❤️RIDE (™️) Drivers Update


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


ይህ ቻናል ከራይድ ሀሳብ መለዋወጫ ግሩፕ (RIDE group) በተጨማሪ ኦፊሻል የአሰራር መረጃ ሲኖር ማሰራጫ መንገድ ነው

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


⭐️የተሻሻለውን Terms and Condition ይመለከታል:- አንዳንድ አባላት የDriver Level 1 ክፍያን በተመለከተ ጥያቄ እንዳላቸውና በፊት በገቡት በወረቀት ውል ላይ እንደሌለ ገልፀው ማብራሪያ ጠይቀውናል:: ሆኖም በበፊቱ የወረቀት ውል አንቀፅ 5 ንኡስ 4 ላይ እንደተጠቀሰው አሽርከርካሪው በወር ጠቅላላ 30 ስራዎች በታች ከሆነ የሰራው 250 ብር የአገልግሎት ክፍያ እንደሚከፍል ተጠቅሷል:: ይህንን ስምምነት ድርጅታችን በራሱ ፍላጎት ላለፉት 7 ዓመታት ሳያስፈፅም የቀረ ቢሆንም - ተሻሽሎ በonline በተተካው Terms and Conditions ላይ ከ30 ስራዎች በታች የሚሰሩ አካላት 200 ብር እንዲከፍሉ የተወሰነ መሆኑን አውቀው አብረውን እንዲያድጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን:: ይህንን ለማስፈፀም በ October ወር በበቂ ሁኔታ ግንዛቤ ማስጨበጫ የተሰራ ሲሆን ለወደፊት ይህንን አሰራር በበቂ ሁኔታ ተግብረው እንዲሰሩ እየጠየቅን- ከዚህ ውጭ የሚደረግ ማንኛውም ውሳኔ Driver app ውስጥ በተገለፀው Terms and Conditions ብቻ የሚፈታ መሆኑን እናሳውቃለን:: ስለቤተሰባዊ ቀናነትዎ እናመሰግናለን


✨የቴክኒካል ችግሩን እየቀረፍን ነው:- ውድ የራይድ ቤተሰብ- በባንኮ integration ላይ የገጠበንን ችግር እየፈተና ስለሆነ በትዕግስት እንዲጠብቁን በአክብሮት እንጠይቃለን::


⭐️ማስታወሻ:- ውድ የራይድ ቤተሰብ- 1. ሌላ መደበኛ ስራ ኖሮት RIDE ጋር በPart time የሚሰሩ ከሆነ - 2. የምሽት ሰራተኛ ከሆኑ - 3. በRIDE Plus ከ30 በላይ ስራዎች ከሰሩ- Driver Level 1 ቢሆኑም አስተያየት አድርገን 200 ብር ተመላሽ የምናደርግ ሲሆን ከዚህ ውጭ በአደጋ ምክንያት ስራ ላይ ካልሆኑ ወይም መኪናው በማንኛውም ምክንያት እርስዎ ጋር ካልሆነ በፍጥነት እንዲያሳውቁን በአክብሮት እንጠይቃለን:: ከRIDE ጋር ወደፊት!


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
✨ብዙ ስራ የመስራት ሚስጥሩ ይሄ ነው:: በተጨማሪም የስልክዎን setting አስተካክለው ለራይድ ብቻ ይጠቀሙ::


✨አዲሱን የግብር አዋጅ ለማስፈፀም የወጣው ረቂቅ ደንብ ምን ይላል? የRIDE አሽከርካሪዎች ከደንበኞች የሚሰበስቡት TOT ወይም VAT በድርጅታችን በኩል እንዲሰበሰብ የሚደነግግ ሲሆን - እነዚህ አባላት ያለሲስተም ከመንገድ ለሚሰሯቸው ስራዎች የTOT ወይም የVAT ሪሲት አሳትመው በጉዞ መጨረሻ ለተሳፋሪው መስጠት እንዳለባቸው ያሳያል:: ይህንንም እንግልት ለመቀነስ የRIDE Plus Street Pickup ፕላትፎርማችንን በበቂ ሁኔታ ያዘጋጀን መሆናችንን እየገለፅን- የግብር ሰብሳቢነት ፈቃድ በፅሁፍ ሲሰጠን ወድያው የምንተግብር ይሆናል::


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
🎙️ ስለ Driver Level ከአባላት ለተነሳ ጥያቄ እዚህ ቪድዮ ላይ በበቂ ሁኔታ አብራርተናል:: ሬከርዱን ያድምጡ


