1) የሞተችው ለመበስበስ ሳይኾን የትንሣኤን አካል ገንዘብ ለማድረግ ነው። ይኸውም ኢመዋቲ አካልን ገንዘብ ለማድረግ እንጂ ለመበስበስ አይደለም። ይህ ዮሐንስ ዘደማስቆ በመደነቅ የገለጸው ነው። ሰውነቷ እንዲበሰብስ ልጇ አለመፍቀዱን ሞታ መበስበስ ሳያገኛት ከልጇ ትንሣኤ በኋላ በልጇ ሥልጣን በሦስተኛው ቀን መነሣቷን ብዙዎቹ ቅዱሳን ሊቃውንት የገለጹት እና እኛም የምናምነው ነው።
2) የሞተችው ሰው ስለ ኾነች ነው። አምላክ በመውለዷ ምክንያት በሕሊናቸው ሰው አይደለችም የሚሉ ሰዎች እንዳይኖሩና በእርሷ ሰው የመኾን ጉዳይ ጥርጣሬ እንዳይፈጠር ሞትን ትቀምስ ዘንድ ልጇ ፈቅዷል። ይህ እነ አብሮኮሮስ በአጽንዖት ያስረዱት ነው። ይህ ምክንያት ቃል ሰው አልኾነም የሚለውን ክሕደትናና እርሷም ሰው አይደለችም የሚለው ስሕተት የሚያርም ነው።
3) ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ እንዳለው ያረፈችው የልጇን የሞት ጽዋ ለመቅመስ ነው። ይህም እንዲኾን የእርሱ ፈቃድ ነው።
4) ሞቷ የመሸነፍ ሳይኾን የክብር እና የድል እንደ ኾነ እንድናውቅ ነው። ይህን ለመረዳት የሞቷን ዜና ከልጇ ዘንድ የተላከው ቅዱስ ገብርኤል ሊያበሥራት ሲመጣ የድል ምልክት የኾነውን የዘንባባ ዝንጣፊ ይዞ መምጣቱን እነ ማክሲሞስ ተናዛዚው የቀደሙ ትውፊቶችን ማዕከል አድርገው "The Life of The Virgin" በሚለው መጽሐፍ ዘግበዋልና።
5) ሞቷ ተራ ሞት ሳይኾን በመደነቅና በመገረም የሚናገሩት ሞት ነው። ቅዱስ ያሬድ "ማትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኲሉ" - ሞትማ ለሚሞት ይገባል የማርያም ሞት ግን ለኹሉ ያስደንቃል" የሚለው ለዚህ ነው። እንደ በሥጋና በደም ኾነን በድፍረት ከመናገር ልንቆጠብና ልናደንቅ ይገባል።
ዲያቆን ዮሐንስ ጌታቸው እንደጻፈው