ቶጳዝዮን


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Inglizcha
Toifa: Kitoblar


"ቶጳዝዮን"ማለት ቢጫ የከበረ ድንጋይ ፣ዕንቍ ማለት ነው። በተስፋ የተቃኘዉን ሀሳባችንን እና ስሜቶቻችንን በዕንቊ ቃላቶች እያዋዛን በብዕራችን የምንገልፅበት ምርጥ ቻናል ነው።
ለማንኛውም አስተያየት👇👇
@Ediwub
@Tirrubel

Bog‘liq kanallar  |  O‘xshash kanallar

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Inglizcha
Statistika
Postlar filtri


ያመሻሽ ስንኞች
(በእውቀቱ ስዩም)

በቀዝቃዛ ጎጆ፤  በደብዛዛ ኩራዝ
እንባ እያጣቀስኩኝ ፤ በምገልጠው ጥራዝ፤
ኑሮየን ባጠናው፤ ፍቺው አይገለጥ
ሊቅ ሆኘ ተፈጠርሁ፤ በቂል ለመበለጥ፤

“””””
እሳቴን አንድጄ
ጭራሮ ማግጄ
ሰታቴየን ጥጄ
ሺ ጊዜ ባማስል፣ ራት አላበሰልሁ
እኔ ከማገዶው፤ ቀድሜ እየከሰልሁ፤

Bewketu seyom
@topazionnn


ዛሬ ተፀፅተሽ በእንባ እንደነገርሺኝ፣
ሰይጣን አሳስቶሽ ከሆነ የተውሺኝ

እኔን እንድትከጂ ላሳሳተሽ ሰይጣን፣
ለውለታው ምላሽ ላጭስለት እጣን።

By endelibu
@topazionnn

654 0 11 1 19

.................... ትሑት ጎበዝ ደራሲ ናት። ወደ አመሻሽ ጀምበር ስታዘቀዝቅ ማየት እጅጉን ያስደስታታል።
ከአንዱ ዛፍ ጥላ ስር ተቀምጣ ሰማይ ሰማዩን እየተመለከተች  ብዙ ሀሳቦችን ስታወጣና ስታወርድ ትቆያለች....ወረቀት እና ብዕሯን ይዛ ትብሰለሰላለች.....አንዳንድ ጊዜ ፈገግ ትላለች ....ሌላ ጊዜ ደግሞ ትክዝ ብላ አይኖቿ በእንባ ይሞላሉ።
ልክ እንደ ገፀባሕሪዎቿ ስሜት የእርሷም ስሜት ይቀያየራል።
የምናቧን ከሰዉ ልብ ማስረፅ ትችልበታለች።ራሷን በድርሰቶቿ ዉስጥ ለመደበቅ የምትጥር ደራሲ ነች።

.....የቀጠረችዉ ሰዉ ያለ ይመስል በየደቂቃዉ የእጅ ሰአቷን ታያለች ስልኳንም አልፎ አልፎ እያነሳች ትመለከታለች።ትክ ብሎ ላስተዋላት ትልቅ እንግዳ የምትጠባበቅ እንጂ የ ዳግምን የፅሑፍ መልእክት የምትጠብቅ አትመስልም.........

..........ከተቀመጠችበት እመር ብላ ተነስታ ወረቀቶቿን ሸካክፋ ወደቤቷ ጉዞዋን ጀመረች።በመንገድ ላይ ሳለች ስልኳን አይታ ፈገግ አለች.... "ይቅርታ ትሑቴ" ይላል....የዳግም መልእክት ነበር...........

