ስለ ገድላት ማስተዋል የሚሹ ጉዳዮች
--
#አስፈላጊነታቸው፡- ለድርድር አይቀርብም፡፡ የክርስትና ሕይወት በሞት አይቋረጥም ለሚለው አቋማችን ምስክሮች ናቸው፡፡ በአስፈላጊነታቸው ላይ የሚሰጥ የማርያም መንገድ የለም፡፡ ገድላት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን የተቀደሱ የአገልግሎትና የጸሎት መጻሕፍት መካከል ናቸው፡፡
#ይዘታቸው፡- የገድልት ይዘት ‹‹ገድል›› ነው፡፡ በጠባዩ የሃይማኖት መግለጫ፣ የታሪክ ሰነድ፣ ግለታሪክ፣ የሕይወት ታሪክ፣ ቀኖናዊ መጽሐፍ (መጽሐፍ ቅዱስ)፣ ወዘተ. አይደለም፡፡ ገድል ነው! ገድል አንድ የቤተ ክርስቲያን የሥነ ጽሑፍ ክፍል ነው፡፡ መነበብም ሆነ መመዘን ያለበት፣ መቃናትና መታረምም ያለበት፣ መጠናትም ያለበት በዚያ መንገድና ዐውድ ነው፡፡
#ፈራጁን_ጠርጥሩ፡- ገድላት ከሥነ ጽሑፍና ከቅጂ አንጻር ውጫዊ የሆነ ጥናት በፊሊዮሎጂ ይጠናሉ፡፡ በነገ መለኮት ኮሌጆች ግን የሚገባውን ያህል እየተጠኑ አይመስለኝም፡፡ በጉባኤ ቤት ውስን ድርሳናት እንደየአጥቢያው በተማሪው ይነበባሉ፡፡ ገድል ሕይወት በተግባር የተተረጐመበትን ታሪክ ስለያዘ እንደ ገቢራዊ ማሳያ ይጠቀሳል፡፡ መጥቀስና ማጥናት ተቀራራቢ አይደሉም፡፡ ዳኝነት ለመስጠት አያበቁም፡፡ ስለዚህ ገድላት ላይ ከውስጥም ቢሆን የሚሰጡ አስተያየቶች በተገቢው ንባብና ጥናት መመርኮዛቸው ላይ ጥርጣሬ አለን፡፡ ትልልቆቹ የሀገራችን የጥናት ሰዎች እነ ፕ/ር ጌታቸው፣ ፕ/ር ታደሰ፣ ከውጪም ስቴፈን ካፕላንና የመሳሰሉ አጥኚዎች ገድላትን በስፋት አጥንተዋል፡ ጥናታቸው ግን በሃይማኖት ዐይን አይደለም፡፡ በታሪክና በሥነ ድርሳን መነጽር ነው፡፡ በእነሱ መነጽር ገድላትን እንዲህ ናቸው ማለት ሃይማኖትን በታሪክና በሥነ ድርሳን ሕግጋት መዳኘት ይሆናል፡፡ በአጭሩ ገድላት ተገቢውን ኦርቶዶክሳዊ የጥናት ዐይን ይፈልጋሉ፡፡ በዚህ ረገድ ቀሲ ዶ/ር አምሳሉ ተፈራ (የነቅዐ መጻሕፍት ደራሲ) ደስ ብሎኝ እጠቅሳቸዋለሁ፡፡ የፕ/ር ጌታቸው ‹‹ስለግዕዝ ሥነ ጽሑፍ የተሰበሰቡ አንዳንድ ማስታወሻዎች›› የተሻለ ሃይማኖታዊ መነጽር አለበት (‹‹ከግዕዝ ሥነ ጽሑፍ ጋራ ብዙ አፍታ ቆይታ›› ከሚለው በተለየ)፡፡
ለሰማዕያንና አንባብያን ያለን ምክር፡- አብዛኛው የውስጥም ሆነ የውጭ ተናጋሪ ስለገድላት ሲናገር ንባቡን ጠርጥሩ! ግምቱን ነው ወይስ ንባቡን? ቁንፅል ዕውቀቱን ነው ወይስ ጥናቱን? ሥራዬ ብሎ ውሎበታል አልዋለበትም? የሚለውን ጠርጥሩ! ብዙ ፈትነን ያረጋገጥነው ምክንያታዊ ጥርጣሬ ስለሆነ! የሐዲስ ኪዳን ትርጓሜ ማስመስከር ወይም የሥነ መለኮት ምሩቅ መሆን ስለገድላት በሥልጣን ለመናገር መብት እንደሚሰጥ ተደርጎ መታመኑ መበረታታት ያለበት ተግባር ሆኖ አይታየንም፡፡
