ሐመር መፀሀፍ መደብር


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል ተቀላቀሉን !!!

ሀሳብ አስተያየት እና መጸሀፍ ለመጠየቅ @Hiloga_bot
ያናግሩን
ቻናል @xobya
ግሩፕ @etyolis

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


ለ ጥያቄ 👇👇👇👇

@Hiloga_bot ይጠቀሙ


signup ስታደርጉ refer code ቦታ ላይ Rf744 ያስገቡ




I have earned 150 ETB in a day. Use my refer code to earn 10 ETB on signup. My Refer Code is RF744


ምሺት ከሌለ ንጋት አይኖርም፠፠፠፠፠ ነገም ሌላ ቀን ነዉ🌟✨🌟✨


ዉብ አዳር👍


📍በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፕላን የተሳፈረ ሰውዬ የበረራ አስተናጋጇ በሰጠችው ጥቆማ መሰረት የአውሮፕላኑ መጸዳጃ ቤት ውስጥ መጠቀም ይጀምራል። ታዲያ በመሐል አንዲት ቀይ ማብሪያና ማጥፊያ የምትመስል ነገር ያይና ነካ ያደርጋታል። በዚህ ቅፅበት አውሮፕላኑ በሐይል መንገጫገጭና ወደ ጎን ማጋደል ይጀመራል። ሰውዬውም ደንግጦ ወይኔ ሳላውቅ የማይነካ ነገር ነክቼ ሕዝብ ጨረስኩኝ ብሎ በነካት ቀይ ነገር ይጸጸታል። ከጥቂት ቆይታ በኃላ ግን መንገጫገጩ ይቆምና ጨርሶ ከመጸዳጃ ቤት ይወጣል። ሁሉም ሰው "አንተ የማትረባ! ጨርሰኸን ነበር እኮ!" ብሎ ይጮህብኛል ብሎ ቢጠብቅም ዞር ብሎ ያየው ሰው እንኳን አልነበረም።

  📍መቀመጫው ላይ እንደደረሰም አጠገቡ የተቀመጠውን ሰው ቀስ እና ስቅቅ ብሎ "ይቅርታ የማይነካ ነገር ነክቼ ጨርሻቹ ነበር አይደል?" ይለዋል።  ሰውዬውም "አረ በፍጹም እንደዛ እንዳታስብ! ይህን ያሕል ጥንቃቄ የሚፈልጉ ነገሮች እኮ መፀዳጃ ቤት ውስጥ አይደረጉም ...ካፒቴኑ ያለበት ክፍል ውስጥ ነው ያሉት። በአጋጣሚ ትንሽ የአየሩ ሁኔታ አስቸጋሪ ስለሆነ ነው አውሮፕላንኑ የተንገጫገጨው" ይለዋል።

  📍ብዙ ጊዜ ሰዎች እንደዚህ ያስባሉ። የሆነች ነገር ነክተው ሕይወትህን የሚያንገጫግጩ እና መጨረሻህን የሚወስኑ ይመስላቸዋል። የረሱት ነገር ቢኖር ይህን ያክል ጥንቃቄ የሚፈልገው ነገር እነሱ አጠገብ ሳይሆን የሕይወትህ ካፒቴን ጋር እንዳለ ነው። እንደዛማ ባይሆን ኖሮ ቀይዋን ነገር እየጠቀጠቁ ሕይወታችንን መንገጫገጭ ብቻ ያደርጉት ነበር። ምስጋና ለካፒቴኑ ይሁንና እንደዚሕ አይነት ጥንቃቄ የሚፈልጉ ነገሮችን በሱ እጅ ብቻ እንዲገኙ አድርጓቸዋል።

