"RELIEF የሚባል ሕገወጥ መድኃኒት እንዳትጠቀሙ" - የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን
የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን RELIEF የሚባለው መድኃኒት ህገወጥ እና በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ያልተመዘገበ፤ ጥራቱ፣ ደህንነቱና ውጤታማነቱ የማይታወቅ ነው ሲል ገልጿል።
መድኃኒቱ በውስጡ ዲክሎፌናክ፣ ፓራሲታሞል፣ ክሎረፊኒራሚን እና ማግኒዥየም ትራይሲሊኬት እንዳለው ይገመታል ያለው ባለሥልጣን መስሪያቤቱ በኢትዮጵያ ገበያ እየተዘዋወሩ መሆኑን ተደርሶበታል ብሏል።
አክሎም "ጥናቶች እንደሚያሳዩት ይህንን መድኃኒት ለረጅም ጊዜ መጠቀም ከባድ የጉበት፣ የኩላሊት ጉዳት፣ የልብ ድካም እና ስትሮክ የመያዝ እድልን ከፍ ሊያደርግ ይችላል።" ሲል ህብረተሰቡ ከመጠቀም እንዲቆጠብ አሳስቧል።
አክሎም RELIEF የተሰኘው መድኃኒት የጎንዮሽ ጉዳቶች የምግብ ፍላጎት ማጣት ፣ ተቅማጥ ፣ የሆድ ህመም ፣ ማቅለሽለሽ ፣ ማስታወክ ፣ እንቅልፍ ማጣት ፣ ድካም፤ የእይታ መዛባት፤ መፍዘዝ ፣ ራስ ምታት ፣ የቆዳ ሽፍታ ፣ የጉበት ኢንዛይሞች መጨመርና ለረጅም ጊዜ ጥቅም ላይ ሲውል የኩላሊት ጉዳትን ያጠቃልላል ሲል ባወጣው መግለጫ ገልጿል።
@TikvahethMagazine