ስዕለ አድኅኖ


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር!!!!!!

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


ዝማሬ ቲዩብ zemare tube dan repost
​​ጾም እስከ ስንት ሰዓት ነው?
ክፍል 1


እንኳን በሰላም አደረሳችሁ! ?
የቅድስቲቱ ቤተክርስቲያን ሥርዓቱ በልኬት እና በምክንያት የታጀበ ነው። ጾምን ስንመለከት አብዛኞቻችን በተለምዶ ሰዓት ሳንጠብቅ (እስከ 3፣ 6፣ 7፣ 9፣ 11 ሰዓታት እያልን) እንጾማለን እንጂ የአዋጅ አጽዋማት የተወሰነ የተገደበ ሰዓት አላቸው።

ፍትሐ ነገሥታችን “ሕማማት እስከ 12 ሰዓት ይጹሟቸው፥ ሌሎቹን አጽዋማት በዓለ ልደት እና ጥምቀት ረቡዕ እና ዐርብ የሚውሉባቸው ካልሆኑ በቀር እስከ 9 ሰዓት ይጹሙ” (ፍት.ነገ አን 15፥565-566) ብሏል።

የአጽዋማትን ዝርዝር ካስቀመጠ በኋላም በዚሁ  አንቀጽ ቁጥር 572 ላይ ደግሞ “በእነዚህ በታዘዙት ጾሞች ከቀኑ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ይጹሙ፣ ... ከዚህ አብልጦ  የጾመ ግን ዋጋው ይበዛለታል፣ ከጥሉላት ምግቦች መታቀብ ካልሆነ በቀር እሑድና ቅዳሜ ግን አይጹሙ” ብሎ ወስኗል።

ዐቢይ ጾም ሁዳዴ፣ ጾመ ዐርብዓ ግን ይለያል። “በዐቢይ ጾም መጀመሪያ  ሱባኤ ፀሐይ እስኪገባ ይጹሙ፣  ሌሎቹን ሳምንታት እስከ  11 ሰዓት ይጹሙ፥ በሰሙነ ሕማማት ግን ኮከብ እስኪወጣ ይጹሙ” ብለዋል። (ፍት.ነገ.አን 15፥595)።

ፍትሐ ነገሥት ቁጥር 578 ላይ ደግሞ “(የሰሙነ ሕማማትን) ዓርብንና ቅዳሜን ግን ሁለቱንም በአንድነት ይጹሟቸው፣ የሚችል እስከ ሌሊት ዶሮ ጩኸት ድረስ ምንም ምን አይቅመስባቸው፣ ሁለቱን በአንድነት መጾም የማይቻለው ግን ቅዳሜን ይጹም” ተብሎ ህግ ተሠርቷል።
├───────────────
├ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
├───────────────
•✥•🍁  @Z_AbelMakbeb  🍁•✥•
              @Z_AbelMakbeb  
  •✥•🍁 @Z_AbelMakbeb 🍁•✥•


#ማረኝ_መመኪያዬ

ማረኝ ማረኝ ማረኝ መመኪያዬ
አርጅቻለሁ እኔ(በኃጥያት ጎስቁዬ )/2/
       አዝ-----
ከፊቴ ናትና ኃጥያቴ ሁል ጊዜ
ተውጫለሁ እኔስ(በሀዘን በትካዜ)/2/
በፊትህ ክፋትን አድርጌያለሁ እኔ
ምንም ጽድቅ አልሠራው(በሕይወት ዘመኔ)/2/
       አዝ-----
ከፊትህ መቅበዝበዝ መሠደድ ፈለኩኝ
ኃጥያት ከሁዋላዬ(እያሳደደችኝ)/2/
ወዴት አሄዳለው መሸሸጊያም የለኝ
ምህረት መጠጊያ(ዋሻ ካልሆነችኝ)/2/
       አዝ-----
ከፊቴ ናትና ኃጥያቴ ሁል ጊዜ
ተውጫለሁ እኔስ(በሃዘን በትካዜ)/2/
በፊትህ ክፋትን አድርጊያለሁ እኔ
ምንም ጽድቅ አልሠራው(በሕይወት ዘመኔ)/2/
       አዝ-----
የተሰባበረው አጥንቴ እንዲጠገን
በምህረት እና(በቸርነት ዳሠኝ)/2/
የቀና መንፈስን አድስ በልቤ ውስጥ
ነፍሴ በእሺታ(በደስታ ትለወጥ)/2/
       አዝ-----
ቅዱስ መንፈስህን ከኔ ላይ አትውሠድ
በንስሐ ድኜ(በተስፋ እንድላመድ)/2/
አቤቱ ንፁህ ልብ ፍጠርልኝና
በደስታ ልስከር(በፍቅርህ ልፅናና)/2/

