📢
ውጤታማ የአጠናን ዘዴ------------------------------------------------
➡️ በትምህርት ህይወታችን ስኬታማ መሆን ከፈለግን በመጀመሪያ ለምንማረው ትምህርት
ፍቅርና ፍላጎት እንዲኖረን ማድረግ አለብን።
➡️ ለመምህራን ያለን አመለካከትም አዎንታዊ መሆን ይገባል።
➡️ እነዚህን ሁለት ቁልፍ ነገሮች በትክክል ከተገበርን በትምህርታችን ውጤታማ የመሆን ሚስጥርን የመጀመሪያ ምዕራፍ አወቅን ማለት ነው።❗️
➡️ ምክንያቱም በትምህርት ላይ ፍላጎት ካሳደርንና መምህራንን የምንወድ ከሆነ ትምህርቱን ከልብ ለመከታተልና ያልገባንን ጠይቀን ለመረዳት ወኔ ይኖረናል። ✊🏾
➡️ ሌላው መሰረታዊ ነገር ክፍል ውስጥ የሚሰጠውን ትምህርት በሚገባ በማስታወሻ ይዞ ከልብ መከታተል ነው።
➡️ ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ካልሆነ በስተቀር ከክፍል ፈጽሞ መቅረት
የለብንም።
➡️ በተደጋጋሚ ከክፍል የምንቀር ከሆነ የሚሰጠው ትምህርት ተከታታይነትና ተያያዥነት ያለው ስለሚሆን ቀጣዩን ርዕስ ለመረዳትና አብሮ ለመሄድ ያስቸግረናል።
➡️ እንደዚሁም ይኸው በተደጋጋሚ ከትምህርት ገበታ የመቅረት ጉዳይ በመምህራን ዘንድ ከታወቀ መጥፎ አመለካከት በራሳችን ላይ እንዲፈጠር እናደርጋለን። ይህም ደግሞ
ከመምህራን ጋር እንዲኖረን የምንፈልገውን መልካም ግንኙነት ያሻክርብናል። እንዲህ ከሆነ
ደግሞ ትምህርቱን እየጠላነው እንመጣና መጨረሻ ላይ ግድ የለሽ መሆን እንጀምራለን። ይህም የውድቀታችን የመጀመሪያ ምዕራፍ ይሆናል። ❗️
➡️ ቀጣዩ ስራችን የተለያዩ ማጣቀሻ መጽሐፍት መፈለግና ማንበብ ይኖርብናል። መምህራን ከሚሰጡን ትምህርት ጋር እያዋሃድን የምናዘጋጀው ሰፋ ያለ ግን ደግሞ ቅደም ተከተሉን
የጠበቀ፣ ግልጽና ያልተንዛዛ፣ ዋና ዋና ፍሬ ሃሳቡን ብቻ የያዘ፣ የራሳችን ማስታወሻ ሊኖረን ይገባል። ✅
➡️ ማስታወሻ ማዘጋጀት ባይሆንልን ደግሞ፣ ማስታወሻ በጥንቃቄ የመያዝና ያነበቡትን ነገር ነጥብ በነጥብ የማስቀመጥ ችሎታ ካላቸው ተማሪዎች ልምድ መቅሰም አለብን፤ እንዲረዱንም መጠየቅ ይኖርብናል። አንዳንድ ተማሪዎች በዚህ የተካኑ ናቸው። ማስታወሻ ሲይዙ አጥንቱን ከስጋው ለይተው፣ ግሳንግሱንና የማያስፈልገውን አበጥረው፣ እጥር-ምጥን ያለ፣ መተው የሌለበትን ፍሬ ነገር ብቻ የያዘ፣ እጅግ ምርጥ ማስታወሻ ያዘጋጃሉ።👏🏾
ከነዚህ ተማሪዎች ልምድ መቅሰም ብልህነት ነው። 👌🏽
➡️ በመጨረሻም የመምህሩን የማስተማር ስልት፣ የትኩረት አቅጣጫውን፣ የፈተና አወጣጥ ዝንባሌውን የመገመት ብቃት ልናዳብር ይገባል።
➡️ የፈተና አወጣጥ ዝንባሌውን በማጥናት፣ የት ላይ የበለጠ ትኩረት መስጠት እንደሚፈልግ መገንዘብ ያስፈልጋል። ራሳችንን ለዕውቀትና ለፈተና ስናዘጋጅ እነዚህን ነገሮች ሁሉ ታሳቢ ማድረግ አለብን። ይህን ከግምት
ውስጥ አስገብተን የምንጓዝ ከሆነ ስኬት በእጃችን ነች። ጊዜያችን በከንቱ አይባክንም። በአጭር ጊዜ ውስጥ በበቂ ሁኔታ አጥንተን ብዙ ሳንደክም ውጤታማ እንሆናለን።
➡️ ሁልጊዜ የህይወታችን መርህ “አስተውሎ የሚራመድ ረጅም መንገድ ይጓዛል፡” የሚል ይሁን።
"... እነዚህን ቁልፍ ሀሳቦች ተረድታችሁ ከተገበራችኋቸው ጎበዝ የማትሆኑበት ምንም ምክንያት የለም!❌
▪️
ልዩ እገዛ የሚያገኙበት ገፅ 👇👇
JOIN: @FRESHMAN_2019JOIN: @TOPSTUDENTS1
------------------------------------------