የጎሠቆለ ባሕርይ (Fallen Nature)
ይህን ጉዳይ ትንሽ ዘርዘር አድርጎ ለመረዳት አዲሱን "ዐይነ ልቡና" የሚለውን መጽሐፌን ይመልከቱ። አምስት ኪሎ "ሰርዲኖስ የመጻሕፍት መደብር" ዋና አከፋፋይ ኾኖ በሌሎችም የመጻሕፍት መደብር ታገኙታላችሁና። ዛሬ በአጭሪ ላቀርብ ወዳሰብኹት ጉዳይ ልግባ።
የጎሠቆለ ባሕርይ የሚባለው በዋነኛነት አዳም ከበደለ በኋላ የኾነው ነው። አዳም ከውድቀቱ በኋላ የሰውነት ባሕርዩ አልተለወጠም። ከውድቀት በፊት ኾነ ከውድቀት በኋላ በሰውነት ለውጥ የለምና። ነገር ግን ከውድቀት በፊት በንጹሕ ባሕርይ መልክአ እግዚአብሔሩ ሳይደክም፤ የጸጋ ልብስን ለብሶ በፍጥረት ላይ የገዥነትን ሥልጣን ተጎናጽፎ በክብር ይኖር ነበረ። ሕገ እግዚአብሔርን ተላልፎ በወደቀ ጊዜ ግን የባሕርይ ውድቀት (ሕማም) ወይም ንዴተ ህላዌ (የባሕርይ ድህነት) ገጠመው።
- Fallen Nature በዋነኛነት የመልክአ እግዚአብሔር መድከምን፦ አዳም የተፈጠረው በእግዚአብሔር መልክ ነው። ያን በተፈጥሮ የተሰጠውን መልክአ እግዚአብሔር ሙሉ በሙሉ ባያጣውም በሕግ መተላለፉ ምክንያት አደከመው። አንዱና ዋነኛው የጎሠቆለ ባሕርይ ምልክት ይህ ነው። ኹለተኛው የጎሠቆለ ባሕርይ የሚባለው ከጸጋ እግዚአብሔር የተራቆተ፦ ማለትም እግዚአብሔር አልብሶት የነበረውን የብርሃን ልብስ ያወለቀ፥ የእግዚአብሔር ልጅነትን ያጣ ባሕርይ ነው። ሦስተኛ ከባሕርዩ መጎሥቆል የተነሣ ለኃጢአት የሚያዘነብል መኾን ነው። አራተኛ ጉሥቁል ባሕርይ ያለው ሰውነት ርግማንን ተሸክሟል። ይኸውም መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ነው። በሥጋው ወደ መቃብር ገብቶ መበስበስ (ሞተ ሥጋ)፤ በነፍሱ ወደ ሲኦል መግባት ነው (ሞተ ነፍስ) ዋናው ሞተ ነፍስ ከእግዚአብሔር መለየት ገጥሟቸዋል። ስለ ርግማን ሞት ስናነሣ በዋነኛነት የነፍስ ከሥጋ መለየትን ብቻ ሳይኾን የሥጋን ወደ መቃብር ገብቶ መበስበስ፣ የነፍስን ከእግዚአብሔር መለየት (ሞታ ለነፍስ ርሒቅ እም እግዚአብሔር እንዲል ሊቁ ቅዱስ ያሬድ) ይህን ይመለከታል። የሐዲስ ኪዳንን ሞት ለመረዳት "ዐይነ ልቡና" የምትለውን መጽሐፌን ይመልከቱ። እነዚህ በመሠረታዊነት ሰውነትን የጎዱና ያደከሙ ናቸው።
