ቅዱስ ሄሬኔዎስ እና የሰዉ እድገት ክፍል 1
ስለ ቅዱሱ በጥቂቱ፦
ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ሰማዕትና ጸረ መናፍቃን የነበረውን የኤዶሙን (ሊዮን-ፈረንሳይ) ጳጳስ፡ ቅዱስ ሄሬኔዎስን (Irenaeus) ነሐሴ 17 ታስበዋለች፡፡
በሃይማኖተ አበዉ ዘሄሬኔዎስ ስሙን፤ "የሐዋርያት ደቀ መዝሙርራቸዉ ተከታያቸዉ ኤዶም በምትባል አገር ኤጲስ ቆጶስነት የተሾመ፤ ሄሬኔዎስ እንዲህ አለ"፤በማለት ስራዉን የሚያነሳ የሃይማኖት ምስክርነቱን ይጽፋል።
"[120–220ዓ.ም.]ቅዱስ ሄሬኔዎስ የጥንቷን ቤተ ክርስቲያን ያስተዋውቀናል። ክርስቲያናዊ የልዑካን ቡድኖች ለአንድ ምዕተ ዓመት ያህል ወደ ለመለሙባት ወደ Rhone ወንዝ ዳርቻዎች እንሻገራለን። በመርቅልስ እና በሰርመኔስ መካከል ንቁ የንግድ ልውውጥ የነበረ ይመስላል፤ አቡሊካርዮስም(ፖሊካርፐስ) ገና በጥንቱ ዘመን ፎጢኖስን ወንጌልን እንዲሰብክ ወደ ሴልቲክ ጎል ልኮት ነበር። እሱም መንበረ ጵጵስናውን በሊዮን ካደላደለ በኋላ፣ሄሬኔዎስ በአቡሊካርዮስ ሥር አብሮት የተማረ የጋራ ደቀ መዝሙር እንደመሆኑ መጠን፣ በቅስና ማዕረግ ተቀላቀለው።
እዚያም “ደጉ አውሬሊየስ” ተብሎ በተሳሳተ መንገድ በሚጠራው ማርከስ አውሬሊየስ ዘመን (በ177 ዓ.ም.)፣ “የሊዮን እና የ Vienne ሰማዕታት” የተባሉትን ታሪክ የማይረሳቸው ያደረገው ያ አስከፊ ስደት ተቀሰቀሰ። ሄሬኔዎስ እየተስፋፋ የመጣውንና እንደ ወረርሽኝ የታየውን የክህደት ትምህርት ለመቃወም የሚያስገነዝቡ የቅሬታ ደብዳቤዎችን ይዞ ወደ ሮም የተላከው በዚሁ ስደት ወቅት ነበር፤ ከሰማዕትነታቸው ምስክርነት ጋር ተያይዞ ለቀረበው የሰማዕታቱ መከራና ስቃይ መግለጫ ታሪክም ዋነኛው ጸሐፊ እርሱ ሳይሆን አይቀርም።
ነገር ግን የሮም ኤጲስቆጶስ የነበረው Eleutherus የሞንታኒዝምን (Montanist) የክህደት ትምህርት ሲደግፍ በማየቱ ሄሬኔዎስ በእጅጉ አዝኖና ተከፍቶ ነበር፤ እዚያው Rome ውስጥም ከ አቡሊካርዮስ ትምህርት ቤት የሚያውቀውንና በኋላ ግን የቫለንቲኒያንን (Valentinian) የክህደት ትምህርት የተቀበለውን አንድ የድሮ ጓደኛውን አገኘው።
ይህም ጉብኝት ፣ እንደ አንበጣ መንጋ መጥተው የወንጌልን አዝመራ ለመበላት (ለማጥፋት) የተነሱትን የክህደት ትምህርቶች ለመመከት ሄኤኔዎስ ዕድሜ ልኩን የታገለበትን ተጋድሎ እንዳስገኘልን አንጠራጠርም። ...የልዮን ቤተ ክርስቲያንም በሮም ኤጲስቆጶስ ዘንድ የታዩትን የክህደት ዝንባሌዎች ነቅፋለች። "
ወደ ልዮን በተመለሰ ጊዜ፣ ክቡር ፎጢኖስ ቅዱስ ሕይወቱን በሰማዕትነት ፍጻሜ እንዳጠናቀቀ ተረዳ፤ በዚህም የተነሳ ሄሬኔዎስ የእርሱ ተተኪ (ሊቀ ጳጳስ) ሆነ።
ከዚህ በመቀጠል እንደ ሰደደ እሳት ሙሉ የቤተክርስቲያንን አስተምህሮ እና ሕይወት ሊየጠፋ የደረሰውን የቫለንቲኒያንን (Valentinian) እና የግኖስቲክ( Gnostic) የኑፋቄ ትምህርቶች ከመሰረታቸዉ ነቅሎ ለመጣል የሚገባዉን ዝግጅት ፈጽሞ፤
ለቅድስት ቤተክርስቲያን እምነት እና ሕይወት ምስክር የሚሆኑ በዋናነት የሚታቁ 2 ድንቅ መጽሐፍትን አበርክቷል።
1. መድፍነ መናፍቃን (Against Heresies)
2.Demonstration of the Apostolic Preaching
ስለ ደራሲዉ ከብዙ በጥቂቱ ይህን ካልን ይበቃል።