├───────────────
├የሊቀ መዘምራን ይልማ መዝሙር
├───────────────
•✥•🍁  @Z_AbelMakbeb  🍁•✥•
              @Z_AbelMakbeb  
  •✥•🍁 @Z_AbelMakbeb 🍁•✥•






Mootiin samiif lafaa  ilma kee
Waqni samiif lafaa  mucaa kee
Kadhanaaf ati gara samii hin ilaaltu
Harka keera jira kan ati kadhattu/waaqessitu

Waaqayyoo samiiraa addunyaa daawwate
Kasoominakee arge maariyam si filate
Kan akka kee hin jiruu uumama hunda kessaa
arabnin koowaa'eekee addunyadhaaf labsa

dokimas dhiphuu isaa osson dubatiinii
Rakkoo isaa hubattee argamuu keetiinii
Iddoon atti jirtuu hundumtuu guutuudhaa
Namni sin qabaane jiruunsaa hiruudhaa


Nutoo  hin dandeenyu fuula isaa dhaabachuuf
Sumaaaaf yaa Maariyaam kun kan dnda'aamuuf
Akka sadoom taanee akka gamooraatti
Kadhanaa keetiinii nu gargaari atii

├───────────────
├ዘማሪ ዲ/ን ተክሌ
├───────────────
•✥•🍁  @Z_AbelMakbeb  🍁•✥•
              @Z_AbelMakbeb  
  •✥•🍁 @Z_AbelMakbeb 🍁•✥•


አዲስ ዝማሬ “ማርያም ማርያም“ ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ

ማርያም ማርያም ልበል
እረፍቴ ሆይ በስምሽ ልጠለል
የቃል እናት ያድናል ቃልሽ
ታምር ይሰራል ስምሽ


#አዝ__

ማር ልበል በምድር ያም ልበል በሰማይ
የማይጠግቡት መና የማይጨርሱት ሲሳይ
መንፈስ ቅዱስ ቃኝቶ ሰርቶ በሚስጥሩ
አፌ ላይ ጣፈጠኝ ስምሽ አጠራሩ (2)

#አዝ___

መዳኒት ታቅፈሽ  የአለሙን ጌታ
ከቤተልሄም ደጅ እስከ ጎለጎታ
የዓለሙን ህምም የዓለሙን በሽታ
ታክሚው ነበረ ድንግል በዝምታ (2)

#አዝ___

በምን እንመስልሽ የለሽም ምሳሌ
አንጠግብም ብንጠራሽ ብንዘምርልሽ ሁሌ
ምስክር አያሻም ያንቺ ልእልና
የአለሙን ንጉሥ ወልደሺዋልና (2)


#አዝ___

የወርቅ ማእጠንት እሳት የታቀፍሽ
የአዲስ ኪዳን ኪሩብ ማርያም አንቺ ነሽ
የአርያም እጣን ነሽ መአዛሽ ያማረ
ዘላለም አይወድቅም አንቺን ያከበረ (2)


├───────────────
├ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
├───────────────
•✥•🍁  @Z_AbelMakbeb  🍁•✥•
              @Z_AbelMakbeb  
  •✥•🍁 @Z_AbelMakbeb 🍁•✥•


