እስራኤል እና ሃማስ አራት የታጋቾች አስከሬንን በመቶዎች በሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን እስረኞች ለመለዋወጥ ከስምምነት ላይ ደረሱ፡፡
ከአንድ ወር በፊት የተጀመረው እና በርካታ መሰናክሎችን የተጋፈጠው የጋዛው የተኩስ አቁም ስምምነት በተለያዩ ዙሮች በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውን እስረኞች እና በሀማስ ስር የሚገኙ ታጋቾች እንዲለቀቁ ምክንያት ሆኗል፡፡
እስራኤል ከቅዳሜው የእስረኞች እና ተጋቾች ልውውጥ በኋላ ፍልስጤማውያን እስረኞችን የምትለቅበትን ጊዜ ማራዘሟን አስታውቃ ነበር፡፡
ቴልአቪቭ በዚህ ሳምንት እንደምትለቃቸው የሚጠበቁትን 23 ህጻናትን እና አንዲት ሴትን ጨምሮ 620 ፍልስጤማውያን እስረኞችን የመፍቻ ጊዜ ያዘገየችው፤ “ታጋቾች በሚለቀቁበት ጊዜ ሀማስ የሚያዘጋጃቸው መድረኮች የዜጎቼን ክብር የሚነኩ ናቸው” በሚል ነበር፡፡
በቀጣይ ታጋቾች በሚለቀቁበት ጊዜም መሰል የመድረክ ላይ ፕሮግራሞች እንዳይኖሩ ይህ የማይሆን ከሆነ ስምምነቱ አደጋ ላይ ሊወድቅ እንደሚችል አስጠንቅቃለች፡፡
ባለፈው ወር በጀመረው የተኩስ አቁም ስምምነት የመጀመሪያ ምዕራፍ በህይወት የሚገኙ የመጨረሻ ዙር 6 ታጋቾች ቅዳሜ ዕለት በሁለት ህዝባዊ ስነ ስርዓቶች መለቀቃቸው ይታወሳል፡፡
ሀማስ በበኩሉ እስራኤል በዚህ ሳምንት እንደምትለቃቸው የሚጠበቁትን ፍልስጤማውን እስረኞች ካልፈታች የሁለተኛው ምዕራፍ የተኩስ አቁም ድርድር የማይታሰብ ነው ብሏል፡፡
ሁለቱ ወገኖች በግብጽ አደራዳሪዎች በደረሱበት ስምምነት 620 እስረኞችን በአራት እስራኤላውያን ታጋቾች አስክሬን ዛሬ ምሽት ለመለዋወጥ ወስነዋል፡፡
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሉን Join በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ👇👇👇
https://t.me/thejamalnews