💎ዋና ነገሬ ያለው እኔና ፈጣሪ ጋር ነው በማለት በእረፍት እንኑር፣ ሰማያዊ ጥበብ በጆሮ አይሰማም። እምነት በዓይን አይታይም።

ሁሉንም ክብርና ምስጋና የፈጠረን ይውሰድ።

📖አርምሞ

ወብ አዳር ❤️

@telemondo
@telemondo


የተወዳጁ የደራሲ ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ አዲስ መጸሀፍ ችቦ


ነገን አይተን ተመስገን የምንል ሰው ፈጣሪ ያድርገን በዚህ ሰዓት ተኝቶ በዛው የሚቀር ስንቱ አለና።

🙏 ተመስገን ሸጋ ለሊት

@telemondo


የሰው ልጅ ሀሳብ ባህር ነው ባሕርን ደሞ በዋና ማቋረጥ አይቻልም ስለዚ ባሕርን ለመሻገር የተሻለ ነገር መፍጠር ያስፈልገናል ያም መርከብ ነው። ሀሳብ ብቻ ሳይሆን ያሰብነውን የምናሳካበት መንገድ መከተል አስፈላጊ ነው ካለበለዚያ መስመጣችን ነው።

የመፍትሔ ሰው እንሁን

ሸጋ ምሽት ተመኘን

✍ፍራ

@telemondo
@telemondo


ሠላም የተከበራችሁ የሐመር ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ ከረዥም ጌዜ መጥፋት በኋላ ተመልሰናል። ቻናላችንን እንደ አዲስ ስራ ይጀምራል። በውስጥ መስመር ብዙ ሀሳብ ስታቀርቡ እና ስትጠይቁን የነበራችሁን ከልብ እናመሰግናለን🙏🙏 አብሮነታችን ከዚም በላይ ይቀጥላል እኛ ቤተሰብ ነን እስቲ አቀባበላችሁን 👍 በማድረግ አሳዩን


❤️እስቲ አፍቅሩ !

✍አሌክስ አብርሃም

💙በምድር ላይ ያልባከነ ምርጥ ጊዜ ማለት በፍቅር ያሳለፋችኋቸው ደይቃዎች ናቸው … እስቲ አፍቅሩ …መልካችሁ ምንም ይሁን አፍቅሩ …እድሚያችሁ ምንም ይሁን አፍቅሩ … ኑሮ ቢከብዳችሁ ራሱ ኑሮ ከከበደው ጋር ተፋቀሩ …ፍቅር ተያይዞ ማደግ ብቻ አይደለም ተያይዞ መውደቅም ነው ! በጥላቻና በድርቅና ከመቆም ለፍቅር መውደቅ ተለማመዱ !

💜``አገር፣ህዝብ ፣ፖለቲካ በሚል ግዙፍ ነገር ውስጥ እየዳከራችሁ የጤፍ ቅንጣት አክላችሁ አትሙቱ … ፍቅር የሚባል እጅግ ረቂቅ አየር ወደውስጥ ሳቡና አገር አክሉ ! የማታፈቅሩበት አገር ምን ያደርግላችኋል? ገብስ ልታመርቱበት ነው? …የማታፈቀሩበት ህዝብ ምን ያደርግላችኋል ቀብራችሁን እንዲያደምቅ ነው …?የማታፈቅሩበት ፖለቲካ ምን ያደርግላችኋል? ፓርላማ ልተሰየሙበት ነው? …የማታፈቅሩበት ህገ መንግስት ምን ያደርግላችኋል ሲጀመር ይልተጣመራችሁትን መገንጠል እንዲፈቅድላችሁ ነው? …

💙ተያዩ ተነጋገሩ ትዝብት ጥርጣሬ ፍርሃትን ወደዛ ጣሉና በፈገግታ በተሞላ ፊታችሁ የወደዳችኋትን ወደእናተ ሳቡ የወደድሽውን ወደራስሽ ጋብዥ ! ተቃቀፉ …አብራችሁ ቡና ጠጡ … ተደዋወሉ ‹ቴክስት› ተላላኩ ! በሚወዷችሁ ሰዎች እቅፍ ውስጥ ስጋችሁ ይድላው !ነፍሳችሁም ደስ ይበለው !ተሳሳሙ …ለመጨረሻ ጊዜ በፍቅር ከተሳማችሁ ስንት ቀን ስንት ወር ስንት ዓመት ሆናችሁ … ኪሳራ !

