#AddisAbaba
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 በሻሌ 72 አካባቢ በሚገኝ የግል ባንክ ውስጥ የሚሰራ የደንበኞች አገልግሎት ሰራተኛ ከደንበኞች አካውንት በመቀነስ ለግል ጥቅሙ አውሏል ተብሎ በቁጥጥር ስር ውሏል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ እንዳስታወቀው ግለሰቡ በቁጥጥር ስር እስከዋለበት ቀን ድረስ ከ5 የባንኩ ደንበኞች ከ2መቶ 78ሺህ ብር በላይ ወደ ግሉ አስተላልፏል።
ተከሳሹ ድርጊቱን መፈጸሙን ያመነ ሲሆን ከሂሳብ ወደ ሂሳብ እና በሞባይል ባንኪንግ በማስተላለፍ የወሰደ መሆኑም በምርመራ መረጋገጡን ፖሊስ አስታውቋል።
በተጨማሪም የኃላፊዎቹን አለመኖር በመጠቀም ለደንበኞች መልዕክት እንዳይደርስ ሲስተም ላይ የራሱን ስልክ ቁጥር በማስገባት በፈፀመው ወንጀል ክስ እንደተመሰረተበትም ተገልጿል።
ተጠርጣሪው እንዴት በቁጥጥር ስር ዋለ?
የአንደኛ የግል ተበዳይ ለወላጅ አባታቸው በባንክ ቤቱ በአካል ቀርበው ገንዘብ አስተላልፈው ሊሄዱ ሲሉ ስልኮትን ይስጡኝ ሞባይል ባንኪንግ እንዲጠቀሙ ላስተካክል በማለት ይቀበላቸዋል።
ለኃላፊው የግል ተበዳይ የስልክ ቁጥር መቀየራቸውን ዋሽቶ በመግለፅ አዲስ ስልክ ላይ መልዕክት እንዲደርሳቸው ጠይቀውኛል በማለት ኃላፊውን በማታለል የራሱን ስልክ አስገብቶ ያስተካክላል።
ከዚያም ከ35ሺህ ብር በላይ ወደ ግል ሂሳቡ ያስተላልፋል። የግል ተበዳይ ይህንን ጉዳይ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄደው በማመልከታቸው በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል። ተጠርጣሪው በዚህ መልኩ የሌሎች ተበዳዮችን ስልክ በመቀየር ወንጀሉን መፈጸሙን የፖሊስ መረጃ ያሳያል።
ፖሊስ በመልዕክቱ ህብረተሰቡ የባንክ ሂሳቡን ሲያንቀሳቅስ በስልኩ ላይ ምንም ዓይነት መልዕክት ካልደረሰው በአካል ወደ ባንኩ ቀርቦ ሊያመለክት እንደሚገባ አስተላልፏል።
@tikvahethmagazine