የቅዱስ ዑራኤል ልጆች / st Urael


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Din


የ.,ኦ.ተዋህዶ መንፈሳዊ ትምህርቶችና ሀሳቦችን መለዋወጫ ገጽ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Din
Statistika
Postlar filtri




እንኳን ለሊቀ መልዓኩ ቅዱስ ሚካኤል በዓለ ሲመት አደረሳችሁ ህዳር 12 ቅዱስ ሚካኤል የተሾመበት እለት ነው


መጪ ንግስ በዓላት
ህዳር 6 ቁስቋም ማርያም
ህዳር 7
ቅዱስ ጊዮርጊስ (ቅዳሴ ቤቱ)
ህዳር 8
ኪሩቤልወሱራፌል
ህዳር 12 ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መልአክ የተሾመበት
ህዳር 15
ቅዱስ ሚናስ እረፍቱ
ህዳር 21 ጺዮን ማርያም
ታቦተ ጺዮን ወደ ኢትዮጵያ የመጣችበት
ህዳር 25
ቅዱስ መርቆርዮስ ሰማእት


እንኳን ለ ቁስቋም ማርያም አደረሳችሁ






ጎዶልያስ የጉዞ ማህበር dan repost
ታላቅ የበረከት የፈውስ ጉዞ እሁድ 10 ጥቅምት

ኮራ ማርያም ገዳም

ታላቋ ገዳም ኮራ ማርያም ዳግማዊት ኩክየለሽ ማርያም ትባላለች ከአዲስ አበባ በ30 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ገላን ከተማ ዱከም መግቢያ ላይ የምትገኝ ጥንታዊ ተአምረኛው የእመቤታችን ኮራ ማርያም ገዳም

«እናንተ » ፍቅሯ የበዛላችሁ ደግነቷን ያያችሁ፣ በፈዋሽ ጸበሏ ሁሉም እየዳነ በእምነቷ ተዳብሰው ተዓምሯን በዓይናቸው እያዩ ነው። ኮራ ማርያም በህልም በራዕይ ተገልፃ ለአንድ ቀን ደጇን የረገጠ የማይፈታውን እንቆቅልሽ እየፈታችላቸው ነው ከወደቁበት አንስታ በክብር ማማ ላይ እያቆመች ነው

ኮራ ማርያምን ገዳም .......ኑ.....እዩ ...

እናታችን እንደ እኛ ሀጥያት ሳይሆን እንደ ልጇ ቸርነት ይቅር ባይነት ትረዳን ዘንድ ምልጅዋ በረከቷ ይድረሰን ዘንድ በፍቅሯ ትሰብስበን በሰላም ታገናኘን።

የደርሶ መልስ ጉዞዎችን አዘጋጅተናል

ይመዝገቡ እና አብረን እንጓዝ እንባረክ

09 47 15 15 15

በአሉበት ሆነው ሆነው የመኪና ወንበር ማስያዝ ይችላሉ

የትራንስፖርት ደርሶ መልስ ዋጋ መስተንግዶን ጨምሮ 300 ብር

Fastmerejaa


ጥቅምት 9/2017 #ፃድቁ_አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ለፃድቁ #አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ ወርሐዊ መታሰቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉አቡነ #እስትንፋሰ_ክርስቶስ አባታቸው መልአከ ምክሩ እናታቸው ወለተ ማርያም ይባላሉ የተወለዱበት ልዩ ቦታው ወሎ ክፍለ ሀገር ዳውንት ነው

👉በተወለዱ ዕለት ተነሥተው በእግራቸው ቆመው ሦስት ጊዜ ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ብለው #ፈጣሪያቸውን አመስግነዋል የስማቸው ትርጓሜ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ አንድም #የክርስቶስ እስትንፋስ ማለት ነው

