የአክሊል ችግር ምንጩ ምንድነው?
...
ወንድማችን አክሊል ወደ አገልግሎት መመለሱ መልካም ነው፤ እግዚአብሔር የሰጠውን ጸጋ ለመጠቀምና ለቤተ ክርስቲያን ተልእኮ መሳካት ለማዋል ማበረታታት አለብን። እኔ በትጋቱና በብዙ መንገድ ምእመናንን እየጠቀመ ላለው አገልግሎቱ አድናቆት አለኝ። አድናቆቴን ከምገልጥባቸው መንገዶች አንዱ ስሕተት ሳይ እንዲያስተካክል መምከር እንቢ ካለም የሚሰሙት እንዳይሳሳቱ ማስተማር ነው።
....
በትጋት ሲያገለግል ምርቃትና ድጋፍ እንደሚሰጠው ሁሉ ስሕተት ሲሠራም ለመታረም ፈቃደኛ እንደሆነ እገምታለሁ፤ ለመታረም ፈቃደኛ ነኝ ብሎ ሲናገርም ስለሰማሁት ስሕተት የማይሠራና የማይታረም አድርጎ ራሱን አይቆጥርም ብየ አምናለሁ።
...
ከዚህ ቀደም ያሉኝን ልዩነቶች አገልግሎታችንን በማይጎዳና ፍቅርን መሠረት ባደረገ መንገድ አስተያየት ሰጥቻለሁ። አስተያየቶቼ ይዘትንም አካሄድንም የሚመለከቱ ነበሩ፤ በዚህ ጽሑፍ ግን መታረም አለመታረማቸውን መገምገም አልፈልግም።
....
አክሊል በቅርቡ በቪዲዮ ያስተላለፈውን መልእክት ሁለት ጊዜ ሰማሁት፤ አንድ ጊዜ የሰማሁት ሌሊት ከ9:30-10:35 ነው። ይህ ጊዜ ጸጥታ የሰፈነበት ስለሆነ በትክክል ሰምቼዋለሁ። ስሕተት ነው ብየ ያመንሁትን ነጥብ የለየሁት በዚህ ጊዜ ነበር። ተመልሼ ስሰማው ማስታወሻ ይዤ ቪዲዮ በየስፍራው እያቆምሁና መልሼ እያዳመጥሁ ነበር።
...
"ያልነሣውን አላዳነውም" የሚለው ርእስ የታወቀና የታመነ ንባብ ነው፤ የነሣውን በትክክል ዐውቀን በትክክል እየገለጥነው ነው ወይ? የሚል ጥያቄ ግን አለኝ።
...
ጥቅሱን ተገቢ ባልሆነ መንገድ እንደተረዳውና እንደተጠቀመው ተረድቻለሁ። እንደ አቻዎቹ ያለ ሥጋን ይዟል እያለ ደጋግሞ ይናገራል። የአክሊል እንደ አቻዎቹ ያለ ሥጋ ማለት ምን ማለት ነው? የአቻዎቹ ማለት የሁላችንም ሰዎች ሥጋ ማለት ነው። ክርስቶስ ገንዘብ ያደረገው ሥጋችንን ወይም ባሕርያችንን ነው። ባሕርያችን በተፈጥሮ አንድ ነው። የእኛ ሥጋ ኀጢአተኛ ሥጋ/ባሕርይ ግን መሆኑን አክሊልም አይክድም። የጌታ ሥጋም እንደ አቻዎቹ ያለ ሥጋ ከሆነ ኀጢአተኛ ሥጋ (ባሕርይ) ነው ማለት ነው? ይህን እያለ ከሆነ ስሕተት ነው። ቢያንስ ይህን አጥርቶ መናገርና ሰሚን ከማደናገር መታቀብ አለበት። የጌታ ሥጋ እንደ ሁላችንም የሰው ልጆች ሥጋ ነው። ይህም ማለት ሞት የሚስማማው ሥጋ ነው ማለት ነው። መዋቲነት፣ መታመም፣ መራብና መጠማት፣ መድከም እነዚህ ሁሉ የሥጋ (የሰው ባሕርይ) ገንዘቦች ናቸው እንጂ በኀጢአት ምክንያት በኋላ የመጡ አይደሉም።
....
የሳዊሮስና የአትናቴዎስን ትምህርት በትክክል ካነበበ መዋቲነት የሰው ተፈጥሮ ገንዘብ እንጂ የኀጢአት ውጤት አይደለም። ዲያቆን ያረጋል በተረጎመው የቅዱስ አትናቴዎስ መጽሐፍ ገጽ 160 ላይ
"ሕጉን መተላለፍ ሲጀምር ሰውን በባሕርዩ የነበረ መዋቲነትና መለወጥ (moryality and corruptibility) ገንዘቡ አድርጎ ወርሶታል" ይላል። በቅዱስ ሳዊሮስና በቅዱስ አትናቴዎስ ትምህርት መሠረት ሞት እንጂ መዋቲነት የኀጢአት ውጤት አይደለም። መዋቲነትና መለወጥ (mortality and coruptibility) የሰው የባሕርይ ገንዘቦች ናቸው። ኢመዋቲነትና አለመለወጥ ( immortality and incorruptinility) ደግሞ የእግዚአብሔር ብቻ የባሕርይ ገንዘቦች ናቸው። እግዚአብሔር ሰውን ኢመዋቲ ሊያደርገው ፈቃድም ችሎታም አለው እንጂ ኢመዋቲ አድርጎ አልረጠረውም።
....
