Spiritual Books


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Din


" የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ። በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ አስተምሩና ገሥጹ። በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ በጸጋው በልባችሁ ለእግዚአብሔር ዘምሩ።"
(ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:16)

Read best christian spiritual books.
ምርጥ መንፈሳዊ የ ክርስቲያን መጻሕፍት ያንብቡ!
Your Comment @puritanBaxter

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Din
Statistika
Postlar filtri


ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያው ድረስ የእግዚአብሔር ስም ይመስገን።
— መዝሙረ ዳዊት 113:3


"በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል።"
(መዝሙረ ዳዊት 65: 11)

  እንኳን አደረሳችሁ
 መልካም አዲስ ዓመት ይሁንላችሁ።


👆👆👆👆👆👆👆
-------------------
The Prayer Of A Broken Heart

By  Robert Candlish
------------------
@spiritual_books




ወንጌሉ አገልግሎት Wongelu Ethiopia Ministries dan repost
ምክንያታዊነት ዓመጽን ሲያገለግል | ሰኔ 12

ሰነፍ፣ “አንበሳ ውጭ አለ፤ መንገድ ላይ እገደላለሁ” ይላል። (ምሳሌ 22፥13)


ምሳሌው ይላል ብዬ ያሰብኩት ይህንን አልነበረም። “ፈሪ፣ ‘አንበሳ ውጭ አለ፤ መንገድ ላይ እገደላለሁ’ ይላል” እንዲል ጠብቄው ነበር። ነገር ግን የሚለው “ሰነፍ” እንጂ “ፈሪ” አይደለም። ስለዚህ፣ እዚህ ጋር ተቆጣጣሪው ስሜት፣ ስንፍና እንጂ ፍርሃት አይደለም።

ታዲያ ግን ስንፍናን እና በመንገድ ላይ ያለ የአንበሳ አደጋን ምን አገናኛቸው? መቼም አብዛኛውን ጊዜ፣ “ይህ ሰውዬ አንበሳ ውጪ አለ ብሎ ስራውን ለመስራት እጅግ ሰንፏል” አንልም።

ምን እያለ ነው? ሰነፍ ሰው ሥራ ላለመስራቱ ማመካኛ ለማቅረብ ምናባዊ ሁኔታዎችን ይፈጥራል። ከዚያም የሁሉንም ትኩረት ከስንፍና በሽታው አንስቶ ወደ አንበሶች ያዞረዋል። ቀኑን ሙሉ ቤት የሚቀመጠው በስንፍናው ብቻ ከሆነ ማንም አይቀበለውም። ግን መንገድ ላይ አንበሳ አለ ካለ፣ አሳማኝ ምክንያት ሊመስልለት ይችላል።

ከዚህ ልንማር የሚገባን መሠረታዊ የሆነ አንድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት፣ ልባችን የሚፈልገውን ነገር ለማግኘት ማሳበቢያ የሚወስደው አእምሮአችንን በመጠቀም እንደሆነ ነው። ይህ ማለት፣ ጥልቅ ምኞቶቻችን፣ ጥሩም ሆኑ መጥፎ፣ ከአእምሯችን ምክንያታዊ አሠራር ይቀድማሉ። አዕምሯችን እነዚህን ምኞቶች የሚረዳው ተገቢ እንደሆኑ ፍላጎቶች አድርጎ ነው።

ሰነፍም ሰው የሚያደርገው ይህንኑ ነው። አለመሥራትን እና ቤት መጎለትን ከልቡ ይፈልጋል። ነገር ግን ሥራ ፈትቶ ቤት ለመቀመጥ ጥሩ ምክንያት ያስፈልጋል። ስለዚህ ምን ያደርጋል? ክፉውን የስንፍና ፍላጎቱን ያሸንፋል? አያሸንፍም። ይልቁንም ለምኞቱ ማመካኛ ለማቅረብ፣ አእምሮውን በመጠቀም ምናባዊ አደጋዎችን ይፈጥርና ለዚህ ነው ቤት ቁጭ ያልኩት ይላል።

ኢየሱስ፣ “ብርሃን ወደ ዓለም መጣ፤ ሰዎች ግን ሥራቸው ክፉ ስለ ነበረ፣ ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ወደዱ” ብሎ ተናግሯል (ዮሐንስ 3፥19)። ጨለማን የምንወደው ማድረግ የፈለግነውን ሳንጋለጥ ማድረግ ስለሚያስችለን ነው። አዕምሯችን ደግሞ የልባችን ክፉ ምኞት እንዳይጋለጥና እንዳይጠፋ ለመጠበቅ ሲል ጨለማ የሚያመርት ፋብሪካ ይሆናል። ዕለት ዕለት ግማሽ እውነት፣ ውሸት፣ ማጭበርበር እና ክህደት በዓይነት በዓይነት ያመርታል።

ይህንን ልብ በሉ። አስተዋይ ሁኑ።

Telegram
| YouTube | Facebook | Instagram | TikTok | Website

#ለዛሬ




ደሙ እንደ ውሃ(2×) ጎረፈ፤
የጌታ ጀርባ በጅራፍ ተገረፈ፤
እግሩ እስኪነቃ ተራራውን ነጎደ፤
እስከሞት ድረስ ጌታ እኔን ወደደ።


ሮሜ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ ገና ደካሞች ሳለን ክርስቶስ ዘመኑ ሲደርስ ስለ ኃጢአተኞች ሞቶአልና።

⁷ ስለ ጻድቅ የሚሞት በጭንቅ ይገኛልና፤ ስለ ቸር ሰው ግን ሊሞት እንኳ የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል።

⁸ ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል።
--------------


አዝ፦ አንጨነቅ x3
በከንቱ በከንቱ
ጌታችን ሲጠብቀን
ከእጁ ማንም አይነጥቀን
ያድነናል ከሚያስፈራው ቀን


Q1: What is the chief end of man?

Ans: Man's chief end is to glorify God, and to enjoy Him forever.


👆👆👆👆👆👆👆👆
----------------------------------
 መጽሐፈ ትርጓሜ ገላትያ ቅጽ ፩

በ ሔኖክ ኢሳይያስ
----------------------------------
@spiritual_books




"በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል።"
(መዝሙረ ዳዊት 65: 11)

  እንኳን አደረሳችሁ
 መልካም አዲስ ዓመት ይሁንላችሁ።


👆👆👆👆👆👆👆
-------------------
God's high calling for women

By  John MacArthur
------------------
@spiritual_books




“እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።”
— ኢሳይያስ 53፥5


👆👆👆👆👆👆👆👆
------------------

መንፈስ ቅዱስ እና
ካሪዝማዊ ቀውሶች

ከ ዘላለም መንግሥቱ
----------------
@spiritual_books







20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.