#EEU
° "የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኖች ከመስከረም ወር ጀምሮ ያለባቸውን የኋላ ክፍያ በታህሳስ ወር በሚወጣው ቢል ላይ ተጨምሮ የሚከፍሉ ይሆናል፡፡ " የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
ከ200 ኪሎ ዋት ሰዓት በላይ የተጠቀሙ ደንበኖች የፍጆታ ሂሳብ ላይ እና አዲስ ደንበኛ ማገናኘትን ጨምሮ ደንበኞች በሚፈፅሟቸው ልዩ ልዩ የአገልግሎት ክፍያዎች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡
በዚህ መሠረት ደንበኞች ወርሃዊ የፍጆታ ሂሳብ በሚከፍሉበት ወቅት የፍጆታ መጠናቸው ከ200 ኪሎ ዋት ሰዓት በላይ ከሆነ እላፊ የመጣው የፍጆታ መጠን የተጨማሪ እሴት ታክስ ተሰልቶ ሂሳባቸው ላይ የሚደመር ይሆናል፡፡
የተጨማሪ እሴት ታክስ ተግባራዊ የሚደረገው ከህዳር ወር የክፍያ ደረሰኝ ጀምሮ ሲሆን፤ የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኖች ከመስከረም ወር ጀምሮ ያለባቸውን የኋላ ክፍያ በታህሳስ ወር በሚወጣው ቢል ላይ ተጨምሮ የሚከፍሉ ይሆናል፡፡
ዓመታዊ የቴሌቪዥን አገልግሎት ክፍያን በተመለከተ
ወርኃዊ የኤሌክትሪክ የፍጆታ መጠናቸው ከ50 ኪሎ ዋት ስዓት በላይ የሆኑ ደንበኞች 10 ብር ከወርሃዊ ኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ጋር የቴሌቪዥን አገልግሎት ክፍያ እየከፈሉ ይገኛሉ ብሏል።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቲቪ) ዓመታዊ የቴሌቪዥን አገልግሎት ክፍያ የመሰብሰብ መብት የተሰጠው ሲሆን ሁለቱ ተቋማት ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያ ስርዓትን በመጠቀም በየወሩ እንዲሰበሰብ ህዳር 2 ቀን 2015 ዓ.ም ስምምነት ማድረጋቸው ይታወሳል።
@tikvahethmagazine