✨በስራዎ ውጤታማ እንዲሆኑ ይህንን መረጃ ይመልከቱ


📺Driver Level እንዴት እንደሚሰራ ለማወቅ ይህንን ይመልከቱ https://youtu.be/_xPMtAklanM?si=qyxrKrbANcsrvEj-


❤️RIDE (™️) Drivers Update dan repost
💥ጠቃሚ መረጃ:- እባክዎ ቆም ብለው የRIDEን Terms and Conditions (የስምምነት መግለጫ) ከDriver አፕዎ ውስጥ ይመልከቱ:: Terms and Conditions ገፅ ለማግኘት Driver App ውስጥ Menu > Settings > Get in touch > Get Legal Information > Terms and conditions ውስጥ ይግቡ


💥ስልክዎን በቀላሉ ከዝርፊያ እንታደግልዎ! የስልክዎ ኔትወርክ እንደበራ ዝርፊያ ቢፈፀምብዎ- ዘራፊዎች የስልክዎን ዳታ ወይም ስልክዎን ያለፓስወርድ ማጥፋት እንዳይችሉ እንደሚደረግ ያውቃሉ? ስልክዎም ከRIDE System ጋር የተገናኘ ስለሆነ በቀላሉ ያለበትን ማወቅ እንችላለን:: ስልክዎ ያለፓስወርድ እንዳይጠፋ ለማድረግ ይህንን ቪድዮ ይመልከቱ https://vm.tiktok.com/ZMhCRLW8S/


💥አዲስ መመርያ:- ውድ የRIDE ቤተሰብ- በRIDE Plus Street Pickup ማስጀመርያ ከ30 በላይ ስራዎችን ከሰሩና የRIDE Driver Levelዎ 1 ላይ ከሆነ የሚቆረጥብዎን Subscription Fee በ2 ቀን ውስጥ እንደምንመልስ በአክብሮት እናሳውቃለን:: መልካም ስራ


🚨የአፋልጉኝ ጥሪ! White Toyota Yaris ታርጋ 3AA-B14395 በትላንትናው እለት 3 ከመንገድ ላይ ያለሲስተም የተጫኑ ግለሰቦች አስገድደው መኪናውን ይዘው ተሰውረዋል:: ይህንን መኪና በአካባቢያችሁ ካያችሁ በ8294/8812 ወድያው እንድታመለክቱልን በትህትና እንጠይቃለን




Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish


🎙️የቴክኒካል ሴሚናራችን ካመለጠዎ እነሆ ሬከርዱ:: ስራ በአግባቡ እንዲደርስዎ የተሰጠውን መግለጫ አንድ በአንድ ተከትለው የስልክዎን setting ያስተካክሉ::


🎙️የቴክኒካል እገዛ ሴሚናራችንን አሁኑኑ በዚህ ሊንክ ይቀላቀሉ:: Live የስልክዎን setting እንዴት እንደሚስተካከል እናሳይዎታለን https://t.me/rideFamilyDriver?livestream=673764e478644c2fb2


🎙️የዛሬ Online Technical Seminar:- ውድ የራይድ ቤተሰብ ዛሬ ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ የስልክዎን ቴክኒካል ሴቲንግ ለማስተካከል በቴሌግራም ቻናላችን በቀጥታ Seminar ስለምናካሄድ እንዲቀላቀሉን ጥሪ እናቀርባለን:: በዚህ ሴሚናር ላይ የሚስተካከሉ ነገሮችን አንድ በአንድ የምናሳይ ሲሆን ከአባላት የሚመጡ የቴክኒካል ጥያቄዎችንም Live እንመልሳለን::


👏RIDE ለረዥም ስራዎች ተመጣጣኝ ክፍያ ያስገኛል! በባዶ እንዳይመለሱም መመለሻ ስራ በBack to Back Feature ይሰጥዎታል:: ከRIDE ጋር ወደፊት!


⭐️✨👏 BRAVO! የፍጥነት ሬከርዳችንን አሻሽለናል:: ይህንን አመርቂ ውጤት ለማስቀጠል ጥሪ እንደገባልዎ በፍጥነት ደንበኛ ጋር ደውለው በቦታው ይድረሱ:: እንበርታ!


🎙️Online Technical Seminar:- ውድ የራይድ ቤተሰብ መጭው ረቡዕ Oct 30 ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ የስልክዎን ቴክኒካል ሴቲንግ ለማስተካከል በቴሌግራም ቻናላችን በቀጥታ Seminar ስለምናካሄድ እንዲቀላቀሉን ጥሪ እናቀርባለን:: በዚህ ሴሚናር ላይ የሚስተካከሉ ነገሮችን አንድ በአንድ የምናሳይ ሲሆን ከአባላት የሚመጡ የቴክኒካል ጥያቄዎችንም እንመልሳለን::

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.