ኢትዮጵያና ሶማሊያ በሶማሊላንድ ወደብ ዙሪያ የነበረውን ውዝግብ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት መስማማታቸውን አስታዉቀዋል።
የሁለቱ አገራት መሪዎች በቱርክ አደራዳሪነት ባደረጉት ስብሰባ፣ ኢትዮጵያ በሶማሊያ ሉዓላዊነት ውስጥ በመሆን የባህር በር ለመጠቀም የሚያስችል የጋራ ተጠቃሚነት ያለው የንግድ ስምምነት ላይ ለመድረስ ተስማምተዋል።
ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሞቃዲሾን ጎብኝተው ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ ጋር ተወያይተዋል። በስብሰባው አጀንዳ ቀዳሚው የዓፍሪካ ቀንድ ደህንነት እንዲሁም ባለፈው ታኅሣሥ በአንካራ እንደተስማሙት የኢትዮጵያ ወደብ ተደራሽነት የቴክኒክ ድርድር መጀመር እንደነበር ተጠቁሟል።
የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሐመድ ዑመር አሊ እንዳስታወቁት፣ ድርድሩ ቀጥሏል፤ ግቡም እስከ ሰኔ ወር ድረስ የአሠራር ማዕቀፍ ላይ መድረስ ነው። ይህ ማዕቀፍ ኢትዮጵያ የምትጠቀምበትን ወደብየሚገኝበትን ቦታና ወጪውን ይወስናል።
ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት ፍላጎቷን በሰላማዊ መንገድ እንድታሳካ ትልቅ እድል የሚፈጥር ነው። ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ በሶማሊላንድ በኩል የባህር በር ለመጠቀምያደረገችው ጥረት ውዝግብ አስነስቶ ነበር።
አሁንግን ሁለቱ አገራትበመደራደርና በመስማማት የጋራ ጥቅምን ለማስጠበቅ ቁርጠኝነታቸውን ማሳየታቸውን ዘ ማሪታይም ኤክስኪዩቲቭ ዘግቧል ።
ኢትዮጵያ ከኤርትራ መገንጠል በኋላ የባህር በር አልባ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ የራሷን የባህር በር ለመገንባት ጥረት ስታደርግ ቆይታለች። ይህ ስምምነት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ እድገትየሚያግዝና በክልሉ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሉን Joinበማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://t.me/thejamalnews