"BE THE CHANGE YOU WANT TO SEE IN THE WORLD"....
"
ብርቅዬ አባባል አይደል? ብዙ ማውራት እንችላለን። ከነዚህ ብዙ ነጥቦች እስቲ ስለአንድ ነገር እናውራ።
"
"
በዚህች ታላቅ በነበረች፤ አሁን ላይ ከውስጥም ከውጭም በደረሰባት ቡጥበጣ፣ ግፍገፊ ምክንያት፤ ከ5ሺህ አመት በላይ ታሪክ ያላት፤ አሁን ግን ተቦጥቡጣ ተቦጥቡጣ የ 18አመት ሸንቃጣ ችክ የምትመስለዋ ሀገራችን "ኢትዮጲያ" ላይ በእኛ በልጆቿ የሚዘወተሩ አባባሎች አሉ።
....."እዚህች ሀገር ላይ የህግ የበላይነት የለም"!!
......" ሁሉም ያው ነው። ህዝቡም፣ መንግስቱም፣ ሀገሪቱም ያው ናቸው። ያበላን ጣት ነካሽ።" አዎ ልክ ነው። ከታሪክ ባንማርም ብዙ አይተናል። የሆነው ሆኖ፣ የተበደለው ተበድሎ፣ የበደለው ተፀፅቶ ተቀጥቶ አምልጦ ... ምናምን ምናምን አልፏል። ይሄ ለኛ የሚጠቅመው አንድ ነገር ቢኖር ስህተታችንን እንዳንደግም ማድረጉ ላይ ብቻ ነው። ከዛ ውጪ ዘመን ያሻገረው በዳይነት እና ተበዳይነት ትርፉ የምፅዐት ቀንን ማፋጠን ብቻ ነው።
ስለዚህ የኔ ጥያቄ፤ አክሱምን ላነፁ፣ ላሊበላን ለገነቡ፣ አድዋ ላይ በዠግንነት ለተዋጉ፣ ጣሊያንን ለ5አመት ሰላም አሳጥተው ለመከቱ፣ ኤርትራን ከኢትዮጲያ ጋር መልሶ አንድ ለማድረግ ለለፉ አብዮተኞች አይደለም። የኔ ጥያቄ የዚህ ትውልድ አካል ነን ለባዮች ነው።
?እስቲ በዚህች ሀገር ላይ አየኖራቹ ለሀገር ሸክም ከመሆን ውጪ ለሀገሪቷ የፈየዳቹት ነገር ምንድነው???????
....ከአንድ የግቢ ተማሪ ጋር እያወራው መምረጥ ስለሚፈልገው (ፊልድ) ጠየቁት። ተማሪውም" የህግ ተማሪ መሆን ነው የምፈልገው" የሚል መልስ ነበር የሰጠኝ። ጥሩ ነው አልኩት። ከዚያም ለምን ህግ መማር እንደሚፈልግ አክዬ ጠየኩት። " ከሀገር ለመውጣት አሪፍ እድል ስለሚከፍትልኝ ነው" ነበር መልሱ።......
ቆይ ቆይ ልቡ ከሀገር ለመውጣት የሚመኝ ህግ አስከባሪ ይዛ ፣ ለኔ ከማለት ወጥቶ ለኛ የሚል ትውልድ ካጣች፣ ሁሉም አማራሪ ከሆነ የዚህች ሀገር ተስፋ ምንድነው።? ወገን ያጣነው እኮ ከዳር ቆሞ ችግር ጠቋሚ አይደለም። ከመሀል ገብቶ ችግር ለመፍታት የሚሞክር እንጂ።
አዎ በሆነ መንገድ በsystemu ምክንያት የሆነ ነገር ሆነሃል። አዎ ለሆዳቸው ባደሩ አጋሰሶች ምክንያት ማግኘት የሚገባህን ተነጥቀሀል። ግን ደግሞ አስተውል የደረሰብህን ያደረሱብህ ሰዎችም አንድ ጊዜ ላይ በአንተ ላይ የደረሰው ደርሶባቿል። ሀገሪቷን የሞላው እኮ አኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ባይ ነው።
.... ዐፄ ቴዎድሮስ የመቅደላን ጦርነት እንደተሸነፉ እርግጥ በሆነበት በዛች ቅፅበት መኳንንቱ " ጦርነቱን ማሸነፍ ባንችል ቢያንስ ለዚህ ጦርነት ምክንያት የሆኑትን ነጮቹን እንግደላቸው"ሲሉ ዐፄውን መከሩት። ዐፄውም " አንድ ላርግህ ብዬ ያንገላታውት ሳያንስ ለውጪ ጥቃት አሳልፌ አልሰጠውም" ነበር ያሉት። ኋላም ሀገሬው እንዲህ ሲል ለዐፄው ገጠመለት...
"ከመቅደላ አፋፍ ጩኸት በረከተ፣
የሴቱን አናውቅም ወንድ አንድ ሞተ።"...
እስቲ ሁላችንም "ሴት" ከተባሉት " አድር ባዮች፣ በትንሽ ነገር ተስፋ ቆራጮች፣ ምን አገባኝ ባዮች፣ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ባዮች" ከመሆን ወጥተን "ከራሳችን ጥቅም የሰው ጥቅም የምናሰቀድም፣ ትንሽ ተነካሁ ብሎ የሀገር ሰውን ሁሉ ምን አገባኝ ብሎ ከመተው የምንቆጠብ፣ በእኛ የደረሰው በሌላ እንዳይደርስ የምንከላከል የሀገር መከታ ሆነን" በታሪክ ባይሆን በአንድ ሰው ልብ ውስጥ ኩሩ፣ ዠግና "ወንድ" ለመባል እንጣር።
ደግሞ በሀገራቹ ተስፋ ከመቁረጣችሁ በፊት አንድ ነገር አስታውሱ፤ ሀገሪቷ እንዲህ ውጥንቅጧ የወጣው በየቀኑ እንደናንተ ተስፋ በሚቆርጡ ሰዎች ምክንያት ነው።
"ስለዚህ እንዲለወጥ የምትፈልጉት ነገር ካለ ለውጡን ከራሳችሁ ዠምሩ"።።።።
ፀሐፊ : የሱስራ
""""""NO ROOM FOR RACISM"""""
ሀሳብ ካላቹ leave comment 👇👇
@poemers