በኮንጎ በዋና ከተማዋ ባጋጠመ ጎርፍ የ33 ሰዎች ህይወት አልፏል።
በኮንጎ ዋና ከተማ ኪንሻሳ በዘነበው ከባድ ዝናብ ባጋጠመ የጎርፍ አደጋ በትንሹ 33 ሰዎች መሞታቸውና በአብዛኛዋ የከተማዋ አካባቢዎችም የግንኙነት መስመሮች መቋረጣቸው ተነግሯል።
ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪ 46 ሰዎች ወደ ሆስፒታል ሲገቡ፤ 75 ቤተሰቦች ከቤታቸው ውጪ ተወስደው በስታዲየም እንዲቆዩ ተደርጓል።
አብዛኛው ሰው የሞተው በቤቶች መፈራረስ ምክንያት መሆኑን የከተማዋ የጤና ባለሙያዎች የተናገሩ ሲሆን ወደ ኤርፖርቱ የሚወስደው መንገድ በጎርፍ መዘጋቱንና ከ72 ሰዓታት በኋላ ለሁሉም አገልግሎቶች ክፍት እንደሚሆን የኪንሻሳ አስተዳዳሪ ተናግረዋል።
የተዘጋው መንገድ የኮንጎን ትልቁን ከተማ ከተቀሩት የሃገሪቱ ከተሞች ጋርም የሚያገናኝ በመሆኑ ንግዱን እንዳያቀዘቅዝ ተሰግቷል።
በ2022 በተመሳሳይ በከተማዋ ባጋጠመ የጎርፍ አደጋ የ100 ሰዎች ህይወት አልፎ የነበረ ሲሆን የተለያዩ የሲቪል ድርጅቶች የከተማዋ ከንቲባ ከሃላፊነታቸው እንዲለቁ ጠይቀዋል።
የከተማዋ አስተዳዳሪዎች ግን በጎርፉ ቤቶች የፈረሱት በከተማ ፕላኒንግ ደረጃቸውን ጠብቀው ስላልተሰሩ ነው ብለዋል።
Source: AP, XINHUA
@Tikvahethmagazine @tikvahmagbot