ትሑት እና ዳግም የአንድ እዉቅ ደራሲ መፅሐፍ ምርቃት ላይ ነዉ የተዋወቁት።ሁለት አመታትን በትዉዉቅ አስቆጥረዋል። ዳግም ጥሩ የስነፅሑፍ ወዳጅ ነበረና እርሷ በምትገኝበት መድረኮች ሁሉ አብሯት ይገኛል። ከእለት ወደ እለት  የምታነሳቸዉ ሀሳቦች ጥልቅነት እየተገረመ.....በስብዕናዋም እጅግ እየተማረከ መጣ።

....ሐሳባቸዉን ሳይለዋወጡ ዉለዉ አያድሩም የሷ መልእክት ሲደርሰዉ እንደ ህፃን ልጅ ይቦርቃል።ትሑትም ሳይደዉል ሲቀር ጭንቅ ይላት ጀምሯል።መስታወት ፊት ቆማ ራሷን እየመለከተች "ምን እየሆንሽ ነዉ ? ትሑት" ትልና ፈገግ ትላለች........

ከማንም አብልጦ ይወዳታል ግን አልነገራትም...........ባይነግራትም መዉደዱን ታዉቃለች......በመፈለግ እና ባለመፈለግ ዉስጥ በመሐል ቤት ሆና ዝምታን መርጣለች።

............................................
✍ዔደን ታደሰ
@Ediwub
@topazionnn
@topazionnn


# ኤፍሬም_ስዩም እንደፃፈው
# ኑ_ግድግዳ_እናፍርስ_2008

# የማርያም_ንግስ_እለት ።
.
አዳፋ ነጠላ በቀጠነ ገላ ፥ ነፋስ የሚጥለው
የነተበ ጫማ. ጥቁር ያዘን ቀሚስ ፥ ኑሮ ያጨቀየው
ለብሳ የተገኘች .........
ከቤተክርስቲያን አፀድ ፥ ቆማ ከዋርካ ስር
አንዲት ምስኪን ባልቴት .....ትለማመን ነበር
,
አደራሽን ማርያም
አደራሽን ማርያም
እበላው የለኝ መሶቤ ተራቁቷል
እለብሰው የለኝም ጀርባዬ በርዶታል።
,
ወድቃ እየተነሳች
እምባ እያፈሰሰች
ተስፋዋ ማርያምን ትለማመን ነበር
ከቤተክርስቲያን ጓሮ ቆማ ከዋርካ ስር።
,
የደብሩ አለቃ
ካባ ላንቃ ለብሶ ምጣህቱን ደርቦ
ልክ የሌለው ቦርጩ ወደፊት ተስቦ
የንግሱን ምዕመን ወደፊቱ ስቦ
ጮክ ብሎ ያወራል
ጮክ ብሎ ያስተምራል።
,
1
የመቅደሱ ቀለም ሊታደስ ይገባል
2
የካህናት ደመወዝ ሊጨመር ግድ ይላል
3
ደጀ ሠላም ወንበር እጅጉን ያንሰናል ......
.
እናም.......
በዚህ ታላቅ ደብር ይህ ችግር ስላለ
ለማርያም የሚሆን እጃቹ የት - አለ?
እያለ።.....
ህዝቡን ያስተምራል
ህዝቡን ይደልላል።......
ለንግሱ የመጡ.....
ባለ ብዙ ብሮች
ብዙ ባለጠጎች....
ጥለት የለበሱ ፥ በሽቶ የራሱ
ቆመው የነበሩ....እፊት ከመቅደሱ
ቀለም እንዲቀባ እንዲታደስ ደብሩ
ለደጀ ሠላሙ ደግሞም ለወንበሩ
በሺ .....የሚቆጠሩ
ብሮች ወረወሩ....
.
የደብሩ አለቃ ግንባር በጣም ውዛ
የሚወረወረው ብሩም በጣም በዛ።
.
የዛች የምስኪን ነፍስ
ያች ታላቅ መቅደስ
ቆማ ከዋርካ ስር
ተስፋዋ ማርያምን ትለማመን ነበር::
,
ኣዠአደራሽን ማርያም
አደራሽን ማርያም
እበላው የለኝም መሶቤ ተራቁቷል
እጠጣው የለኝም ማድጋዬ ጎድሏል
እለብሰው የለኝም ጀርባዬ በርዶታል
አንቺ ነሽ ተስፋዬ የኔስ ተስፋ ሞቷል
ወድቃ እየተነሳች
እምባ እያፈሰሰች።
,
,
ግና ግን ለዛሬ ፥ ለክብርሽ እንዲሆን
ተቀበይ ስጦታ ውሰጂ አምኃዬን
የሟች ባሌን ማስታወሻ የአንገት ሃብሌን::

