ነገረ መፃህፍት 📚📗📓📖


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


እናነባለን ያነበብነውን እናጋራለን በመፃህፍት ስለመፃህፍት እናወራለን
✅በዚህ ቻናል ድንቃድንቅ መረጃዎች፣ ጣፋጭ ግጥሞች፣ መጣጥፍና አጫጭር ልቦለዶች፣ የረዥም ልቦለድ ትረካ እና ወጎች ግጥሞች(በድምፅ)፣ ባጠቃላይ ጥበብ እና ጥበብ ነክ ነገሮች ይቀርቡበታል። ይቀላቀሉ!
👇👇👇👇
https://t.me/seido27hurelhub
To contact me @seido11

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri




ታኅሳስ በታሪክ ውስጥ
ታኀሳስ 4 1953 ዓ.ም. በአገራችን ተሞክረው ከከሸፉት መፈንቅለ መንግሥቶች ዋነኛው ተሞከረበት ቀን ነው፡፡ የመፈንቅለ መንግሥቱ ዋና ተዋናዮች ወንድማማቾቹ ጄኔራል መንግሥቱ ነዋይ የክብር ዘበኛ አዛዥና ገርማሜ ነዋይ እንዲሁም የፀጥታው ዘርፍ ኃላፊ ሌ/ኮሎኔል ወርቅነህ ገበየሁ ናቸው፡፡ መፈንቅለ መንግሥቱ በዚህ ቀን ለመደረግ ይወሰን እንጂ በነዚህ ሰዎች አእምሮ ለብዙ ጊዜያት ሲብላላ ቆይቷል፡፡ ከእነሱ በተጨማሪም አብዛኛው የተማረውና ወጣቱ ክፍል የለውጥ ፈላጊ ስለነበር በየትኛውም መንገድ ለውጥ እንዲመጣ ይመኛል፡፡ ታኅሳስ 4 የጃንሆይን ወደ ብራዚል ለጉብኝት መሄድን ተከትሎ መፈንቅለ መንግሥቱን ለማድረግ ተወሰነ፡፡ የታሪኩ አመጣጥ ረጅምና ተደጋግሞም በሚዲያ ስለተነገረ ለዛሬ ለማሳየት የፈለኩት ለምን ከሸፈ የሚለውን ነው፡፡
በኔ ሐሳብ መፈንቅለ መንግሥቱ የከሸፈበት አንዱ ምክንያት ጠንሳሾቹ ከራሳቸው ውጪ ማንንም ማመን ስላልቻሉ ሊያግዟቸው የሚችሉ ሰዎችን ስላላማከሩ በቂ ድጋፍ አላገኙም፡፡ ይህ የሆነው ከነሱ ብቃት ማነስ ብቻ ሳይሆን የጃንሆይ አገዛዝ ከፋፍሎ በመግዛት ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ማንም ማንንም እንደዚህ የከበደ ነገር ለመንገር አያምንም፡፡ ሁለተኛው ምክንያት ክብር ዘበኛው ከሌላው ሠራዊት የተነጠለ ስለነበር በክብር ዘበኛው የሚቀርብን ማንኛውንም ሐሳብ ሌላው ሠራዊት በቀላሉ አይቀበልም፡፡ ሦስተኛውና ዋነኛው አብዛኛው የአገሪቱ ሕዝብ የሚቀበላት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መፈንቅለ መንግሥቱን ባለመደገፏና ይንንም የሚገልፅ በራሪ ወረቀት በአውሮፕላን በመበተኑ ምክንያት ለመደገፍ የመጣው የክብር ዘበኛ ሠራዊት አባላት ጭምር ሸሹ፡፡ መፍንቅለ መንግሥቱም በቁጥጥር ስር ውሎ ንጉሠ ነገሥቱ ወደ መናገሻ ከተማቸው ተመለሱ፡፡ የመፈንቅለ መንግሥቱ ተዋናዮችም ገርማሜና ሌ/ኮሎኔል ወርቅነህ ራሳቸውን ሲያጠፉ ጄኔራል መንግሥቱ ተይዘው ሞት ተፈረደባቸው፡፡ የታሪኩን ዝርዝር ለማወቅ የሚፈልግ ሰው የአቶ ብርሃኑ አስረስን “ማን ይናገር የነበረ… የታኅሳስ ግርግርና መዘዙ” የሚለውን መጽሐፍ እንዲያነብ እመክራለሁ፡፡
ይህ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ በታሪካችን ትልቅ ምዕራፍ የከፈተ ነው፡፡ ምክንያቱም ንጉሠ ነገሥቱ ከሥልጣን መወገድ እንደሚችሉ ለሕዝቡ ያሳየ ነው፡፡ ለንጉሠ ነገሥቱ መንግሥትም ቢሆን ከፍተኛ ባለሥልጣኖቻቸውን ያሳጣ ሆኗል፡፡ ከተገደሉት ውስጥ አንዱ አቶ መኮንን ሀብተወልድ ሲሆኑ ለጃንሆይ ታማኝ ሆነው ከጸሀፌ ትዕዛዝ ወልደጊዮርጊስ ወልደዮሐንስ ጋር ለረጅም አመታት አገልግለዋል፡፡ በጸሐፌ ትዕዛዙ መነሳት አንድ እግሩን አጥቶ ሲያነክስ የነበረው የአፄ ኃይለሥላሴ መንግሥት በአቶ መኮንን ሞት ሌላኛውን እግሩን አጣ፡፡ ከዚያ በኋላ ተቀያሪ እግሮች አግኝቶ መቆም ሳይችል እንደዳኸ ለውድቀት በቃ፡፡ ይህ መፈንቅለ መንግሥት ተሳክቶ ቢሆን ለአገራችንም ሆነ ለንጉሣዊው ቤተሰብ ከ1966ቱ ለውጥ የተሻለ ውጤት ያስገኝ ነበር ብዬ አስባለሁ። እናንተስ ምን ይመስላችኋል?








