ከእለታት....📖📚📖📚📖📚


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Inglizcha


ለአስተያየታችሁ @Shedorka

Bog‘liq kanallar  |  O‘xshash kanallar

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Inglizcha
Statistika
Postlar filtri


ይሄንን Back Support ብቻ በማድረግ በቁመትህ ላይ ትልቅ ለውጥ እንደሚመጣ  ታውቃለህ?

አብዛኞቻችን አጭር ሳንሆን  ነገር ግን በተለያዩ ጫናዎች ምክንያት በተለይ ቢሮ ውስጥ ለምንሰራ,ለራይድ ሾፌሮች እንዲሁም ከ ኮምፒዩተር ጋር የምናሳልፍ ሰዎች ጀርባችን ላይ በሚደርስ ጫና ምክንያት የጀርባችን አከርካሪ አጥንት እንደመጉበጥ አይነት ቅርጽ ይይዛል በዚህም ምክንያት ቁመታችን እንዲቀንስ ያደርጋል

ነገር ግን ይሄንን Back Support ከተጠቀማችሁ ለጀርባችሁ መጉበጥ መፍትሄ ይሰጣል በተያያዥነት ደግሞ ቁመታችሁን ይጨምራል

      💴ዋጋ:- 1750ብር + free delivery

ይሄንን Back Support ለማግኘት በ t.me/DashXpress ያናግሩን በአዲስ አበባ እንዲሁም በክልል ከተሞች እና ክፍለሀገራት በነጻ deliver እናደርጋለን


እንዲሁም የእኛን Promo code #ይሄንን Back Support ብቻ በማድረግ በቁመትህ ላይ ትልቅ ለውጥ እንደሚመጣ  ታውቃለህ?

አብዛኞቻችን አጭር ሳንሆን  ነገር ግን በተለያዩ ጫናዎች ምክንያት በተለይ ቢሮ ውስጥ ለምንሰራ,ለራይድ ሾፌሮች እንዲሁም ከ ኮምፒዩተር ጋር የምናሳልፍ ሰዎች ጀርባችን ላይ በሚደርስ ጫና ምክንያት የጀርባችን አከርካሪ አጥንት እንደመጉበጥ አይነት ቅርጽ ይይዛል በዚህም ምክንያት ቁመታችን እንዲቀንስ ያደርጋል

ነገር ግን ይሄንን Back Support ከተጠቀማችሁ ለጀርባችሁ መጉበጥ መፍትሄ ይሰጣል በተያያዥነት ደግሞ ቁመታችሁን ይጨምራል

      💴ዋጋ:- 1750ብር + free delivery

ይሄንን Back Support ለማግኘት በ t.me/DashXpress ያናግሩን በአዲስ አበባ እንዲሁም በክልል ከተሞች እና ክፍለሀገራት በነጻ deliver እናደርጋለን


እንዲሁም የእኛን Promo code 4 ተጠቅመዉ ሲገዙ የ 5% ቅናሽ ያገኛሉ


ታስገቡኛላችሁ🥹


እንደምን ከረማችሁልኝ


ታጥበው የማይጠሩ ትዝታዎች የሚጠለሉበት ጫካ ይመስለኛል....ፀጉር...አንድ አንዴም ክፉ ደጋችንን የሚመዘግብ የሆነ ነገረኛ የእድር ቤት ዳኛ.....


አዲስ ታሪክ ያስፈልገኛል....


ፀጉሬን ብቻ እንደቆረጥኩት አላስብም....የፀጉሬን ዘለላ የዳበሱ ቆሻሻ እጆችንም አብሬ የቆረጥኩ ይመስለኝና አንጀቴ ቂቤ ይጠጣል...አፍንጫዬ ስር የቀሩ የትዝታ ጠረኖችንም ጭምር....ለሀጥአን የመጣ ለፃድቃን ይተርፋል እንደሚሉት የሀያቴንም ውብ እጆች አብሬ የቆረጥኳቸው ይመስለኛል....ብዙ ናፍቆት የቆረጥኩ....የማይመጣን ሰው መጠበቅ ያቆምኩ ይመስለኛል....


ትዝታን ማባበል ያቆምኩ....ከሀያ ሀምስት አመት በኃላ እድሜዬን አንድ ብዬ የቆጠርኩ ይመስለኛል.....



ሸዊት እባላለሁ....ዛሬ ከተወለድኩ አንደኛ ቀኔ ነው....



✍Shewit



https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka




ነገ ይሁንልኝ....ድካም ተጫነኝና ይሄን ረጅም ስሜን ማብራራት ደከመኝ😁


ስንቶቻችሁ ናችሁ ስሜን እንዳስቀየርኩ የምታውቁት.....?



በአስራ አምስት አመቴ ያሳፍራሉ ብዬ ጓዳ የከተትኳቸው ታሪኮቼ ብዙ ናቸው....በሀያ አምስት አመቴ ግን በታሪክ ማፈር ራሱ እንደሚያሳፍር ገባኝ.....



ስሜን እየገመታችሁ ቆዩኝ እኔ አመሻሽቼ ሙሉ ታሪኩን እነግራችኃለሁ....



💙




አንተን የማመልክበት ሀይማኖት ፈጠርኩ....'ከንፈርህን በቅርበት ያየውበት ቀን የተቀደሰ ነው'....ብዬ አንቀፅ ፈበረኩ...ያድናል ብዬ አደባባይ ስምህን ሰቅዬ ወጣሁ....እኔ ብቻዬን ስለምከተልህ የአይን እማኝ የጠየቀኝ የለም....እኔን አምኖ የሚከተልህ የለም....እንዴት ተደፈነባቸው ጃል....ብቻዬን የምገባበት ኤዶም....ብቻዬን የምነግስበት መንበር ሆንክ..


