የሀገራት አማካኝ የቀን ገቢ ስንት ነው ?
የተለያዩ ሃገራት ዜጎች ከጊዜ ወደጊዜ የሚያገኙት ገቢ ከኑሮ ውድነቱ ጋር እየተጣጣመ አይደለም። በአብዛኛው ሃገራት በተለይ እያደጉ ባሉ ሃገራት የዜጎች የቀን ገቢ በጣም አነስተኛ ስለሆነ ዜጎች ለመኖር ሲፈተኑ ይታያል።
በሀገራችን ኢትዮጵያ በ2023 በነበረ ቁጥራዊ አኀዝ ግማሽ ያህሉ ህዝብ በቀን ከ3.06 ዶላር በታች ባለው ገቢ የሚኖር ሲሆን 19.54% ያህሉ ህዝብ ደግሞ በቀን ከ1.9 ዶላር በታች ያገኛል።
በተጨማሪ UNDP በ2024 ባወጣው ሪፖርቱ በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ከድህነት ወለል በታች የሚኖር ወይም በቀን ከ2.15 ዶላር በታች ገቢ የሚያገኝ ነው።
ይህ አነስተኛ ገቢ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ታዳጊ ሃገራትም የሚታይ መሰረታዊ ችግር ነው።
በጎረቤት ሃገር ኬንያ በተመሳሳይ መረጃ በ2023 ግማሽ ያህሉ ህዝብ በቀን ከ3.1 ዶላር በታች የሆነ ገቢ ሲያገኝ 31.25% በመቶ ያህሉ ህዝቧ በቀን ከ1.9 ዶላር በታች ያገኛል።
በUNDP የ2024 ሪፖርት መሰረት ደግሞ ኬንያ 36.1 በመቶ ያህል ዜጎቿ በቀን ከ2.15 ዶላር በታች የሚያገኙ ወይም ከድህነት ወለል በታች የሚኖሩ ናቸው።
ግብፅ በ2023 በወጣው መረጃ ግማሽ ያህሉ ህዝቧ በቀን ከ5.07 ዶላር በታች የሚያገኝ ሲሆን በUNDP የ2024 ሪፖርት መሰረት 1.5 በመቶ የሚሆነው ህዝቧ በቀን ከ2.15 ዶላር በታች ያገኛል።
እንደ ሉግዘምበርግ ባሉ ያደጉ ሃገራት ይህ የቀን ገቢ ተገላቢጦሽ ነው። በሉዘምበርግ ግማሽ ያህሉ ህዝብ ከ69.48 ዶላር በታች ገቢ በቀን ያገኛል።
በሉግዘምበርግ በቀን ከ1.9 ዶላር በታች የሚያገኘው 0.28% የሚሆነው ህዝብ ብቻ ነው።
እነኚህ ቁጥሮች በታዳጊ ሃገራት ያሉ ዜጎች የሚኖሩትን ኑሮ መደምደሚያ ባይሆኑም አመላካች ሲሆኑ ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ለውጦች ተደርገው የዜጎች ኑሮ መሻሻል እንዳለበት የሚያሳዩ ናቸው።
Source: UNDP, WISE VOTER
@tikvahethmagazine