ከእለታት አንድ ቀን በሀገረ አሜሪካ እንዲህ ሆነ ።
..............
ዝግጅቱና የአቀባበል ዝግጅቱ ምን መምሰል እንዳለበት ፡ ጊዜ ወስዶ የመከረው የአሜሪካ መንግስት ታላቅ ዝግጅቱን አጠናቆ የእንግዳውን አሜሪካን መድረስ መጠበቅ ጀመረ ።
.....
በእለቱም የዋሽንግተንና የአካባቢው ህዝብ እኝህን አሜሪካንን ሊጎበኙ የሚመጡትን ንጉስ በአደባባይ ወጥቶ እንዲቀበል ግብዣ ተደረገለት ።
......
ኦክቶበር 1 - 1963 የሀገረ ኢትዮጵያ ንጉሰ ፡ ቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ ዋሽንግተን ሲደርሱ ፡ በወቅቱ የአሜሪካን ፕሬዝደንት JF ኬኔዲ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው
.....
ከዛም ንጉሱ ከአሜሪካን ፕሬዝደንት ጋር በመሆን በግልፅ መኪና ሆነው ወደ ነጩ ቤተመንግስት ሲጓዙ ፡ በተጓዙበት ጎዳና ላይ ህዝቡ ግራና ቀኝ በመቆም በዚህ መልኩ እያጨበጨበ ተቀበላቸው ።
....
እና ....
በወቅቱ በአሜሪካን ብቻ ሳይሆን በመላው አለም የነበረን ክብር ይህን ይመስል እንደነበር ሲታሰብ ያስቆጫል
@wasihune


ጀብደኛው፣ በአደንዛዥ ዕፅ የናወዘው፣ አምባጏሮ ወዳዱ ታይሰን አሁን የለም:: ያሁኑ ማይክ ታይሰን ሰዎች ሁሉ አንድ ዓይነት ነገር እንዲያስቡ ሊያስገድድ የሚፈልገውን ድባብ ያሸነፈ ጥልቅ አሳቢ፤ ራሱን የገዛ ታላቅ ሰብእና ነው:: የዛሬውን ግጥሚያም ሆነ ሌሎች ፈተናዎች የጀግንነት ማስመስከሪያ እንዳልሆኑ ደጋግሞ ገልፆዋል:: ትግል ሁሉ ከራስ ጋር ነው፤ ድልም ያለመስካሪ የራስን ግብ መምታት ነው ይላል:: እናም ግቡ የሚችለውን ሁሉ አድርጎ: የራሱ ምርጥ አቋም ላይ ሆኖ መወዳደር ነበር:: በ58 ዓመቱ ያንን ማድረግ ችሏል:: Can you be the best version of yourself? CAN YOU!? #miketyson


