1. 📝 RB ላይፕዚግ
ላይፕዚግ ግብ ጠባቂውን ኦርጃን ኒላንድ ከሴቪያ በነጻ ዝውውር አስፈርመዋል።
ተጫዋቹ እስከ 2028 የሚቆይ ውል የፈረመ ሲሆን 1ቁጥር ማልያ ይለብሳል። 🧤🔴
2. 📝 ስታድ ሬንስ
ስታድ ሬንስ የመሀል ተከላካዩን ቻርሊ ክሬስዌል ከቱሉዝ በውሰት አስፈርመዋል።
የውሰቱ ክፍያ 2.5 ሚሊዮን ዩሮ ሲሆን፣ በሚቀጥለው ክረምት በቋሚነት ለመግዛት 22.5 ሚሊዮን ዩሮ የግዴታ ግዢ ስምምነት ውሉ ላይ አለው። 📝
3. 📝 ኢፕስዊች ታውን
ኢፕስዊች ታውን ፍሎረንቲኖ ሉዊስን ከበርንሌይ በ5 ዓመት ውል አስፈርሟል።
ዝውውሩ የመጀመሪያ 16 ሚሊዮን ፓውንድ እና ተጨማሪ 3 ሚሊዮን ፓውንድ ጉርሻዎችን ያካትታል። 🤝
4. 🚨🇪🇸 አዲስ የላሊጋ የዳኝነት ደንቦች (ለ 2026/27 የውድድር ዘመን)
ቪኤአር (VAR): ለሁለተኛ ቢጫ ካርድ፣ በስህተት ለታዩ ቀይ ካርዶች እና በስህተት ለተሰጡ የማዕዘን ምቶች ጣልቃ መግባት ይችላል። 🖥️
የተቀየሩ ተጫዋቾች: ከሜዳ የሚወጡ ተጫዋቾች በ10 ሰከንድ ውስጥ መውጣት አለባቸው፤ ካልሆነ የሚገባው ተጫዋች 60 ሰከንድ መጠበቅ አለበት። ⏰
ህክምና: በህክምና ምክንያት ከሜዳ የሚወጡ ተጫዋቾች ከመመለሳቸው በፊት ቢያንስ ለአንድ ደቂቃ ከሜዳ መቆየት ይኖርባቸዋል። 🤕
የግብ ጠባቂዎች ህክምና: ግብ ጠባቂ ያለ ጥፋት ጉዳት ሳይደርስበት ጨዋታውን በህክምና ምክንያት ካቆመ፣ አንድ የቡድን አጋሩ ለአንድ ደቂቃ ከሜዳ መውጣት አለበት። 🧤
የእጅ ውርወራ: የእጅ ውርወራዎች ጥብቅ የአምስት ሰከንድ ቆጠራ ይደረግባቸዋል ። ⏱️
የዳኛ ማብራሪያ: ዳኞች ከቪኤአር ምርመራ በኋላ የመጨረሻ ውሳኔያቸውን ለተመልካቾች በድምጽ ያስረዳሉ እንዲሁም ግልጽ ያደርጋሉ። 🗣️
👉
@perfectsportet