ስለ ሰሞኑ ጉዳይ ...
***
1. ያለሕግ ፍርድ የግድያ ቅስቀሳ ማድረግ ወንጀል ነው። እስከምናውቀው ድረስ ኢትዮጵያ ለሃይማኖት የማይወግን (secular) ሕገ መንግሥት ያላት ሀገር እንጂ በሸሪዓ የምትተዳደር ሀገር አይደለችም። በመሆኑም የሚያስቆጣ ነገር ሲኖር ወደ ሕግ መውሰድ እንጅ በደቦ ለመግደል መነሣት ትልቅ ስሕተት ነው። ሰው ሁሉ ፍርድን በእጁ አድርጎ መገዳደል ከጀመረ የሚነደው እሳት መጥፊያው ጭንቅ ይሆናል።
2. የሃይማኖት ውይይት (ክርክር) መደረጉ አስፈላጊ እና የማይቆም ነገር ነው። ሁሉም ሃይማኖቶች ዕቅበተ እምነት የመሥራት እና ሌላውን ወደራስ የማምጣት ኃላፊነት አለባቸውና።
3. በውይይቶች ምን ዓይነት መንገድ እንከተል? የሚለው ወሳኝ ነገር ነው። Double standard አያስኬድም። "እኔ እንደ ልቤ ልናገር። ሌሎች ግን እኔ እስከፈቀድኩት ልክ ብቻ ይናገሩ" ማለት ፍትሕ አይሆንም። ዘላለማዊ እውነትን ከሚፈልግ ሃይማኖተኛ የሚጠበቀው ለራስም ለሌሎችም አንድ አይነት መሥፈርት ማውጣት ነው። በመሆኑም አንዳንድ ጠንከር ያሉ የእቅበተ እምነት አካሄዶችን የሚያወግዝ ሰው በሁለቱም በኩል ያለውን ቢያወግዝ ቢያንስ ፍትሐዊ ይሆናል።
4. ከሰሞንኛው ችግር ተነሥተን የክርስትና-እስልምና ተዋሥኦ እንዴት ይሠራ? እኛ ላለንበት ሁኔታ ትክክለኛው ተግባራዊ አካሄድ የትኛው ነው? በሚሉ ጉዳዮች ላይ ውይይቶች ቢደረጉ ጥሩ ይመስለኛል።
ዲያቆን በረከት አዝመራው እንደጻፈው