@topazionnn
@topazionnn


እንደ ጣይ የበራም
ይጨልማል ላምባ
ሲስቅ የኖረ ሰው
ይቀበራል በእምባ።

ከልብ የገዘፈም፡
ከነፍስ የቀዘፈም
አድጎ፣ ወልዶ፣ ከብዶ፥
አዎን አይቻለው
እንደሚሆን ባዶ።

አልጠፋኝም እኮ:
ሰላም ነሳኝ እንጂ

ያልኖረችው ምኞት፣
ያልነካችው ተስፋ፣
ያለፋት ልጅነት፣
   .. ህሊናዬን ታኮ፤
"ኖራ ሞታ" ቢሆን
አይቆጨኝም እኮ።

#mikiyas_feyisa
@topazionnn


እንበልና!!

ዛሬ ዓለም ተጀመረ፣
እንደገና
ሰማይና ምድር ተፈጠረ፣

እንበልና....

«ብርሃን ይሁን!» ተባለ፣
ወገገን በሸጥ ተሳለ፣
ጨለማ ተርመሰመሰ፣
ከዋክብት ለጉድ ታመሰ፣

እንበልና...

መላእክትም በአክናፍ መጡ፣
አዳምና የአዳም ዘሮች ተቀመጡ፣
ብንል....
ይለይ እርጉሙ ከተከበረ፣
ሳጥናኤል ብፁዕ ነበረ፣

ድሮ ድሮ ድሮ....

ቅዱሱ መልአክ
በጥፍር ታክል ክፋት ሰይጣን የተባለው፣
እንደኔና እናንተ
ሰው የተባለው ሰው ስለሌለ እኮ ነው።

by ገ/ግጥም አየነው


https://t.me/eliyasshitahun/4055



ተሳተፉ ፍላጎቱ ያላችሁ❤️‍🔥🤝


ከብዙ ብዙ ነገር በኋላ

ከአመታት በኋላም  ስታገኙት በመሳቀቅ
                    :
" አወቅከኝ ግን ? "  ተብሎ የማይጠየቅ ...


የሚያውቃችሁ
          :
የሚያውቅላችሁ!

✨ ኢየሱስ ክርስቶስ !


(ኤልያስ ሽታሁን)

@topazionnn
@topazionnn


#በራ_የመስቀል_ደመራ

የአደይ ችቦ እየፋመ እየጋመ
ኢዮሃ እያስገመገመ እየተመመ
የመስቀል ደመራ
በራ።
በራ የአዲስ ዘመን ችቦ
በመስከረም ላብል እብቦ
ከዋከብቱን ፈነጠቀ
ርችቱን አንጸባረቀ
ተኳለ አዲስ ደመቀ
መለኩን በቀለም እዝርእት በጥበብ አጥለቀለቀ
ሸለቆው ተንቆጠቆጠ፥ ተራራው አሸበረቀ
ኢዮሃ ኢዮሃ አበባዬ! ምድር ሕይወት አፈለቀ።
ነጋ፥ የእዲስ ዘመን ችቦ
ፈካ፥ ፀደይ አርብቦ
ሌሊቱ እንደጎሕ ቀደደ፥ ጨለማው እንደ ቀን ጠራ
እንደውቅያኖስ ዕፅዋት  እንደጠፈር ኮከብ ደራ
ምድር ሥጋጃ ለበሰ፥ የጌጥ አልባሳት ተቀባ
ሰማይ በእልልታ እስተጋባ
እዮሃ መስከረም ጠባ።
ነጋ የአዲስ ዘመን ችቦ፥ ምድር ሕይወት አፈለቀች
የምሥራች እዝርእቷን፥አዲስ ቡቃያ ወለደች
የአደይ አበባን ለገሠች
ለአዲስ ዘመን አዲስ ብርሃን፥ አዲስ መስከረም ገበየች።
ነጋ፥ የአዲስ ዘመን ችቦ
ፈካ፡ ፀደይ እረብቦ
በራ፥
የመስቀል ደመራ።