-በባሕርዩ መጎሥቆል ምክንያት የመጡ ጎጂ ያልኾኑ ኹኔታዎች ወይም ሕማማት ዘአልቦቱ ኃጢአት (blemeless Passions) ኃጢአት አልባ ሕማማትን መቀበል ግን በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስለኛ ተብሎ በፈቃዱ ለቤዛነት ብሎ የተቀበላቸው ናቸው፤ እመቤታችን ደግሞ ሰው እንደ መኾኗ ያን እንድትቀበል ልጇ ወዳጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ፈቅዷል። ስለዚህም ተርባለች፣ አዝናለች፣ ተሠቃይታለች፣ ሞታለች። እነዚህ ኹኔታዎች በራሳቸው ኃጢአቶች አይደሉም። እንደ ነውርና ርኲሰትም አይቆጠሩም። ጌታችንም እነዚህን ስለኛ ብሎ የተቀበለው በዚህ ምክንያትና ስለኛ ቤዛ ሊኾነን ነው። ይሄን የተቀበለው ደግሞ ሥግው ቃል እንደ መኾኑ ነው። ስለኛ መራቡን፣ መጠማቱን፣ መገረፉን፣ የእሾህ አክሊል መቀዳጀቱን፣ መራራ ሆምጣጤ መጠጣቱን፣ በመስቀል ላይ ዕርቃኑን መሰቀሉን፣ መሞቱን በእውነት የተቀበላቸው ቤዛ ሊኾነን እንጂ ያን በመቀበሉ ምክንያት የጎሠቆለ ባሕርይን ለብሷል ለመሰኘት አይደለም። ቃል ከሥጋ ከተዋሐደ በኋላ ሥግው እንደ መኾኑ ለቤዛነት የተቀበላቸውን ነገሮች የማዳን ሥራ (Economy of Salvation) እንላለን እንጂ በሌላ መንፈስ እንዲታይ ፈጽሞ አናደርግም።
እነዚህን ነገሮች ሥግው ቃል በፈቃዱ ያደረጋቸው ናቸው። ብዙ ቅዱሳን ሊቃውንትም ቅዱስ ቄርሎስ፣ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ፣ ቅዱስ ያሬድ፣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ... "ኅሥሩ" -"ጉሥቁል" ሥጋን ነሣ ሲሉ በአንድ በኩል ከደካማው አዳም ሰውነት የተከፈለውን ሰውነት መንሣቱን ለማሳየት ሲኾን በሌላ በኩል በፈቃዱ ሕማም፣ መከራና ሞት የሚስማማውን ሰውነት ገንዘብ ማድረጉን ለማመልከት ነው። ከዚህ ውጭ ከላይ በዋነኛነት የወደቀ ባሕርይን የሚገልጡ ነገሮች ያሉበትን ሰውነት ለበሰ ለማለት አይደለም። ለዝርዝሩ "ዐይነ ልቡናን" ይመልከቱ። በነገራችን ላይ አኹን እንኳን እኛ ኦርቶዶክሳውያን አምነን፣ ተጠምቀን በቅብዐ ሜሮን ከብረን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብለን የክርስቶስ አካል ከኾን በኋላ blemeless passions የሚባሉት ያልቀሩልን በራሳቸው ክፉዎች ስላልኾኑ ነው። እነዚህ ነገሮች አዲስ ሰውነትን ገንዘብ አለማድረግን የሚያመለክቱ አይደሉም። ይኸውም ማለት በጥምቀት ከአሮጌ ማንነት ወጥተን ክርስቶስን ለብሰን አዲስ የምንኾን መኾናችንን የሚያስቀሩ አይደሉምና። ከአሮጌ ማንነት በጥምቀት ከተላቀቅን በኋላ መልሰን ባረጀ ሰውነት ውስጥ እንዳለን አድርገን አንናገርም። በትንሣኤ አኹን ከለበስነው የበለጠ የከበረ ኢመዋቲ ኢድኩም ወኢሕሙም የኾነ ሰውነትን መልሳችንን ፍጽሙ ድኅነት ከትንሣኤ በኋላ መኾኑን የሚያረጋግጥ እንጂ አኹን