እነዚህ የፍጹም ሕይወት፣ የአንድነት፣ የሰላም፣ የዕርቅና የፍቅር ምሳሌዎችም ምልክቶችም ሲሆኑ በውስጣቸውም እኛ በኅብረት በፍቅር ኾነን ፈጣሪያችንን ማመስገን እንደሚገባን የሚያስገነዝበን መልካም አርአያና ትምህርት ያለበት መልእክት አለው፡፡
ምክንያቱም የሰላም ምልክት ኅብረት በመኾኑ፣ የሁሉም ኃጢኣት መደምሰሻ፣ የመንግሥተ ሰማያት መውረሻ፣ የጽድቅ ማሰሪያ ደግሞ እውነተኛ ፍቅር ነውና፡፡
ጌታችን በቤተ ልሔም በተወለደ ጊዜ በመላእክትና በሰው ምን ምስጋና ተደረገ?ጌታችን በብተ ልሔም በተወለደ ጊዜ ሰዎችና መላእክት በአንድ ኾነው ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብእ፣ ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰው በጎ ፈቃዱ በማለት እግዚአብሔርን አመስግነዋል፡፡
መሠረታዊ ትርጉሙም አምላክ ለሆነ ሥጋ ከሥላሴ ጋር በአንድነት ምስጋና ይገባዋል፡፡ እግዚአብሔር ለሰው ግእዛኑን ወይም ነጻነቱን ይሰጠው ዘንድ በምድር ዕርቅ ተወጠነ ወይም ተጀመረ በዓለም ሰላም ሠፈነ፣ በፈጣሪና በፍጡር መካከል፣ በሰውና በመላእክት፣ በፍጥረት ሁሉ ፍጹም ሕይወት፣ አንድነት ሰላም፣ ዕርቅና ፍቅር ሆነ ማለት ነው፡፡ ሉቃ. ፪÷፲፬፡፡
ጌታችን በቤተ ልሔም በተወለደ ጊዜ ሰማያት ተከፍተዋል፣ መላእክት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ ፈጣሪን እያመሰገኑ ከሰማይ ጌታችን ወደ ተወለደባት ወደ ቤተ ልሔም ጌታቸውን ለማመስገን ሲወርዱ ከምድርም ወደ ሰማይ ሲወጡ ይታዩ ስለነበር ትንቢት በተፈጸመበት መላእክት ባመሰገኑበት ቀን ወለድኩህ ይላላ ዋናው የትርጉሙ ምሥጢር፡፡
አዎ ጌታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በመወለዱ በመላእክትና በልሳነ ሰብእ (በሰው አንደበት) በፍጥረቱም ሁሉ እግዚአብሔር አብ፣ እግዚአብሔር ወልድ፣ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ተብሎ ተመሰገነ፣ አብ ወላዲ፣ ወለድ ተወላዲ፣ መንፈስ ቅዱስ ሠራፂ እንደሆነም በፍጥረቱ በግልፅ ታወቀ፡፡
የእግዚአብሔር አንድነትና ሦስትነት ምንም እንኳ ቀድሞሞ በነቢያት አንደበት ሲነገር፣ በብሉያት ቅዱሳት መጻሕፍትም ሲመሠጠር እንደነበር ቢታመንም በልደቱ ምሥጢር ደግሞ በሥራ ተገለጠ፡፡ ጎልቶ ታየ ማለት ነው፡፡
ጌታችን ቤተ ልሔም በተባለው ቦታ በተወለደ ጊዜ ሰዎችና መላእክት በአንድ ኾነው ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብእ እያሉ እግዚአብሔርን ማመስገናቸው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የፍጹም ሕይወት፣ የአንድነት፣ የላም፣ የዕርቅና የፍቅር አምላክ መሆኑን ያመለክታል፡፡ እኛም ያንን መሠረት በማድረግ ዛሬም ሁልጊዜም ጌታችንን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እናመሰግነዋለን፡፡
ከበዓሉ ረድኤት በረከት ያሳትፈን!አሜን!🙏
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
•➢ ሼር // SHARE
☑️ሼር ይደረግ
#share & join
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻
@ort_mezmurr@ort_mezmurr🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