መስከረም - ፲፱፻፳፫ - መስቀል አደባባይ

ፀጋዬ ገብረመድህን

@topazionnn
@topazionnn


ዕቡህ_ብዕር dan repost
በብላቴና ላይ አምላክ ተገለጠ
‎ሟች የተባለው ነፍስ ከሞት አመለጠ
‎በመከራው ሁሉ ሰሪዋ አልተዋትም
‎ያድነኛል አለች አላሳፈራትም !

ማዕዶትዬ ከነበረባት Cancer ድናለች 🥹
አያቹ ግን አይደል የእግዚአብሔርን ስራ ! አያቹ አይደል ግን በምንም ውስጥ ብንሆን እንደማይተወን....እግዚአብሔር ይመስገን.

አማልጅኝ ያለቻት ማርያም አቀፈቻት
በሰው ማይቻለውን እርሷ አሻገረቻት
✨

ያመነችው አምላክ አላሳፈራትም

ከዚህ በላይ ምናገርበት ቃል የለኝም.....ንጉሥ ይዘን ለባሪያ አንስገድ ሊያድነን የታመነው ከበራችን ነው ✨

[ ጥሩቤል ]

@ebuhbhr
@ebuhbhr
@tirrubel


ዕቡህ_ብዕር dan repost
አይበጀኝም ብዬ የጥፍሬ ገፅታ
ምላጭ አስታትኬ የቆረጥኩት ለታ
ገላባ ያልኩት ሲወድቅ ቁልቁል ከመሬቱ
ስንቅ አገኘን ብለው ጉንዳኖች ዘመቱ
አወይ ዓለም አጃይብ ተፈጥሮ
ለአንዱ አረባው ያለው ለሌላው ነው ኑሮ
!

[ ጥሩቤል ]

@ebuhbhr
@ebuhbhr
@tirrubel




ቀስ በቀስ
እንደ ሳቅ ፈገግታ
እንደ ጧት ወገግታ
ቀስ በቀስ
እንደ ሕይወት ዳና
እንደ ትላንትና
ቀስ በቀስ
እንደ ራስ ቅል ጠጉር
እንደ ቆዳ ብጉር
ቀስ በቀስ
ተንሸራትቶ መምጣት
ሀገር ወደ ማጣት ።

____
©️ ሄኖክ በቀለ
@topazionnn
@topazionnn


.......
እነሱ፡
ምድርን ቢሸፍኑ
በኒውክለር ሚሳኤል፣
ለእኛ፡
በክንፉ ሚከልል
አለልን ሚካኤል፤

እነሱ፡
በጊዜ ቢመኩ
ቢይዙ ምንሽር፣
ለእኛ፡
ማርያም ከጎን አለች
ጉልበትን የምትሽር፤

እነሱ፡
ምስኪንን ለማራድ
ቢያነግቱ መውዜር፣
ለእኛ፡
አልፋና ኦሜጋ
አለልን አንድ እግዜር፤

እምነት አለን እኛ ከአለት የበረታ
ጎልያድን ሞገድ በጠጠር ምንረታ
በምድራዊ ፍቃድ ሀሰት ብታይልም
እመኑኝ 'ላመኑት' አምላክ ዝም አይልም!

