የት ነው ያ ስፍራ ?
ሁላችንም በመንፈሱ ጠንካራ የሆነ፣ ከውሳኔዎቹ በፊት ቆም ብሎ የሚያስተውል፣ ህይወቱንም እንደ እግዚአብሔር ሀሳብ የሚመራ ጠንካራ ማንነት ያለው ሰው መሆን እንፈልጋለን ነገር ግን መፈለግ ብቻ እንጂ ያንን የምንፈልገውን አይነት ሰው መሆን ይከብደናል 😔 ይህ የሁላችንም ችግር ነው ዛሬ ያንን የምትፈልጉት አይነት ማንነት አግኝታቹ የምቶጡበትን ስፍራ እጠቁማቿለሁ ይሄ ስፍራ በግላቹ ከጌታ ጋር ህብረት የምታደርጉበት ስፍራ ነው... አዎ ብዙዎቻቹ በቤተሰብ ወይም ከጓደኞቻቹ ጋር ትፀልዩ ይሆናል ነገር ግን ከዛ ባለፈ በየግላቹ ከጌታ ጋር ህብረት የምታደርጉበት የፀሎት ሰዓት ሊኖራቹ ይገባል፤ ብቻቹን ከጌታ ጋር ህብረት የማድረጊያ ጊዜ ሲኖራቹና ያንንም ደጋግማቹ ስታደርጉት የእናንተን ሙሉ ስብዕና የሚቀይር፤ እግዚአብሔርንም ደስ የሚያሰኝ አዲስ ማንነት በዛ ህብረት ውስጥ ታገኛላቹ። ዳንኤል ትዝ ይላቹ ከሆነ በቀን ሶስት ጊዜ ከአምላኩ ጋር የግል ህብረት ነበረው በዚህም ምክንያት ዙሪያው ካሉት ጓደኞቹ ሁሉ በላይ በጥበብና በማስተዋል የጠነከረ ፣ የእግዚአብሔርም ሞገስ ያረፈበት ሰው እንደነበር መጽሐፍ ይነግረናል፤ ልክ እንዲሁ እናንተም በየቀኑ ከጌታ ጋር የግል ህብረት የሚኖራቹ ከሆነ በመንፈስ አለም ብቻ ሳይሆን በሰዎችም ዘንድ ተፅዕኖ መፍጠር የሚችል ህይወት ይኖራቿል።
@thedayofpentecost