ሂንድ ቢንት አቢ ኡመየህ አል መኽዙሚ የነቢዩ ሚስቶች ክፍል 5
👉ሂንድ ቢንት አቢ ኡመየህ ቢን አልሙጊረህ አልመኽዙሚይ እናቷ: ዓቲከህ ቢንት ዓሚር አልከናኒየህ አባቷ: አቡ ኡመየህ ሱሀይል ቢን ሙጊራህ አልመኽዙሚ የመካ ሰዎች ዛዱራኪብ/የተጓዦች ስንቅ/ ይሉታል ምክኒያቱም ከተጓዦች ጋር አብሮ ከወጣ ስንቃቸው በሱ ወጪ ስለሚያደርግ ነው፡፡
👉ክብሯ: እሷና የቀድሞው ባሏ አቡሰለማ ለዲናቸው ሲሉ ወደ ሀበሻ ከተሰደዱት ውስጥ ናቸው ከዛም የሁለተኛውን ስደት ወደ መዲናም ተሰደዋል አቡ ሰለማ የነቢዩ/ ﷺ / የአጎቱ ልጅ እና የጡት ወንድማማች ናቸው ባሏም ሲሞት ነብዩ / ﷺ / አገቧት ነብዩ / ﷺ /ጋር አብራ ከፊሉን ጅሀድ ወታለች እሷም የአማኞች ሁሉ እናት ናት።
👉መሕሯ: ከተምር ቅጠል የተሰራ ፍራሽ፡ጆክ፡ትሪ እና ጥቂት ምግብ
👉የስነ-ምግባሯ ባሕሪ:
አሏህን ተጠንቃቂ አማኝ፡ታጋይ፡ለባሏ ታዛዥ፡አርቆ አሳቢ እና ታጋሽ ናት ልጆቿ: ከነብዩ / ﷺ / ልጅ አልወለደችም ከቀድሞው ባሏ/አቡሰለማ/ የወለደቻቸው ሰለመህ፡ ዑመር፡ዘይነብ እና ሩቀየህ ናቸው እነሱም ከነብዩ / ﷺ /በሆነ እንክብካቤ ነው ያደጉት ህልፈቷ: በ ዚልቂዕዳ ወር በ59ኛው አመተ ሂጅራ ላይ አረፈች ያስተላለፈችው ሀዲስ: 378 ሀዲሶችን አስተላልፋለች።