መንፈሳዊ ትምህርት ዘኦርቶዶክስ| eotc theology ✟ dan repost
#እንኳን_አስተርእዮ_ማርያም_አደረሳችሁ

አስተርእዮ ማለት መታየት፣ መገለጥ ማለት ነው። ቃሉ አስተርአየ ታየ፣ ተገለጠ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ነው። ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገባው ቃል ኪዳን መሠረት በሥጋ የተገለጠበት(የታየበት) ፣ አንድነት ሦስትነቱም የተገለጠበት ወቅት በመሆኑ ከልደት በዓል እስከ ጥር መጨረሻ በሙሉ ዘመነ አስተርእዮ በመባል ይታወቃል።
✅ የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት በዘመነ አስተርእዮ ውስጥ ስለሚከበር “አስተርእዮ ማርያም” ተብሏል።ልቡናዋ በይኩነኒ የጸና ንጽሐ ሥጋ ፣ ንጽሐ ነፍስ ፣ ንጽሐ ልቡና አስተባብራ የያዘች ወላዲተ አምላክ ምንም እንኳን የአምላክ እናት ብትሆንም ሞተ ሥጋ ለሁሉም ዕጣ ፈንታ በመሆኑ በቃል መነገሩ በልብ መታሰቡ ከፍ ከፍ ይበልና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ተንሥኢ ወንዒ” የነፍሴ ደስታ የኾንሽ ውድ እናቴ ሆይ ተነሥተሽ ወደ እኔ ነዪ (መኃ ፪፥፲) ብሏታል።

♦ ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ፣ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉ
ቅዱስ ዳዊት “ነኪር ነገሩ በእንቲአኪ ሀገረ እግዚአብሔር” መዝ.፹፮፥፫ እግዚአብሔር ማህጸንሽን ከተማ አድርጎ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን የኖረብሽ ሆይ ስለ አንቺ የተነገረው የተደረገው ነገር ዕጹብ ድንቅ ነው እንዳለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ሆና ማረፏ ይደንቃል።
✅ ታላቁ የቤተክርስቲያናችን አባት ቅዱስ ያሬድ ሞቷ የሚያስደንቅ መሆኑን «ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉ፤ ሞት ለማናቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል» በማለት ገልጿል❗

✅ ባሕረ ጥበባት ፈልፈለ ማኅሌት ሊቁ ቅዱስ ያሬድ እመቤታችንን ሶልያና በማለት በሐዲስ ቅኔ ይቀኝላታል።

♦ለሶልያና ስመ ተጸውኦ መነሻ ግንዱ “ሴሊኒ” የሚለው ልሳነ ጽር (የግሪክ ቃል) ነው ይላሉ የሀገራችን የሰዋስው ሊቃውንት፤ በትርጉም ሶልያና ያለውን የቅዱስ ያሬድን ስያሜ ከሴሌኒ ጋር በአቻ ፍካሬ “ጨረቃ” የሚል ትርጉም ሰጥተውት እናገኛለን።

♦ ቅዱስ ያሬድ “ጊዜ ዕረፍታ ለሶልያና፣ ወረደ ወልድ እም ዲበ ልዕልና፣ ጠሊሳነ ንግሥ ሶቤሃ ከደና” አለ። ሶልያና ባረፈች ጊዜ ክብር፣ የክብርም ክብር የተገባው ወልድ ልጇ ክርስቶስ ከልዕልናው በልዕልና ወረደ እናቱን በጠሊሳነ ንግሥ በዚያን ጊዜ ሸፈናት። “ ጠሊሳነ ንግሥ ያለው የክብሯን መንዲል የንግሥናዋን መጎናፀፊያ ነው።


ሶ ➡ ሶበሰ ኪዳንኪ ምክንያተ ድኂን ኢሀሎ (ኪዳንሽ ባይኖር ምክንያተ ድኂን የለም)
ል ➡ ልሳንየ ላእላእ ይሴብሀኪ (ዲዳው ትብ አንደበቴ ያመሰግንሻል)
ያ ➡ያንቅአዱ ሀቤኪ ኩሉ ፍጥረት(ፍጥረታት ሁሉ ወደአንቺ ያንጋጥጣሉ)
ና ➡ ናሁ ተግህደ ልዕልናሃ ለድንግል፥ (እነሆ የድንግል ታላቅነቷ ተገለጠ)