ሞተሀል ይሉኛል.....ይቅር ይበላቸው.....አምላክ ቢሞትስ በሰልስተኛው ቀን ይነሳ የለ እንዴ....ለምን ዝም ትላለህ.... እስቲ ገብርኤልን ልከህ የቤታቸውን መጋረጃ ቅደደው....ሚካኤል እንዳያስቆመው 'አንድ አፍታ ባህራን እንዴት ሆነ....ደብዳቤውን ቀየርከው እና ለንጉስ ልጅ ዳርከው እንጂ ትዳር እንዴት ነው ብለህ አልጠየቅከውም....ጠይቀኧው ና' ብለህ ላከው.....



እንዴት አይነት ብልግና ነው....አብደሻል ደግሞ ይሉኛል....'እርቃንሽን ቆምሽ' ብለው እኮ ነው....ታዲያ አንተ ፊት ብራቆት ምን አለ....



'ይበርድሻል ደርቢ' ብለው ዲሪቶ ያሸክሙኛል....እቅፍህን ከማያውቅ ድፍን ህዝብ ጋር እንዴት ልግባባ....



ምን ቤት አለሽ መሀል አስፋልት ላይ ነው ውሎ አዳርሽ ይሉኛል'....ኧረ ገብርኤልን ላከው ግድ የለህም....





✍Shewit




https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

5k 0 15 10 82



አልተኛችሁም ወይ....የሆነች 'ፍሪ ስታይል' ፅሁፌን ላጋራችሁማ


ሶፊ ሲጠይቅ ሰምቼ ነው.....




እኔስ የሆነ የምንገናኝበት መድረክ ባዘጋጅ ስንቶቻችሁ ትመጡልኛላችሁ...?



የምትመጡ በላይክ አሳዩኝ

4.3k 0 2 17 125

እናንተ መፅሀፌን መፃፍ ጀመርኩ እኮ🥹


ለአንድ ሰአት ልተኛ ብዬ ባሸልብ እዛው ቀረሁና ሰይጣን ልጁን በሚድርበት ሰአት ነቃሁ😁


ቦሀላ የምነግራችሁ አለኝ💙


እንደዚህም እንሰራለን💐




ለማዘዝ👉@shedorka


ሳየው ልጅነቴን የሚያስታውሰኝ ልጅ ነበር...ምንም ምንም ሳላውቀው ልጅነቴን ያስታውሰኝ ነበር...


ለህክምና ስራ ቦታዬ የሚመጣው በሳምንት ሶስት ቀን ነበር...ፈገግታው እንደትናንት ትዝ ይለኛል....ያለ ምንም ወሬ ለምን ልጅነቴ ጋር ፊጥ እነዳለ አላውቅም....ጠይም ነበር....የተመጠነ ፈገግታ ያለው...እድሜ ለህክምናው ሂደት....ነፍ ጊዜ ጠጋ ብዬ አይቼዋለሁ....አሌክስ እንደሚለው አፍንጫው ሌላ ሀገር አይኑ ደግሞ ሌላ ሀገር ቢገኙ እኩል የሚደነቁለት አይነት ሰው ነበር....



አሁንም ግን ጥያቄ የሚሆንብኝ እንዴት ልጅነቴ ጋር ወሰደኝ የሚለው ነው...ልንወድ ስንፈልግ....ልባችን ሲከጅል ካብ ላይ እንደምንሰቅለው ሆኖ ነው ወይስ የምርም ልጅነቴን ይመስላል....?....አላውቅም።



'ልጅነቴ እንደ እሱ ጠየም ያለ ነበር'.....አልኳቸው የስራ ባልደረቦቼን....'ምክንያት ስደረድር እንጂ ልጅነት ከለር ነበረው....?'....መሄጃ የላቸውም ብዬ ተፈላሰፍኩባቸው.....



አንድ ቀን ግን በጣም ጠበቅኩት....ላቅፈው....የእንግዳ መቀበያ ጋር የተቀመጡ የስራ ባልደረቦቼን 'ይሄን ልጅ ላቅፈው ስለምፈልግ ሲመጣ ያየው ሰው ይጥራኝ' ብያቸው ገባሁ....የአንዳንድ ቀን ድፍረቴ የእብድ ነው....ጨርቁን የጣለ ድፍረት።



...'ስለፈጠረሽ አምላክ አትጃጃይ' ብሎ ያልለመነኝ ጓደኛ አልነበረም....አንገቴ በካራ ልጅነቴንማ አቅፈዋለሁ አልኩ.....



ጠበቅኩት....በጣም ጠበቅኩት....ሳይመጣ መሸ....'ሙሽራዬ ቀረ' ብዬ ልዘፍን ትንሽ ነበር የቀረኝ....እንደ ምንም ታግሼ ቀጣይ ቀንም ጠበቅኩት....አልመጣም.....



እዚች ጋር ልጅነቴን መሰለ....ልጅነቴም ቀረሁ ሳይለኝ ነበር የቀረው.....ልክ ነበርኩኝ።




(based on true story)




✍Shewit




https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

5.1k 0 14 7 129



ካልተኛችሁ የሆነ ነገር ላጋራችሁ


የሆነ ጊዜ ላይ 'እነዚህ ጓደኞቼ ነገዬን ያበላሻሉ' ብዬ የተውኳቸው ሰዎች ነበሩ.....


አሁን ምን አይነት መበለሻሸት ውስጥ እንዳለሁ ሳስበው 'እነሱ ቢኖሩ ከዚህ በላይ ምን ይፈጠር ነበር' እላለሁ....



ወግ ወጉንማ ይዤው ነበር...የእነሱን ነገ ሳላበላሽ አመለጡ😁

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.