#የመሥዋዕቱ_ማሳረጊያ፡- የቤተ ክርስቲያን ዋነኛ የአምልኮ መፈጸሚያ ቅዳሴው ነው፡፡ በቅዳሴ ውስጥ የሚነበቡት መጻሕፍት ከመጽሐፍ ቅዱስ የተመረጡ 4 ምንባባት (ከመልእክታት፣ ከሐዋ.ሥራና ከወንጌል) ብቻ ናቸው፡፡ ገድል በቅዳሴ አይነበብም (የቅዳሴውን አንድምታ ትርጓሜ ገጽ 96 ማየት ይቻላል)፡፡ የመሥዋዕት ማሳረጊያው ቅዱስ መጽሐፍ ነው፡፡ ገድላት ከቅዳሴ በኋላ ወይም በፊት ለማጽኛና መጽናኛ ይነበባሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ለቅዱስ ወንጌል በምትሰጠው ቦታ ላይ ብዥታ የለም፡፡
#ገድላትና_ድርሳናት_ለሃይማኖት_ማስረጃነት፡-
(1)ገድላትና ድርሳናት በቤተ ክርስቲያን ለቅዱሳት መጻሕፍት መተርጐሚያና ማብራሪያነት ይጠቀሳሉ፡፡ በነገረ ሃይማኖት ረገድም በቀደሙት አበው ዘንድ ገድላትና ድርሳናት ለሃይማኖት ማስረጃነት ሲጠቀሱ እናያለን (ሃይ.አበ.ዘባስልዮስ ም.96፡42 እና ዘዮሐንስ 114፡20)፡፡ በቦሩ ሜዳ ጉባኤ ሦስት ልደቶች ከደብረ ብርሃኑ ተአምረ ማርያም መጥቀሳቸው የተነቀፈበት ዐውድ መለጠጥ የለበትም፡፡
(2)መጀመሪያ ወደ ምንጭና ሥልጣን ወዳለው ንባብ ክርክር የተሔደው ያላስማማ ኃይለ ቃል ስላለ ነው፤ የተአምሩ አስፈላጊነት ላይ ክርክር የለም፤ ቦሩ ሜዳ ክርክርና ጥያቄ ሲነሣ በበላይነት መምራት ያለበትና ልንከተለው የሚገባው ዋነኛው የበላይ ገዢ የክርስትና ሕግ መጽሐፍ ቅዱስ ነው በሚል የተነገረበት ነው፤ ጥያቄ በማይነሣባቸውና በትርጉም ባላከራከሩ ነጥቦች መጠቀሱ ይቀጥላል፤ ማረም ቢያስፈልግ የደብረ ብርሃኑ ተአምረ ማርያም የሦስት ልደቶችን በመደገፍ የተጻፈው ክፍል ተለይቶ ይታረማል እንደማለት ነው፡፡ እናስተውል! ገድል ቀኖናዊ መጽሐፍ (Canonical Book) አይደለም! አዳዲስ ተአምራት ሲፈጸሙ ተጨምረው ይጻፋሉ፤ የተፋለሱ ምንባባት ይቃናሉ፡፡
(3)የቦሩ ሜዳ ጉባኤ ውሳኔ የቤተ ክርስቲያን የዶግማ መግለጫዎችን በምንረዳበት ጊዜ ስለሚኖረን የምንጮች ተዋረድ(Hierarchy of sources)ና ምንጮች ሲያከራክሩ በስተመጨረሻ በየትኛው ፍጹማዊ መስፈሪያ እንደሚፀኑ (በሕግ validity requirement እንደሚባለው) በሚያስታውቅ ዐውድ የተነገረ መሆኑን መረዳት ይገባል፡፡ በጉባኤው ‹‹ሁለት ልደት›› ተብሎ የተወሰነው በዋናነት በሃይማኖተ አበው ምንባባት ነው፤ ሃይማኖተ አበው ቁጥሩ ከድርሳን ነው፡፡ እዚህ ላይ ድርሳን የሚለው የግእዝ ቃል የመጽሐፍ ማብራሪያን (Homily) እና የመላእክት/ቅዱሳን ድርሳንን (Encomium) ስለሚጠቅልል ዐውዱ እንዳያሳስተን፡፡
--
የመልእክቱ ጭብጥ፡- በገድላት ጉዳይ የማርያም መንገድ ለመስጠት አንፋጠን!
ሦስት ነገሮች ይቅደሙ፡-
(1)የገድላቱን አስፈላጊነት አምኖ መነሣት፣
(2)በሃይማኖታዊ መነጽር ማጥናት፣
(3)ማቅናት፣ የቀናውን ማጽናት፡፡
--
በቀናች ሃይማኖት አጽንቶ ከቅዱሳኑ ይደምረን! አሜን!!!
✍️ደብተራ በአማን ነጸረ እንደጻፉት