተ ልበርታ
መተከዝ ማልቀስ ይብቃኝ አፅናናኝ ጌታ
ተነግሮ አያልቅም የአምላኬ ውለታ
በስምህ ታምኛለሁ እን ዳትተወኝ
ለሚያሳድደኝ ጠላት ለሞት አትስጠኝ
ፀጥታዬ ነህ ጌታ ሰላም ዕረፍቴ
ጉዞዬን አንተ አቅናልኝ ቅደም ከፊቴ
አዝ
በለስም ባታፈራ ዘይትም ባይኖር
የህሊና ሰላም አለኝ ካንተ ጋር ስኖር
በአባቶቼ በረከት የ ባረከኝ
የእስራኤል ታዳጊያቸው ክበርልኝ
ዘላለም ተመስገን ከፍ በልልኝ
አዝ
የፈተናዬ መውጫ መልሴ ነህ
አንተ ጨለማውን አሻግረኝ እልፍኙን ከፍተህ
ስታፅናናኝ ኖሬአለሁ ለብዙ ዘመን
ተገፍቶ መች ይወድቃል በአንተ የሚታመን
አይሞትም ይኖራል በአንተ የሚታመን
አዝ
ይቅርታና ምህረትህ እነሱ ይምሩኝ
ወጥመድና እንቅፋቱ እንዳያደክሙኝ
በጽድቅህ ሀሴት ላድርግ በአንተ ልበርታ
መተከዝ ማልቀስ ይብቃኝ አፅናናኝ ጌታ
ተነግሮ አያልቅም የአምላኬ ውለታ
እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇
@ney_ney_emye_maryam
#ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏
🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