ዘግይቶ ወደ ጀማዐ ሶላት የሚቀላቀል ሰው
~
1- ወደ ሶላቱ ሲገባ ተረጋግቶ እንጂ እየተዋከበ መምጣት የለበትም። ኢማሙን ሩኩዕ ላይ ቢያየው እንኳ መሮጥ የለበትም።
2- የተጀመረ ሶፍ ሳይሞላ ጥሎ ለብቻው መቆም ወይም አዲስ መጀመር የለበትም።
3- እንደደረሰ ኢማሙን ባለበት ሁኔታ ሊከተለው ይገባል። እንጂ ሶፍ ላይ ቆሞ ኢማሙ እስከሚቆም ወይም ለተሸሁድ እስከሚቀመጥ መጠበቅ የለበትም። ሩኩዕ ላይም ይሁን ሱጁድ ላይም፣ ተሸሁድ ላይም ቢሆን ይከተለው።
4- ኢማሙን መከተል ከመጀመሩ በፊት ወደ ሶላት መግቢያ የሆነውን ተክቢረተል ኢሕራም ሊዘነጋ አይገባም። ያለ ተክቢረተል ኢሕራም ሶላት ውስጥ እንደገባ አይቆጠርምና። ተክቢረተል ኢሕራም ቆመን ነው ማለት ያለብን። እየወረድን፣ እየተንቀሳቀስን አይደለም።
5- ኢማሙን ቆሞ ካላገኘው ከተክቢረተል ኢሕራም ቀጥሎ የሚቀራውን የመክፈቻ ዱዓእ አይቀራም። (ለምሳሌ
سُبْحَانَكَ اللَّهُمَّ وَبِحَمْدِكَ، وَتَبَارَكَ اسْمُكَ وَتَعَالَى جَدُّكَ، وَلَا إِلَهَ غَيْرَكَ)
የመክፈቻ ዱዓእ ቦታው ቂያም (መቆም) ላይ ነው። ተክቢራ ካደረገ ጀምሮ ኢማሙን መከተል ግዴታው ነው። ስለዚህ ኢማሙ ቂያም ላይ ካልሆነ ግዴታ ባልሆነ ነገር ኢማሙን ከመከተል ሊዘናጋ አይገባውም።
6- ኢማሙን ሩኩዕ ላይ ከደረሰበት ሙሉ ረከዐውን እንዳገኘ ይቁጠረው። ነብዩ ﷺ እያሰገዱ ሩኩዕ ላይ እያሉ ሶሐቢዩ አቡ በክረህ - ረዲየላሁ ዐንሁ - ደረሰ። ሶፍ ሳይደርስ ኢሕራም አድርጎ ከዚያም ሩኩዕ በማድረግ ፈጥኖ ከሶፉ ተቀላቀለ። ነብዩ ﷺ ሶላት ካጠናቀቁ በኋላ "አላህ ጉጉትን ይጨምርልህ። ግን እንዳይደገምህ" አሉት። "እንዳይደገምህ" ያሉት መፍጠኑን ነው። እንጂ ሩኩዕ ላይ የደረሰበትን "ስለማይቆጠር ተነስና አንድ ረከዐ ጨምር" አላሉትም። ሩኩዕ ላይ መድረስ የማይቆጠር ቢሆን ኖሮ አንድ ረከዐ እንዲጨምር ያዙት ነበር። ልብ በሉ! አቡበክራ የፈጠነው ሩኩዕ ላይ ለመድረስ ነው። ሩኩዕ ላይ መድረስ የማይቆጠር ቢሆን ኖሮ አቡ በክራ ሩኩዑን ለማግኘት ባልተቻኮለ ነበር። ይሄ ተግባሩ ሶሐቦች ዘንድ በዚህ ጉዳይ ላይ ያለውን ግንዛቤ ያሳየናል።
በነገራችን ላይ ሩኩዕ ላይ ሲደርሱ ሙሉ ረከዐ አድርጎ ማሰብ ከሌሎችም ብዙ ሶሐቦች ተገኝቷል። እንዲያውም በዚህ ጉዳይ ላይ ሰለፎች ዘንድ ልዩነት የለም ይላሉ ኢማሙ አሕመድ ረሒመሁላህ።
7- ያለፈው ረከዐ ካለ ኢማሙ ሳያሰላምት በፊት የጎደለውን ለመሙላት እንዳይነሳ። ይልቁንም ኢማሙ ማሰላመቱን ካረጋገጠ በኋላ ተነስቶ የጎደለውን ይሙላ።
8- ያለፈው ረከዐ ካለ ከኢማሙ ጋር ያገኘው ለሱ የመጀመሪያው ነው። ለምሳሌ ሶላቱ ዒሻእ ቢሆንና ኢማሙን 4ኛ ረከዐ ላይ ቢያገኘው ለሱ የመጀመሪያ ረከዐው ነው። ስለዚህ ኢማሙ ሲያሰላምት የሚነሳበት ረከዐ ለሱ 2ኛው እንጂ የመጀመሪያ ረከዐው አይሆንም። ስለሆነም በዚህ በ2ኛ ረከዐው ላይ ለተሸሁድ ይቀመጣል ማለት ነው። ሌሎቹንም በዚሁ መልኩ ይፈፅማል።
9- ሌሎች እንደሱው ያለፋቸው ሰዎች ከሌሉ ድምፅ ከፍ በሚደረግባቸው የመጀመሪያ ረከዐዎች ላይ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይቅራ። ሌሎች ያለፋቸው ኖረው ሁሉም ድምፃቸውን ከፍ ቢያደርጉ የሚረባበሹ ከሆነ ድምፁን ዝቅ አድርጎ ይቀራል።