አክሊል በሁሉም ንግግሩ ውስጥ ደጋግሞ ስለጌታ መዋቲነት ሲናገር በኀጢአት ምክንያት በሰው መዋቲነት እንደመጣበትና ጌታም ያን ገንዘብ እንዳረገ አስመስሎ ይናራል። ይህን ነጥብ ለብዙ ትምህርቱ ምንጭ አድርጎ እየተጠቀመው ስለሆነ አጥርቶ መረዳትና ማረም አለበት።
.....
ጌታ ሥጋን ገንዘብ ያደረገው ፦ በተፈጥሮው መዋቲ ከሆነ፣ በኋላም በኀጢአት ወድቆ ሞት ከሰለጠነበት ሥጋ ከፍሎ በሥጋዌ ምሥጢር በግብረ መንፈስ ቅዱስ በዐዲስ መልክ በድንግል ማርያም ማኀፀን የተፈጠረ ሥጋን እንጂ ሞት የሰለጠነበትን ባሕርይ ከሞት ነጻ ሳያወጣ አይደለም። በፈቃዱ ለሌሎች ቤዛ ሆኖ ከመሞት በቀር በጌታ የግድ ሞት የሌለበት በተፈጥሮው መዋቲነት ገንዘቡ የሆነ እንጂ ሞት በኀጢአት ምክንያት ያልሰለጠነበት ሥጋን ገንዘቡ በማድረጉ ነው።
...
የእኛ ሥጋ በተፈጥሮው ከጌታ ሥጋ ጋር አንድ ብቻ አይደለም። በኀጢአተኛነቱና ሞት የሰለጠነበት በመሆኑም የተለየ ነው። የጌታ ሥጋ መዳንን የማይፈልግና ከቃል ጋር በመዋሐዱም አዳኝ ነው። ይህን ነጥብ አክሊልም በስሱ አንሥቶታል። ነገር ግን በጉሕህ መነሣት ያለበት ይህ ልዩነትም እንጂ ባሕርያዊ አንድነቱ ብቻ አይደለም። የጌታ ሥጋ እንደ እኛ ነው ብለን በደፈናው ብንሰብክማ ሞት ችግር ያመጣል። ጌታ ሥጋችንን ሲዋሐድ የሰውን ባሕርይ ከኀጢአት በፊት ወደ ነበረው ክብር ብቻ ሳይሆን ወደማይነገር ታላቅ ክብር ያወጣው መሆኑን አክሊል ከተናገረውም ይገኛል።
....
ሳዊሮስና ዩልያኖስ የተለያዩበት ነጥብ ሰው ከኀጢአት በፊት መዋቲ ነው/አይደለም የሚል ነበር። ዩልያኖስ መዋቲ አልነበረም። ኢመዋቲ ነው ብሎ አስተማረ። ሰው ኀጢአት ሲሠራ መዋቲ ሆነ አለ። ስለዚህም ጌታ የለበሰው ሥጋ አዳም ከመበደሉ በፊት የነበረው ሥጋ ነው። ሞት አይስማማውም። የሞተውም በፈቃዱ ነው እንጂ የሚስማማው ሥጋ ስላለው አይደለም አለ። መዋቲነት የኀጢአት ውጤት ነው ብሎ ማመኑ ጌታ መዋቲ ሥጋን ሊዋሐድ አይችልም እንዲል አደረገው። ሳዊሮስ ግን መዋቲነት የሰው ተፈጥሮ ገንዘብ እንጂ የኀጢአት ውጤት አይደለም። የኀጢአት ውጤት ሞት እንጂ መዋቲነት አይደለም አለ። ልዩነቱ ካልገባን ቀጣይ አጽፋለሁ።
...
ጌታ ሰው ሲሆን መዋቲ ሥጋን ገንዘብ ማድረጉ የሰውን ተፈጥሮ መዋሐዱ ነው። ነገር ግን የአዳም ባሕርይ መዋቲነቱ ኢመዋቲ የመሆን እድል ነበረው። ይህን እድል በበደለ ጊዜ አጣ። በቅዱስ አትናቴዎስ አገላለጽ ኀጢአት የነበረውን እድል ማጥፋትዋ ብቻ ሳይሆን ሰውን ወደ አለመኖር እንዲመለስ ጉዞ አስጀምራው ነበር። ኀጢአት የሰውን ክብርና እድል ብቻ ሳይሆን ህልውናውን ለማጥፋት ጉዞ አስጀምራው ነበር። ነገር ግን የፈጠረን እግዚአብሔር ራራልንና ከጥፋት መንገድ መለሰን።
...
ጌታ መዋቲነትን በተዋሕዶ ጊዜ ያላጠፋው ስለማይችል ሳይሆን እንዲያድንበት ፈልጎ እንዳይጠፋ ስለፈቀደ ነው። ሞትን በፈቃዱ ለመቀበልና በእርሱ ሥጋ ለማጥፋት መዋቲነቱ መቆየት ነበረበት። መዋቲነቱን በተዋሕዶ ጊዜ ከራሱ ሥጋ ላይ ካጠፋው እርሱ ኢመዋቲ ይሆናልና ሞቶ ቤዛ ሊሆነን አይችልም። "በሞቱ ለሞት ደምሰሶ" እንዳለው ሞትን አግኝቶ ሊውጠው ወይም ሊያጠፋው አይችልም። ሞት ጌታን መያዝና ማጥፋት አይችልም። እርሱ ንጹሕ ነውና በፈቃዱ ካልሆነ ሊይዘው አይችልም። በፈቃዱ ሊይይዘው የቻለው ደግሞ ሞትን ለማጥፋት ራሱ ስለፈለገ ነው እንጂ ሊሞት ስለተገደደ አይደለም። ይህ ነጥብ በአባቶች ትምህርት በዝርዝር የተገለጠ ነው። አትናቴዎስና ሳዊሮስ ደግሞ ይበልጥ አብራርተውታል።