ጉግል አዲስ “ጄሚናይ 4 አርጎን” የተሰኘ የኤአይ ሞዴል ይፋ አደረገ
ጉግል እንደ ኮዲንግ፣ ምርምር እና ጽሁፍ ያሉ ውስብስብ ስራዎችን ማከናወን የሚችል “ጄሚናይ 4 አርጎን” (Gemini 4 Argon) የተባለ አዲስ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሞዴል አስተዋውቋል። ይህ አዲስ ሞዴል በተለይም ለሳይበር ደህንነት ስራዎች የጎላ አቅም አለው።
ሞዴሉ ለተከላካይ የሳይበር ደህንነት (Defensive Cybersecurity) ስራዎች የሰለጠነ ሲሆን፤ በሶፍትዌሮች ላይ የሚታዩ ወሳኝ የደህንነት ክፍተቶችን በራሱ መለየት፣ ማረጋገጥ እና ማስተካከል እንደሚያስችል ተገልጿል።
አርጎን በተጨማሪም ለኮዲንግ እና ለሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ ስራዎች የላቀ ብቃት አካብቷል፡፡ ረጅም ቪዲዮዎችን እና ቻርቶችን ጨምሮ ምስሎችን በጥልቀት የመተንተን ከፍተኛ አቅም አለው።