ይህ እየሆነ ያለው ኬንያ ወይም ሌላ የአፍሪካ ሀገር ውስጥ ቢሆን አይገርምም ግን ይህ ከምርጫ ጋር ተያይዞ ብጥብጥ ሊነሳ ይችላል የሚል ስጋት የተፈጠረው የ200 አመት የዴሞክራሲ ልምምድ አላት በሚባለው አሜሪካ መሆኑ ነው የሚያስገርመው. .
በዚህም መሰረት
የአሜሪካን የመረጃ ደህንነት ቢሮ ፡ ከሰአታት በኋላ በሚጠናቀቀው የአሜሪካን ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ትራምፕ ከተሸነፈ ፡ በደጋፊዎቹ በሚነሳ ብጥብጥ ፡ አሜሪካን ቀውጢ ልትሆን ትችላለች የሚል ስጋት ውስጥ በመግባቱ ፡ የነጩ ቤተመንግስት ዙሪያ ፡ በረጃጅም ብረቶች ሁለተኛ አጥር ተሰርቶለታል. . እንዲሁም በካፒቶል ሂል እና በካማላ ሃሪስ መኖሪያ ቤት ዙሪያ ተመሳሳይ ሌላ አጥር ተሰርቷል ።
የትራምፕ ደጋፊዎች መስታወቶችን ሰብረው እንዳይገቡም የካፒቶል ሂል ህንጻ መስኮቶች በወፍራም ዝርግ እንጨት ( ፋይዚት በምንለው ) ታሽገዋል ። .......
በአንዳንድ ቦታዎች ማለፍ አይቻልም በሚል ምልክት ተቀምጧል ። የፀጥታ ጥበቃው በተለየ መልኩ ተጠናክሯል ።
....


እንደጓደኞቹ ውድ ..አዲስና ቅንጡ መኪና ሊነዳ አይደለም ፡ ይህችን አሁን የሚይዛትን Vauxhall Corsa መኪና እንኳን ከአንዲት በእድሜ የገፉ አዛውንት ላይ ነው የገዛት ።
......
በሚያስገርም ሁኔታ. . ፌስቡክ ኢንስታግራምም ሆነ ፡ ምንም አይነት የሶሻል ሚዲያ የማይጠቀመው የዛሬው ባላንዶር አሸናፊ ሮድሪ. . ፕሮፌሽናል ሆኖ በሳምንት 120 ሺህ ፓውንድ እየተከፈለው ፡ እንደጓደኞቹ ቤት ተከራይቶ ከመኖር ይልቅ ፡ ማንኛውም ተማሪ የሚያልፍበትን ኖርማል ህይወት ለመኖር ሲል ዶርም ውስጥ እየተኛ ነበር የኮሌጅ ትምህርቱን የጨረሰው ።
.....
በየጊዜው ደም ለመለገስ ሲል በሰውነቱ ላይ ንቅሳት እንዳይኖር የሚፈልገው ይህ ተጫዋች ፡ ደሙን ብቻ ሳይሆን ፡ ከሚያገኘው ገቢ የተወሰነውን በመደበኝነት ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች በመስጠት ይታወቃል ።
....
በመልካም እና ትሁት ባህሪው የሚመሰገነው የማንቸስተር ሲቲው ኮከብ ሮድሪ በጉዳት ላይ ባለበት ወቅት ፡ ባገኘው በዛሬው የባላንዶር ሽልማት ዙሪያ ይገባዋል አይገባውም የሚለው ውዝግብም ቀጥሏል ።
...

@wasihune


"ተስፋ መቀነት ነው መቸም
የሰው ልብ አይችለው የለም!"
ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድሕን


ቃ ላ ት | Words dan repost
ቃ ላ ት - ፩፪ | 12.pdf
22.6Mb
እነሆ

ቃላት 12 | Words | ኪናዊ መጽሔት

ልዩ እትም

https://t.me/Words2014
.
.
ለአስተያየታችሁ :‑
words5102@gmail.com


መዲና ዲጂታል መጽሔት/ Medina Digital Magazine dan repost
መዲና ቅጽ1 ቁጥር4.pdf
10.0Mb
መዲና ፬ እነሆ

https://t.me/Medinamagazine

በተጨማሪም በፌስቡክ እና ኢንስታግራም ቤተሰብ ይሁኑን!