👉ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቃቸውና በመንገዳቸው ሁሉ እየመራቸው ነው ያደጉት #መንፈስ_ቅዱስ ልቡናቸውን ብሩህ አድርጎላቸው በ5 ዓመታቸው የቅዱሳት መጻሕፍት ቃላትን፣ ብሉያትንና ሐዲሳትን፣ ድርሳናትንም ጠንቅቀው ዐውቀዋል

👉በተወለዱ በ14 ዓመታቸው ወደ #አቡነ_ኢየሱስ ሞዐ ደብረ ሐይቅ ገዳም ሄደው ከባሕር ዳር ቆመው የሙሴን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር በጸለዩ ጊዜ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ባሕሩን አሻግሯቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተዋል፡፡

👉ለ3 ዓመታት ያህል በኃይቅ ገዳም ለመነኮሳት እንጨት በመልቀምና ውሃን በመቅዳት #ለአባቶች_መነኮሳት ምግብ የሚሆናቸው ዓሣ ከባህር ውስጥ በማውጣት አገልግለዋል፡

👉አባታችን #እስትንፋሰ_ክርስቶስ 40 መዓልትና 40 ሌሊት ከፆሙ በኋላ ምንም እህል ሳይቀምሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስቀድሞ ለሙሴ በደብረ ሲና እንደሰጠው ለአባታችንም ወደ እርሳቸው መጥቶ ዓሥሩን ቃላተ ኦሪትና ስድስቱን ቃላተ ወንጌል በውስጣቸው የተጻፈባቸው ሁለት ጽላቶችን ሰጥቷቸዋል፡፡

👉አቡነ #እስትንፋሰ_ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ከሠሩ በኋላ ዕለቱን ስንዴ ዘርተው፣ ወይን ተክለው፣ ጽድን ወይራንና ግራርን ተክለው በአንዲት ቀን ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ዕለቱን አድርሰዋል ስንዴውን ለመሥዋዕት ወይኑን ለቍርባን በተአምራት አድርሰዋል፡፡

👉አባታችን በጸሎት ላይ እንዳሉ ቅዱስ ሚካኤል ተልኮ መጥቶ አባታችንን በደመና ጭኖ ወስዶ ከጌታችን ከመድኃኒታችን #ከኢየሱስ_ክርስቶስ ፊት አቆማቸው ጌታንም በቅዱሳኑ ሁሉ እንዲባረኩ ካደረጋቸው በኋላ መልአኩን ‹‹ወደ ተወለድኩባትና ወደ ኖርኩባት ቦታ ወደ ኢየሩሳሌም አድርሰው›› ብሎት ኢየሩሳሌምን አሳልሞ ሀገራችን መልሶ አምጥቷቸዋል

👉አባታችን ሁሉንም የኢትዮጵያን ቅዱሳት ገዳማትን ተዘዋውሮ ሲጎበኙ በሕይወተ ሥጋ የሌሉት የየገዳማቱ ቅዱሳን ሁሉ በአካል ይገለጡላቸው ነበር ጎጃም ውስጥ እያስተማሩ፣ !፣ የታመሙትን እየፈወሱ፣ የዕውራንን ዐይን እያበሩና ሙታንን እያሥነሱ ብዙ ካገለገሉ በኋላ ለዘጠኝ ዓመታት በባሕር ውስጥ ገብተው ቁልቁል ተዘቅዝቀው #ለኢትዮጵያ_ፀልየው የምሕረት ቃልኪዳን ተቀብለዋል

👉ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ጌታችን መጥቶ ‹‹ከመነኮሳት ሁሉ ብልጫ ያለህ ወዳጄ ሆይ #ኢትዮጵያንና_ሕዝቦቿን ምሬልሃለሁ ከዚህች ባሕር ውጣ በማለት በሞት የሚያርፉበትን ቦታ ነግሯቸዋል፡፡