✅ ማኅቶተ ቤተክርስቲያን ሊቁ ቅዱስ ያሬድ የእመቤታችን ዕረፍት የሰርግ ቀን በተባለ የዕረፍቷ ዕለት ሰማያዊውን ሰርግ በዓይነ ሕሊናችን አቅርበን ዕንድናይ እንዲል ሲል ያመሠግናታል።

ዮም ይባቤ የበቡ
ኃጢዓተ እለ ዘገቡ
በኪዳነ ድንግል ካህን ሥርየተ እለ ረከቡ
ከመ ይባኡ ለወልድኪ ውስተ ከብካቡ
የሊቁ ፍቅር ምንኛ ይደንቃል! የድንግሊቱ የአምላክ እናት “ቃልኪዳኗ” ኃጢአት ሲሰሩ ለኖሩ ሥርየተ የሚያሰጥ “ካህን” ነው ይላል። የታመኑባት ኃጥአን በዕለተ ምጽዓት በደስታ እየዘመሩ ወደ ሰርጉ አዳራሽ የሚሻገሩባት አግዓዚት፣ ተጨንቀው ለሚጠሯት ሰማዒት ፣ ወደ ማኅደረ ነፍስ የሚደርሱባት ማዕዶት እርሷው ናትና።

♦የእናታችን የእመቤታችን የእመብርሃን የወላዲተ አምላክ የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን አሜን❗

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
@dnzema
@dnzema
@dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯


ዝማሬ ቲዩብ zemare tube dan repost
🙏🙏🙏❤️❤️❤️

እነሆ የገና ስጦታ

ከተወዳጁ ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
እዲስ የዝማሬ አልበም

‘’በኃጢአተኛው ድንኳን ቅዱሱ ቆመሃል
ልጄ የት ነው ብለህ እኔን ፈልገኻል’’ በሚለው ዝማሬው የሁላችንንም ሕይወት የዳሰሰው…

አጋጣሚ አይደለም: ምልክቴ ነሽ ድንግል ለሕይወቴ፣ ማርያም ማርያም ልበል:
ይለይብኛል ሚካኤል፣ ምስጠረኛዬ ነሽ …..

ቀኑ ቀርቧልና በትዕግስት ጠብቁ‼️
├───────────────
├ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
├───────────────
•✥•🍁  @Z_AbelMakbeb  🍁•✥•
              @Z_AbelMakbeb  
  •✥•🍁 @Z_AbelMakbeb 🍁•✥•
🙏🙏🙏❤️❤️❤️

🌴🌴🌴


ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
        •➢ ሼር // SHARE

╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
          @dnzema
          @dnzema
          @dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯

ጥምቀተ ባሕር


ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
        •➢ ሼር // SHARE

╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
          @dnzema
          @dnzema
          @dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯
ኦ ክርስቶስ


ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
        •➢ ሼር // SHARE

╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
          @dnzema
          @dnzema
          @dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯
እዩት


ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
        •➢ ሼር // SHARE

╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
          @dnzema
          @dnzema
          @dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯

አጅበን መጣን


ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
        •➢ ሼር // SHARE

╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
          @dnzema
          @dnzema
          @dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯
መፅአ ቃል


ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
        •➢ ሼር // SHARE

╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
          @dnzema
          @dnzema
          @dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯

ዮሐንስኒ ያጠምቅ


ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
        •➢ ሼር // SHARE

╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
          @dnzema
          @dnzema
          @dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯

Collection


ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
        •➢ ሼር // SHARE

╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
          @dnzema
          @dnzema
          @dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯
የጥምቀት መዝሙሮች


ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
        •➢ ሼር // SHARE

╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
          @dnzema
          @dnzema
          @dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯

በወንጌሉ ያመናችሁ


ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
        •➢ ሼር // SHARE

╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
          @dnzema
          @dnzema
          @dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯

በዮርዳኖስ የተጠመቀው


ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
        •➢ ሼር // SHARE

╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
          @dnzema
          @dnzema
          @dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯

በጎል ሰብዓ ሰገል


ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE

╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
@dnzema
@dnzema
@dnzema
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯

አለው ሞገስ ጥምቀት ሲደርስ

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.