ታላቁዋ እና ጀግናዋ እንስት
😱😱አስገራሚ_ታሪክ !😱😱
👉👉👉ሠይዱና ኻሊድ ኢብኑል ወሊድ ከሮማውያን ጋር በተደረገው ውጊያ የሙሰሊሞችን ሰልፍ በማሰተካከል ላይ
ሳሉ አንድ ሙሉ ሰውነቱን እና ፊቱን በአረጓዴ ጨርቅ የተሸፈነ ተዋጊ ከሰልፉ
ፊት ለፊት ተመለከቱ። የሙስሊሞችንም ሰልፍ እየመራ የሮማውያኑን ጦር
ከፍተኛ ጉዳት ያደርስበት ጀመር። ከሙስሊሞች ጦር ውሰጥም የተሸፋፈነውን
ሰው የሚያውቅ አንድም ስው አልተገኝም። በውጊያው መሃልም ከሙጃሂድ
ወንድሞቹ ዓይን ተሰወረ። ውጊያው ሲቀዛቀዝም ከሮማውያኑ መሃል በደም
የተነከረ ሰይፉን ይዞ ወጣ። ራፊዕ ኢብኑ ዑመይር (ረድየሏሁ ዐንህ) በወቅቱ
ከሙስሊሞች ጦር ጋር ነበር። ክሰተቱን እንዲህ ሲል ይተርካል። "በውጊያ
ውስጥ እያለን የተሸፋፈነውን ሰው ጀብዱ ስንመለከት የጦር መሪያችን ኻሊድ
ኢብኑ ወሊድ (ረድየሏሁ ዐንህ) ፊቱን ሸፍኖ ገብቶ ይሆናል ብለን ገምተን ነበር። ነገር ግን
ኻሊድ ኢብኑ ወሊድን (ረድየሏሁ ዐንህ) ተመለከትነው። ለኻሊድም "ይህ ከፊት
ለፊትህ ሆኖ አሰገራሚ የጀግና ውጊያ የሚዋጋው ሰው ማን ነው?" ብለን
ጠየቅነው። ኻሊድም "እኔም እንደናንተ ላውቀው አልቻልኩም" አለን።
ውጊያውም እንደ አዲስ ሊጀመር ነው። ኻሊድም "የሙስሊም ጦር ሆይ
በጀግንነት ተዋጉ፣ ከእምነታቹህ ላይ የጠላትን ወረራ ተከላከሉ" በማለት
ሙስሊሙን አበረታታ። የተሸፋፈነውም ሙጃሂድ ጦሩን ከፊት ለፊት ሆኖ
መምራቱን እንደቀጠለ ነው። ውጊያውም ከተጀመረ ቡኋላ ወደ ጠላት ስብስብ
ገሰግሶ ሰለሚገባ ሙጃሂድ ወንድሞቹ ሰልፋቸው ውስጥ አይመለከቱትም
ነበር ጦርነቱም ሲጠናቀቅ ልብሶቹ በደም የተነከሩ ሆነው ወደ ሙስሊሞች
ካምፕ መጣ። ኻሊድ እና ሙጃሂዶቹም "ለአላህ ሰትል ፊትህን ግለጥና
አሳየን" ብለው ተናዘዙት። እርሱ ግን ለንግግራቸው ቦታ ሳይሰጥ ጀርባውን
ሰጥቷቸው ጉዞውን ቀጠለ። ከስውዬው የሚታየው ሁኔታ ጉዳዩ አላህ ዘንድ
እንዲታወቅለት የፈለገ ይመሰላል። ሙስሊም ተዋጊዎችም "አንተ የተሸፋፈንክ
ሰው ሆይ! የጦር መሪህ እያዘዘህ ነው፣ ፊትህን አሳየን" እያሉ ከየአቅጣጫው
መጮህ ጀመሩ። ኻሊድም የሰውዬውን እምቢተኝነት በተመለከተ ጊዜ ከፊት
ለፊቱ ቀደመው።
"ወዮልህ! በተግባርህ የስዎችን ትኩረት ሳብክ" በማለት ጠየቀው። ጀግናው
ሙጃሂድም የጥያቄው መደጋገም ሲበዛበት "እስካሁን መልስ ያልሰጠሁህ
ከአንተ ፊት ድምፄን ለማውጣት ሐያእ (ሀፍረት) ይዞኝ ነው።እኔ ከሙስሊም
ሴቶች ውስጥ አንዷ ነኝ" ስትል በእንስታዊ ድምፅ መለሰችለት።
ኻሊድም በጉዳዩ ተደንቆ "እሺ አላህ ይባርክሽ ሰምሽን ንገሪኝ" ሲል ጠየቃት።
ኸውለት ቢንት አዝወር ነኝ" ብላ መንገዷን ቀጠለች።
አጀብ ጀግንነት እህቶቻችንን ጀሊሉ እንደ ኸዉለት ጀግኖች ያድርግልን።
ለተጨማሪ እና ተከታታይ ደርሶች እንዲሁም ለተከታታይ ኪታቦች ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFbH7Yl6aZER5VgxJA