👉ጻድቁ ወደ ደብረ አሰጋጅ በሚሄዱበት ጊዜ ጸሐይ ልትገባ ስትል ‹‹በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አውግዤሻለሁ ለመስፍን ኢያሱ በገባኦን እንደቆምሽ አሁንም ቀጥ ብለሽ ቁሚ ብለው ፀሐይን አቁመዋል አቡነ #እስትንፋሰ_ክርስቶስም ደብረ አሰጋጅ ሲደርሱ ፀሐይ አፍ አውጥታ ‹‹አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ እገባ ዘንድ ፍታኝ›› ስትላቸው #እግዚአብሔር_ይፍታሽ ባሏት ጊዜ ጠልቃለች

👉ጻድቁ ሌላው በእጅጉ የሚታወቁበት አንድ ትልቅ ቃል ኪዳን አላቸው በአምላክ ልቡና የሚገኝ፣ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ልቡና የሚገኝ፣ በቅዱስ ሚካኤልና በቅዱስ ገብርኤል ልቡና የሚገኝ እንደ #መልክአ_መድኃኔዓለም ያለች እጅግ አስገራሚ ፀሎት አለቻቸው፤ እርሷን ፀሎት በፀለዩ ጊዜ እልፍ ነፍሳትን ከሲኦል ያወጣሉ

👉ጸሎቷም #የመድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች እያንዳንዱ የሰውነት ክፍሎቹ የተቀበሉትን ጸዋትዎ መከራዎች ሁሉ ታዘክራለች በእያንዳንዱ ክፍልም የጸሎት ማሳረጊያ #አቡነ_ዘበሰማያት ይደግማሉ ንስሓ የገባ ኃጢአተኛ ሰው እንኳን ቢሆን ይህችን የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስን ጸሎት በጸለየ ጊዜ ሺህ ነፍሳትን ከሲኦል እንደሚያወጣ ጌታችን በማይታበል ቃሉ ለአባታችን ነግሯቸዋል

👉እያንዳንዱን #የመድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች መከራዎቹን የምታዘክረውን ይህቺን በአምላክ ልቡና ያለች ግሩም የሆነች ፀሎት ነፍሳትን ከሲኦል አታወጣም ብሎ የሚጠራጠር ቢኖር መንግስተ ሰማያትን አያያትም ፃድቁ ታኅሣሥ 8 ቀን ተወልደው ሚያዚያ 9 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል

👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከፃድቁ ረድኤት በረከት ያሣትፈን #የፃድቁ_አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ ምልጃና ፀሎት ሁላችንንም ይጠብቀን የተባረከ #ቀዳሚት_ሰንበት ይሁንልን "አሜን" ✝️💒✝️


ፃዲቁ አባታችን አቡነ ዜና ማርቆስ ወርሃዊ በዓላቸው በ 3 ነው ገዳማቸውን ወይም በስማቸው ቤተክርስቲያን ወይም ታቦት ያለበትን ቦታ ብታሳውቁኝ በትህትና እጠይቃቸዋለሁ በረከታቸው ይደርብን ።




እንኳን ለ ሊቀመልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ወርሃዊ በዓል አደረሳችሁ የቅዱስ ዑራኤል ረድኤት በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን




እንኳን ለሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ወርሃዊ በዓል አደረሳችሁ


ሐዋርያው ቅዱስ ፊሊጾስ






እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መልአክ ወርሃዊ በዓል አደረሳችሁ


ይህ ቻናል መታሰቢያነቱ ለሊቀ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው የመላኩ ወዳጆች በዚህ ገጽ ሚተላለፋ ሀሳቦች ለብዙሀን ይደርስ ዘንድ ለወዳጅ ዘመድ አስተዋውቁ በ አዲሱ አመት ተጨማሪ subscriber እንዲያገኝ የበኩላቹሁን ተወጡ ሰላመ እግዘብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን


እንኳን ከዘመነ ዩሐንስ 2016 ወደ ዘመነ ማቲዎስ 2017 በሰላም አደረሳችሁ ዘመኑ የሰላም የአንድነት የንስሃ የበረከት ያርግልን እግዚአብሔር አምላካችን ከሀጢአት በቀር ሀሳባችንን ይፈጽምልን ።



20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.