❤️ ህግ ስርዓትና አሉባልታ አትፍሩ …ደግሞ አትንቀዠቀዡ! ብቻ ማፍቀርም መፈቀርም ፈልጉ ..ራሳችሁን ብቻ ቀለል አድርጉት አየሩ ራሱ ወደየት እንደሚወስዳችሁ ያውቃል !…ለምርጫችሁ ብዙ መስፈርት አታስቀምጡለት ….ፈልጉ ተፈላለጉ ያለምንም ወሰን በነፍስም በስጋም ወደፍቅር ድንበር ቅረቡ ….ፀብ አትፍሩ መለያየት አያስጨንቃችሁ …ዘላለማዊ ጥላቻም ሆነ ጊዚያዊ ፍቅር ብሎ ነገር የለም ! አልፎ ሂያጅ ፍቅር የሚባል ነገር የለም ፍቅር ወደየትም አያልፍም …ፍቅር ራሱ መንገዱ ነው ! ተራመዱበት ፍጠኑበት …ብቻ አትቁሙ ! መንገድ ላይ በቆማችሁ ቁጥር ለሌላው እንቅፋት ትሆናላችሁ !

💙ማህበረሰቡ የሰከነ... ረጋ ያለ... ቁም ነገር …ሁነኛ ሰው… የማይሆን ሰው…የሚሆን ሰው… እያለ ከጫነባችሁ የጉልት ሂሳብ ውጡና እብደታችሁ በሰፈረላችሁ ልክ ከዚህ ነዝናዛ አዕምሮ ተላቃችሁ በልባችሁ ደስታ ኑሩ ! ካለፈ ታሪካችሁ ውጡ …ካለፈ ህመማችሁ አገግሙ … በዘፈን ስም ሙሾ ከሚያስወርዱ ሙዚቃዎች ራቁ ….እንዴ…! …እንዳሰባችሁና እንደተመኛችሁ እስከመቸ ትኖራላችሁ ?! ባለፈ ጥላቻችሁ ከሬዲዮና ከምናምን በተለቃቀመ የመካካድና ተጎዳሁ ተሰበርኩ ታሪክ (ያውም እንደዛም ብለው ማፍቀር ላያቆሙ) በፍርሃት ተሸማቃችሀ ትኖራላችሁ እንዴ ?!

❤️አንዳንዴማ ልብሳችሁን ጣሉ …እራቁታችሁን መኖር ተለማመዱ …እራቁታችሁን ከሆናችሁ ልብስ አይኖራችሁም… ልብስ ከሌላችሁ ኪስ አይኖራችሁም ….ኪስ ከሌላችሁ በኪስ ከሚያዙ ነገሮች ሁሉ ነፃ ናችሁ … ምንም ነገር ልትይዙ የምትችሉት ብቸኛ ነገር ልባችሁ ብቻ ይሆናል … እንደልባችሁ ኑሩ ! የነፍሶቻችሁ ባሉን ላይ የተቋጠሩ ክሮችን ከራሳችሁ የፍርሃት እጅም ይሁን ከሌሎች ሰዎች የቁጥጥር እጅ ላይ አላቁና ወደሰፊው ህዋ ልቀቋቸው በአየሩ ላይ ይንሳፈፉ !

ሸጋ ውሎ ተመኘን❤️


✍ አሌክስ አብርሃም

@telemondo
@telemondo


ስንት ነው ሚገዙኝ

አይን መነፅር ሆኖ ማንነትን ማያ
ልብስ መስፈርት ሆኖ የሰው ልጅ መለኪያ
የፀጉር ስታይል ጨዋን ሰው መለያ ሆኗቸው መሳሪያ
ከሩቁ አይተውኝ ጨዋ ነው ዱርዬ ብለው ከፈረጁኝ
ስም ከለጠፋብኝ ውስጤን ሳይረዱኝ
እኔን እንደ እንስሳ በቁም ከገመቱኝ
እስኪ ጠይቋቸው ከተመቸኝ ልሸጥ
ስንት ነው ሚገዙኝ?

✍️✍️Teddy

@telemondo
@telemondo


የደራሲ ስብሃት ገ/ እግዛብሔር አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቃ ::

" ደብዳቤዎች ከእብደት ሀገር " የተሰኘው የስብሐት መጽሐፍ ትላንት ለንባብ በቅቷል ::

ገዝቶ መኮምኮም ነው እንግዲ

#share join
@telemondo
@telemondo




#ገንዘብ:- እኔን አግኝና ሁሉንም ተዋቸው ይልሀል!
#ጊዜ:- ሁሉንም ተውና እኔን ተከተለኝ ይልሀል!
#ፍላጎትህ:- ሁሉንም ተውና ለኔ ብቻ ተጋደል ይልሀል!