https://www.facebook.com/profile.php?id=61556884335163&mibextid=ZbWKwL

https://www.instagram.com/medinadigitalmegazine?igsh=ejZqbjN3OXF0dHJj

ለአስተያየትዎ

medinadigitalmagazine@gmail.com

ሰኔ 2016 ዓ.ም


ነብስህ በሰላም ትረፍ ታላቁ ሰው 😢


ስለ አንዳንድ ካምፓኒዎችና ሰራተኞቻቸውን እንዴት እንደሚንከባከቡ ስናነብ አግኝተን ያስገረመን የጉግል ነገር .
...
የአለማችን ግዙፉ የግል ኩባንያ ጉግል ከ34 ሺህ በላይ ሰራተኞች አሉት ::

እና እድል እውቀት እና አጋጣሚ ቀንቶት የዚህ ካምፓኒ ሰራተኛ የሆነ አንድ ሰው በህይወት ሳለ አሪፍ የሚባል ደሞዝ ፡ እና ብዙ ጥቅማ ጥቅም የሚያገኝ ሲሆን ፡ በሆነ ምክንያት በሞት ሲለይ ደግሞ . ቤተሰቡ ችግር ላይ መውደቅ የለበትም ፡ ሚስቱ መቸገር የለባትም በሚል ለባለቤቱ .. ሌላ ሰው እስካላገባች ድረስ ለአስር አመታት ድረስ ፡ ሟች ባለቤቷ ሲከፈለው የነበረውን ደሞዝ ግማሽ በየወሩ ይከፈላታል ።
በህይወት እያለ የገዛቸውን አክስዮኖች ካሉም በስሟ ይዛወራል ።

ሰውየው ልጆች ካሉት ደግሞ 19 አመት እስኪሞላቸው በየወሩ 1 ሺህ ዶላር ደሞዝ የሚያገኙ ሲሆን ልጆቹ የሙሉ ጊዜ ተማሪ ከሆኑ ደግሞ ፡ ይህ የ1ሺህ ዶላር ወርሃዊ የደሞዝ ክፍያ እስከ 23 አመት እስኪሆናቸው ድረስ ይቀጥላል ።

ባጠቃላይ የጉግል ሰራተኛ አደለም እያለ ፡ በሞት ሲለይም አይቸገርም ።

@wasihune


መፅሀፍትን አሳትሞ ለአንባቢያን የማቅረብ ስራ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መሆኑ ተገለፀ

ከዚህ ቀደም በዓመት እስከ አምስት መፀሀፍት የማሳተም ስራ ሲሰሩ የነበሩ አሳታሚ ድርጅቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሙሉ ለሙሉ የህትመት ስራ ማቆማቸውን ሰምቻለሁ በማለት ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል።

የወረቀት ዋጋ መወደድን ተከትሎ አሳታሚዎች መፀሀፍቶቻቸውን እንዳያሳትሙ አድርጓቸዋል የተባለ ሲሆን በዚህ ሁሉ ችግር ታትሞ ለገበያ ቢቀርብም አንባቢ እንደማይኖረው በአንድ የመፀሀፍ ኤግዚቢሽን ላይ የተሳተፉ ደራሲያንን እና መፀሀፍ ሻጮች መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

ይህ የሆነበት ምክንያት መፀሀፍቱ የሚሸጡበት ዋጋ ውድ በመሆኑ ነው ሲባል መፀሀፍ ማሳተም አስቸጋሪ እንደሆነና ይህ ችግር በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ ነባር ደራሲያንን ብቻ ሳይሆን ወደ ዘርፉ የሚመጡ ጀማሪ ደራሲያንንም ያሳጣል ተብሏል።

ፀሀፊያን እና ደራሲያን መንግስት ከቀረጥ ነፃ ወረቀት እንዲገባ እና በህትመት ስራዎች ላይ እንዲሳተፍ ምክረ ሀሳብ የተሰጠ ሲሆን በተጨማሪም ባለሀብቶች የህትመት ኢንዱስትሪው ላይ እና የወረቀት ማምረት ስራ ላይ ሊሳተፉ ይገባልም ነው የተባለው።