ብትጠመቁም አሮጌ ማንነት ውስጥ ነው ያላችሁ የሚያስብል አይደለም። ሌላው ቀርቶ ያን አዳም በገነት እያለ ያወለቀውን የብርሃን ልብስ ስንጠመቅ እንለብሰዋለን (በተለይ ቅዱስ ኤፍሬምና ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ በትኩረት ይህን ያስተምራሉና) ነገር ግን ለኛ ለዐይነ መጭማጮች ከተጠመቅንም በኋላ ያን የብርሃን ልብስ መልበሳችን አለመታየቱ ያለመልበሳችን ማረጋገጫ ሊኾን አይችልም። ነገር ግን በግልጽ አኹን ያን ልብስ መልበሳችንን ማየት ባንችልም ከትንሣኤ በኋላ ተገልጦ እናየዋለን። ያኔ የሚገለጠው ግን ላልተጠመቁ ሳይኾን በጥምቀት ለከበሩት ክርስቶስን ለለበሱ ነው። ይህን ልብ ማለት ይገባል።
- አካላዊ ቃል የተዋሐደው ሥጋ ንጹሕ ሥጋ ነው። ምንም ዓይነት ነውርና ነቀፋ የለበትም። መንሣትና መዋሐድ ያለመቀዳደም የኾነ ስለ ኾነ ከእመቤታችን የነሣው ሰውነት ንጹሕና ነውር ነቀፋ የሌለበት ነው። የኃጢአት ጠባሳም አላገኘውም። ጸጋን የተመላ፣ መልክአ እግዚአብሔሩ ያልደከመ፣ ኃጢአት ያልገዛው፣ መርገም ያላረፈበት ንጹሕ ሰውነት ነው። ቅድስት ድንግል ማርያም የተጠበቀችው የጉሥቁልና ውጤት ከኾነው ከጸጋ መራቆት፣ ከመልክአ እግዚአብሔር መድከም፣ ለኃጢአት ከማዘንበል፣ ከመርገመ ሥጋ ወነፍስ፣ ከልማደ አንስት በወሊድ ጊዜ ከሚመጣ ምጥ ኹሉ ነው። ይህ ከእርሷ በቀር ከሰው ወገን ለማንም ቀድሞ የተደረገ አይደለም። ስለዚህም ምክንያት በዋነኛው የውድቀት ምልክት አንጻር አድርገን ስናይ እርሷ የወደቀ ሰውነትን ገንዘብ እንዳታደርግ ልጇ ጠብቋታል እንላለን። የእርሷን ሕይወት በልዩ ኹኔታዎች እንዲመላ ያደረገው እርሱ አምላኳ ነውና። የጎሠቆለ ሰውነትን አልለበሰችም ስንል ሕማም፣ ኀዘን፣ መከራ፣ ሞት የማይስማማውን ሰውነት ገንዘብ አድርጋለች ማለታችን አይደለም። ይህን የሚልም አይኖርም ይልቅስ ከላይ እንዳልኹት ከዋነኛው የጒሥቁልና ውጤት መጠበቋን ማዕከል በማድረግ የወደቀ ሰውነትን አልለበሰችም እንላለን። አበውም ያስተማሩት በዚህ አግባብ ነው። በዝርዝር የእርሷን ጉዳይ ለመረዳት "ዐይነ ልቡና" ይነበብ። ልጇ በፈቃዱ ስለኛ የሞተው በማስመሰል ሳይኾን በአማን ነው። ሞትንም በፈቃዱ የተቀበለው ያ ሥጋ የዕሩቅ ብእሲ ሥጋ ሳይኾን የሥግው ቃል ሥጋ ነውና። ሞትን ስለኛ የተቀበለው ሥጋ ራሱ ለኛ ሕይወትን የሚያድል ነው። የሞተውም ሊበሰብስ ሳይኾን ሞትን በሞቱ ገድሎ ሞት የወረሰውን ሰውነት ሕይወት ሊያለብሰው ነው። ይህ የቅዱስ አትናቴዎስና የቅዱስ ቄርሎስ የትምህርት ማዕከል ነው።
እመቤታችን ለምን ሞተች? መልሱ በአጭሩ፦