#ፈጣሪ_ግን:- እኔን አስታውሰኝ ሁሉንም እሰጥሀለው ይልሀል።


ዞር ዞር ስንል ከ ማህበራዊ ሚዲያው ያገኘነው ነው ለምን ለብቻዬ አይቼው ልለፍ ብዬ ለናንተ አቀረብኩ❤️

ሰናይ ምሽት🙏


#share join
@telemondo
@xobya
@kurazs


#አንድ ስመጥር የአሜሪካን ፕሬዚዳንት በአንድ ወቅት እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል ይባላል፦

"ሃያ ስድስት ሰራዊት ስጡኝ፤ ዓለምን በቁጥጥሬ ስር አደርጋለሁ"። ፕሬዝዳንቱ 26 ወታደር/ሰራዊት ያሏቸው የሰለጠኑ በሚሌተሪ ሳይንስ የተካኑ፣ ዘመናዊ መሳሪያ የታጠቁ ሰብዓዊያን ወታደሮች ማለታቸው ሳይሆን፣ 26ቱን የእንግሊዘኛ ሆሄያት ማለታቸው ነው። እውነት ነው ፊደላት ከታጠቀ ስልጡን ወታደር ይልቅ ኀያላን ናቸው። የአሜሪካን ልዕለ ኀያልነት ከማንበብና ያነበበቡትን ከመፃፍ ጋር የተቆራኘ ነው።

("የንባብ ባህላችን በንፅፅር ሲፈተሽ" ከተሰኘ የዶ/ር ተስፋዬ ሮበሌ ፅሑፍ የተቆነጠረ)

❤️ሸጋ ቅዳሜ ተመኘን

#share join
@xobya
@telemondo
@kurazs


የጠብታ ፍንጣቂ.pdf
7.7Mb
የጠብታ ፍንጣቂ

✍✍✍ደራሲ - ጊኒቢልጣሶር ( የብዕር ስም )

📜ዘውግ - አጫጭር ልብወለዶች

የህትመት ዘመን - 1986


#share join
@telemondo
@telemondo


መምሸት እና መንጋት የተፈጥሮ ግዴታ ነው። በዛ ሒደት ውስጥ ነብስ ከስጋ እስክትለይ መኖር ደሞ የሰው ልጅ እጣፈንታ ነው። መሽቶ ሲነጋ ተመስገን እያልን ህይወታችንን መግፋት ❤️

ሰናይ ምሽት❤️

@xobya
@telemondo


ሰላም የሀመር ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ ???

እውነት ነው እየጠፋው ነው አውቃለሁ በውስጥ መስመር ሽጋ ሀሳብ እየለገሳቹኝ ነው እያበረታታቹኝ ነው ምነው ጠፋክ ያላቹም አላቹ መጸሀፍትም የምትጠይቁ አላቹ በእውነት ሁላቹንም ከልብ አመሰግናለሁ 🙏🙏🙏 እኔም ይሔን ቻናል ለብቻዬ ነው ማስተዳድረው የናንተ የሞራል ስንቅ እና ትብብር ሳይለየኝ እዚህ ደርሻለሁ ለወደፊትም ጥሩ ቤተሰብ እንደ ሚወጣን ጥርጥር የለኝም እናንተ ባታበረቱኝ እኔ ደካማ ነበርኩ ክብር ይስጥልኝ ጉዞዋችን ወደፊት ብሩህ ነው👍

እስቲ ዛሬም ከጎንክ ነን በሉኝ አብሮነታቹን አሳዩኝ የሞራል ስንቄን 💚 ይችን በመንካት


ከቡስካ_በስተጀርባ_ፍቅረማርቆስ_ደስታ_@worldbook0.pdf
7.9Mb
📗 #ከቡስካ በስተጀርባ
👤 ደራሲ:- ፍቅረማርቆስ ደስታ


#share join
@telemondo
@telemondo

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

7 432

obunachilar
Kanal statistikasi