የሰዉ እድገትወደ ጉዳያችን ስንመለስ ስለ ነገረ ሰብ ነገረ ክርስቶሳዊነት አብዝቶ የጻፈ የሞገተ የቤተ ክርስቲያን ዕንቁ ልጇ ነዉ። በ ነገረ ሰብ ጉዳይ ከ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ ቀጥሎ ተጠቃሽ አባት ነዉ።
በጥቂቱም ቢሆን እነሆ፦
The work of God is the fashioning of man'
(AH5.15.2) “የእግዚአብሔር ሥራ ሰውን መፍጠር (መቅረጽ) ነው።”
ይህ የሄሬኔዎስ የአስተሳሰብ መዋቅር መሠረታዊ ማዕቀፍ ነው። ይህ እውነታ የእርሱን ሥነ-መለኮት በሁሉም ደረጃዎች ይገልጸዋል።
እግዚአብሔር አምላክ በማይመረመር ጥበቡ ራሱን ፍጹም ሰው አድርጎ ገልጧል፤ እግዚአብሔር ባሕርይ ሕይወትና የሕይወት መገኛ (ፈጣሪ) ቢሆንም፣ እርሱ በፈጠረው በተፈጥሮ ባሕርይ—ማለትም በሥጋዊና በሕዋሳዊ (በተባዕትና በአንስት) ማንነት—ውስጥ የሚኖረው ግን ፍጡር የሆነው ሰው ነው። ይህ ሲባል የፈጣሪን ፍጹም ነፃነት (ሉዓላዊነት) እና በራሱ ሙሉ መሆንን ጥያቄ ውስጥ ለመጣል አይደለም፤ እርሱ የሰውን ዘር ፈልጎት (አስፈልጎት) ሳይሆን፣ ከቸርነቱ ፍሬ እንዲያጣጥምና ከባሕርይ ክብሩ (ከመለኮታዊ ጸጋው) ተሳታፊ እንዲሆን ለማድረግ በበጎነቱ ፈጠረው እንጂ። ይህ በቀላሉ እግዚአብሔር ራሱ በገለጠው መለኮታዊ ዕቅድ (ምስጢረ ሥጋዌ) መሠረት የተገለጠውን እውነት መመስከር ነው። እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጡ የሰው ልጅ እውነተኛ ማንነት መገለጫም ጭምር ነው፤ ስለሆነም፣ በእውነት ሰው መሆን ማለት እግዚአብሔር ራሱን የገለጠበትን ያንን መልክ መምሰል ማለት ነው።
ታዲያ፣ በዚህ መለኮታዊ ሥርዓት (economy) ውስጥ የታቀፈው ሰው፣ እንዴት ነው እውነተኛ ሰው መሆን—አምላክ መሆን (መለኮታዊ ባሕርይን መሳተፍ)—የሚችለው? መልሱ በዚያው ተመሳሳይ መዋቅር ውስጥ ይገኛል፦
'God makes, man is made'
(AH4.11.2)” እግዚአብሔር ያበጃል (ይቀርጻል)፤ ሰው ግን ይበጃል (ይቀረጻል)።”
በ AH 4. 38-9 ላይ ሄሬኔዎስ እግዚአብሔር የፈጠራቸውን ማንነት—ማለትም
“'men subject to passions' (homines passionum capaces, AH 4. 38. 4)
“መከራን፣ ውሱንነትንና ተለዋዋጭነትን ሊቀበል የሚችል ደካማ ፍጡር”
” መሆናቸው ለመቀበል አምቢ በማለት ውለታ ቢስነታቸውን የሚያሳዩትን፣ ነገር ግን ገና ከመነሻው እንደ እግዚአብሔር መሆን የሚፈልጉትን
gnostics ይሞግታል። እንዲህ ዓይነቶቹ ሰዎች በአንድ በኩል እግዚአብሔር ራሱን እንደ ሰው የገለጠበትን መለኮታዊ አሠራር (divine economy) ካለማወቅ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በፈጣሪያቸው ላይ ካላቸው የእምነት ማነስ የተነሳ ስሕተት ላይ ይወድቃሉ። እነርሱ መሆን ለሚፈልጉት ማንነት የራሳቸውን plan ያዘጋጃሉ ።
የምስራቅ ኦርቶዶክስ
Metropolitan Anthony of Sourozh ይህን ሁኔታችንን ተመልክተው
God can save the sinner you are, but not the saint you pretend to be"
እግዚአብሔር ድኅነትን የሚሰጠው ላለህበት እውነተኛ ኃጢአተኝነትህ እንጂ በግብዝነት ለለበስከው ሐሰተኛ ምናባዊ ጻድቅነትህ አይደለም።
በማለት ይዘልፋሉ።
..... ይቀጥላል
በወንድም ኒፎን