@Weyblann ያቡ✍


በህመሙ ብዛት
በመከራው ብዛት
በሀዘኑ ብዛት

እያለ በቁሙ ዕድሜ እንዳያጥረው
                      :
የሰውን ልጅ እግዜር "ከመርሳት" ፈጠረው !

(ኤልያስ ሽታኹን)
@topazionnn
@topazionnn


ዕቡህ_ብዕር dan repost
#ፀፀት_ያንባት

የ 2019 የመጀመሪያ ግጥሜ ነው ✨
ልብ የፃፈው ግጥም ነው....
.
Inspired By True Story
የተኖረ ፣ እየተኖረ ያለ ፣ የሚኖር


.
ስለ ፆታዊ ፍቅር አይደለም
.
[ ጥሩቤል ]

@ebuhbhr
@ebuhbhr
@tirrubel


(የታመመ እንጠይቅ..)
==============

እውነትና ንጋት
እንዲህ ከልብ ሲርቅ
አምርሮ ጠያቂን
መ..ምህሩ ሲያ'ንቅ
የሰውነት አፍላግ
ከምንጩ ሲደ'ርቅ
ማን በጤናው ሊገኝ
ኑ ቢያመንም እንኳ...የታመመ እንጠይቅ  !

By #kiyorna

@topazionnn
@topazionnn


በር እና ስንቀር
--------------------------------

የፍላጎት ቤቱ፤ የምኞት ማደሪያው
እያደር ሲለጠጥ' ግድግዳና ጣሪያው
ኗሪው ገላው ሰፋ፤ ጎጆውም ገዘፈ
ለበር የታሰበው፤ ሽንቁር ኾኖ ዐረፈ።

By bewuketu siyum
@topazionnn
@topazionnn


አዲስ አመት
.
.
ያ...ጠቢብ ሰለሞን..........
ያማረ ቀለበት ከእጅሽ ያጠለቀዉ፤
ምን ያክል ዉበትሽ ልቡን ቢገዛዉ ነው?

ከአደይቷ ይልቅ ደምቀሽ ብትታይዉ፤
ሽንፈት የማያዉቀዉ ፍቅርሽ አሸነፈው።

ትዋቢበት ዘንዳ ዉብ እንቁን ለጣትሽ፤
ችግር ሲያገኝሽ ማለፊያ ለጣጣሽ፤
አንድም ለልብሽ ነዉ ማሰሪያ ለቃልሽ፤
ለቅድስቷ ምድር አንድም ለሀገርሽ።

የካም እድል ፈንታ እንቁ ዕጣ ለወጣች፤
ጸሎቷን ለማድረስ እጇን ለዘረጋች፤

ህመምሽ ለሆነች ፈዋሽሽም እሷዉ፤
ለቅድስቷ ምድር አንድም ለሀገርሽ ነው።

ዛሬም ለሀገሬ........
መከራ እንደ ሀምሌ ፀንቶ ላጨገጋት፤
ዉሽንፍር መባርቅት አብሮ ለሚንጣት፤

ቀለበትሽን አዉሻትና........
መከራዋ ያብቃ ነጭ ልብስ ትልበስ፤
ተስፋዋ ይለምልም በፍቅር ትታደስ፤
እንባዋ ታብሶ ብርሃን ይታያት፤
በዚ በአዲስ አመት ደግ ቀን ይዉጣላት።

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
✍✍ዔደን
@ediwub
@topazionnn
@topazionnn


​​➛➛እመ መከራ➛➛

ኢትዮጵያ እመ መከራ
የግዜር መመራመሪያው
የስቃይ ቤተ-ሙከራ
መውደቅማ ነበር ያባት
እንደ ያሬድ እስከ ሰባት
እንደ በላ ብላቴና
የእንክርዳድ ሙልሙል እንጎቻ
የትውልዴ እጣ ፈንታ
መውደቅ፣መውደቅ፣መውደቅ ብቻ!

✍ገጣሚ ፦ በእውቀቱ ስዩም
@topazionnn
@topazionnn

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.