የሞትከውስ አንተ! !
ያ ዒሳን አምላኪ
መስቀልን ሰባኪ
ሞተልኝ ሞተልኝ ማለቱ ሳይበቃው
ሞተልህ ይለኛል እስኪነቃ ላንቃው
የሞትከውስ አንተ ሟችን ያመለ’ከው
በክህደቱ ቢላ ራስህን ያረድከው !!
ያ ሁሉ ድብደባ መገፋት መወገር
ስቃይን መጋቱ በዛ ጉድ መሰንቀር
ከማን ላይ ምን ሊያስቀር? !
ምህረትን የሻ እንደሁ ለሰው ለፍጥረቱ
ማለፍን ቢፈልግ ለወንዱ ለሴቱ
ምን ሊፈይድ ከቶ በ’ንጨት ላይ መሞቱ?!!
ማን ላይ ምን ሊጨመር መድማት መ’ጎተቱ?!
ያ ዒሳን አምላኪ
መስቀልን ሰባኪ
ሞተልኝ ሞተልኝ ማለቱ ሳይበቃው
ሞተልህ ይለኛል እስኪነቃ ላንቃው
የሞትከውስ አንተ ሟችን ያመለ’ከው
በክህደቱ ቢላ ራስህን ያረድከው !!
ያ ሁሉ ድብደባ መገፋት መወገር
ስቃይን መጋቱ በዛ ጉድ መሰንቀር
ከማን ላይ ምን ሊያስቀር? !
ምህረትን የሻ እንደሁ ለሰው ለፍጥረቱ
ማለፍን ቢፈልግ ለወንዱ ለሴቱ
ምን ሊፈይድ ከቶ በ’ንጨት ላይ መሞቱ?!!
ማን ላይ ምን ሊጨመር መድማት መ’ጎተቱ?!