ፎቶ፦ ፋይል

@TikvahethMagazine


#ዓርብ 4 ኪሎ ዋሊያ መጻሕፍት ቤት ይመረቃል

ኑ እና እየዳንን እንሒድ




ማርክ ዙከርበርግ የናጠጠ ቢሊየነር ነው። ሚስቱን ለማስደሰት ማንኛውንም በአለም ላይ ውድ የሆነ ቁስ ሊገዛላት ይችላል—ጌጣጌጦች፣ ቤት፣ መኪና፣ አውሮፕላን፣ የመዝናኛ መርከብ yacht ወዘተ። አንድ ደሴት ወይም ትንሽ ሀገር የሚገዛ ገንዘብ ያለው ሰው ነው። ገንዘብ ሊገዛው የሚችለውን ነገር ሁሉ በስጦታ ሊሰጣት ይችላል።

ማርክ ግን ገንዘብ የሚገዛውን ትቶ ገንዘብ የማይገዛውን ሰጣት። ምን ይሆን ገንዘብ የማይገዛው?! የማርክ ሚስት ፕሪሲላ ቻን ትባላለች። በትውልዷ ቻይናዊ ናት። በላቧ ሰርታ የምታድር ሜዲካል ዶክተር ነች። ደግሞ በባህሪዋም ገንዘብ የሚያስደንቃት፣ ግድ የሚሰጣት ሴት አይደለችም።

ታዲያ ለዚህች ሴት ማርክ ምን ይስጣት? ማርክ ለሚስቱ ሳይነግራት የቋንቋ ትምህርት ቤት ተመዘገበ። ለአመታት ማንዳሪን አጠና። በነገራችን ላይ ማንዳሪን ለመማር በጣም ከባድ ቋንቋ ነው። አይደለም በሁለተኛ እና ሶስተኛ ቋንቋነት አፈ ለፈቱበትም ዳገት ነው። በተለይ ጽሁፉ።

አንዴ ስለ ማንዳሪን ሳነብ ከ48 ሺ በላይ ካራክተርስ አሉት ይላል። መሰረታዊ ጽሁፍ ለማወቅ ቢያንስ 3ሺ ካራክተር ማወቅ ይገባል። ምእራባውያን የለመዱት 26 የላቲን ፊደል ነው። ማንዳሪንን ተዉትና የኛ ቋንቋ 231 ፊደላት እንዳለው ሲያውቁ ልባቸው በድንጋጤ ቀጥ ነው የምትለው። አማርኛ ራሱ ለመማር ቀላል ቋንቋ አይደለም። ማንዳሪን የበለጠ ከባድ ነው። ብዙ ትጋት ይጠይቃል።

ማርክ ራሱ ቋንቋውን በደንብ ለመካን ብዙ አመት ወስዶበታል። ያውም እሱ ከፍተኛ የአእምሮ ብቃት ስላለው ነው እንጂ ቋንቋው የሊማሊሞ ዳገት ነው። ታዲያ ማርክ በማንዳሪን ሲካን ለሚስቱ በመጀመሪያ እንዲህ ነበር ያላት፦

"我爱汝"

ትርጉሙ "አፈቅርሻለሁ" ነው።

ከዚህ የሚበልጥ ምን ስጦታ አለ?! በገንዘብ የማይተመን ዋጋ የማይወጣለት ውድ ስጦታ።

ፍቅርና ቋንቋ። ቋንቋና ፍቅር። ፍቅር በቋንቋ ይገለጻል። እስኪ አንዳችን የሌሎቻችንን ቋንቋ በፍቅር እንማር። ፍቅራችንን እንገላለጽ። ቋንቋዎቻችን የፍቅር ድልድይ እንጂ የልዩነት ግድግዳ አይሁኑብን።

እወዳችኋለሁ!❤❤
Anii sin jaalladha!❤❤
የፍቅረኪ እየ!❤❤

@ Tewodros shiwangizaw


አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ ለ16ኛ ጊዜ የመጻሕፍት አውደርዕይ ትናንት ጀምሮ እያካሄደ ነው። ለሳምንት በሚቆየው በዚህ አውደርዕይ ሥፍራ ሌሎች ተጨማሪ ክንውኖች አሉ። ዛሬ ሚያዝያ 8 ቀን ከሰዓት  በኋላ ዓለማየሁ ገላጋይ ስለ አዲሱ መጽሐፉ ማእበል ጠሪ ወፍና ስለሌሎቹም ሥራዎቹ፣ ፋሲካ ሙሉ ደግሞ ሰለ ያልተገራ ፈረስ መጽሐፏይነግሩናል። ወዳጆቼን ሁሉ በክብር ጋብዣችኋለሁ።



20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.