ደብተር ማርክ
°°°°°°°°°°°°°
የሮቤል ደብተር.....
ቲቸር አየት አየት ሲያደርጓት ከሌላው የተለየ ጽሁፍ አዩ፡
" ልደታ ሲደርስ ለ ሚፍጣ የሚከፈል
ግማሽ ሊትር ዘይት
አንድ ኪሎ ጨው
ሰንደል
እጣን
ከሰል......."
" በጀርባው ምንድነው የጻፍከው? "
" እማዬ አስቤዛ..........".......አቋረጡት
" ጭራሽ!..ምስርስ ትለቅምበታለች? "
" ልገንጥለው? "
" መንጋጋህን ይገንጥለው የሰማዩ! "....ቀና ብለው፡
" በዱቤ የበቀልክ! " አሉት፡ በብስጭት
ቲቸር ከበደ፡ በጣም አጭርና ቀጭን ነበሩ!
በቅጽል ስማቸው " ስሙኒ " ይባላሉ
( እሳቸውም ያውቃሉ! )
የያሬድ ተራ ደረሰ። ያሬድ ክላስ በመቅጣት ትልቅ አርአያችን ነው!
" ይሄን ደብተር ለባለሱቁ መልስ ".....ቲቸር ከበደ
" ለምን ቲቸር? "
" ሰው ይማርበታ!......መጻፍ የሚችል ሞልቷል! "
ደብተሩን የምትይዝለት ኤልሳ ናት
( ሸንኮራ እየተከፈላት! )
***
እኔና ታመነ ለሰሎሜ የፍቅር ደብዳቤ ጽፈን ነበር ያኔ!
( ወግ ወጉን ይዘን! )
ታመነ አፍቅሯት ነበር። ሰሎሜ የሃብታም ልጅ ናት።
ምሳ የሚቋጠርላት በሶቢላ ያለው ምስር ነዋ!
አሁን ሳስታውስ፡ ከግቢው ተማሪ የፊት ቅባት የምትቀባው እሷ ብቻ ነበረች
እኛማ ደመናማዎች ነበርን!
ከዘጠኝ ሰአት እስከ ማታ በዝግ ስብሰባ ጽፈን ጨረስን!
( አስራ ሶስት መስመር! )
ዳሩ ምን ያደርጋል፡ ታሜ ደብተሩ ውስጥ አስቀምጦት ረሳው!
የደብተር ማርክ ሲሞላ፡ ቸኩሎ ሰጠ! ለካ ደብዳቤው
ውስጡ ነበር!
ቲቸር ከቤ ( ስሙኒ ) ደብተሩን ሲያገላብጡ፡ ወረቀቷን አገኙና ማንበብ ጀመሩ። አቤት የደነገጥነው!
መጥፎነቱ ደግሞ ደብዳቤው እሳቸውንም ይጠቅሳል!
በጥቂቱ ሲነበብ፡
" ሰሎምዬ! እኔ በጣም ነው የምወድሽ!....ባለፈው ላናግርሽ ስል ያ "ስሙኒ" እየተንከባለለ ገባ።
ለምንድነው መልስ የማትሰጪኝ?
ሳምንት የስሙኒን ክላስ እንቅጣውና ሻሾ ጮርናቄ ልጋብዝሽ? በናትሽ!?...ያ ኩሩሩ መቼም ታማ ቀረች ካሉት ያምናል!....
በቀደም ሲገርፍሽ አይቼው ተናደድኩ! የዶሮ ኩስ ፈልጌ
ወንበሩ ላይ የለቀለኩበት እኔ ነኝ....ፍቅርሻ ነው ኩሱን ያፋለገኝ!....መሳሳት ባንቺ ተጀመረንዴ?!
Enough ሲነበብ "ኢኖጋህ" ሳይሆን "ኢነፍ" ነው እሺ!?
መልስሽን እጠብቃለሁ!......."
በጦር የተወጋ የልብ ስእል
ከማይነበብ ፊርማ ጋር!
..........ፍቅርሻ እንደለመድኩት በር በሯን አየሁ! ......
Credit:-
Fikre Z Bhere Ethiopia