ጌታ በደሙ ያነፃት ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ንግድ መነገድ የሚያምራቸው አገልጋይ ነን ባይሆች በጊዜ ስነ ስርዓት ብይዙ መልካም ነው፤ ይሄ የእግዚአብሔር ህዝብ መስቀል ላይ የታረደውን በግ እንዲያከብር እንጂ የእነርሱን ኪስ እንዲሞላ አልተጠራም 😡 አሁን ላይ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚሰሩ ስህተቶች ዝም ሲባሉ ቆይተው የሚመጣው ትውልድ እነኛን ስህተቶች ትክክል አድርጎ መቁጠር ቢጀምር ትውልዱ አይፈረድበትም ፤ በዚህ ዘመን ምንም ያህል እግዚአብሔር በባርያዎቹ ላይ የሚገልጠውን ፀጋ ብንቀበልም ፣ በተሰጣቸው ፀጋ በኩል ግን ገንዘብንና ክብርን ለማፍራት ሲሞክሩ አይተን ዝም ማለት የለብንም፤ በመሰረቱ ስህተት የሆነውን ነገር ስህተት ነው ብሎ ማለት አጉል ጥላቻም ሆነ ትችት አይደልም፤ ኢየሱስ በቤተ-መቅደስ ዙሪያ የሚደረጉትን ንግዶች ሲበታትናቸውና በሚደረገው ነገር ሲቆጣ የነበረው ለአባቱ ቤት ካለው ቅናት የተነሳ ነው እኛም በዚህ ዘመን የእውነት ለእግዚአብሔር ቤት ቀናተኞች ከሆንን እነኚን የእግዚአብሔርን ቤት ከወንጌል ይልቅ የንግድ ገቢያ ሊያደርጉ የሚፈልጉትን ሰዎች ዝም ማለት የለብንም።
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost