ለኅብረተሰቡ የሕክምና አገልግሎት እንሰጣለን በማለት የሃይማኖት ተኮር እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ መሆኑን ምእመናን ገለጹ !
መጋቢት ፫/፳፻፲፯ ዓ/ም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ
በአሪ ዞን በባካ ዳውላ ወረዳ ለኅብረተሰቡ የሕክምና አገልግሎት እንሰጣለን ፣ መነጽር እናድላለን በማለት ምእመኑን ስብከት ለመስበክ እና ለማደናገር ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን በአካባቢው የሚገኙ ምእመናን ጠቁመዋል።
ሕክምና እንሰጣለን በማለት ከእስራኤል ሀገር በመጡ የሕክምና ባለሙያዎች "ጉዞን ከመሲሁ ጋር መጀመር" የሚሉ ወረቀቶችን በመበተን ምእመኑን የማወዛገብ ሥራ እየተሠራ መሆኑን ለተዋሕዶ ሚዱያ ማዕከል አስረድተዋል።
ተሚማ የመረጃውን እውነተኛነት ለማጠናከር ባደረገው ጥረት የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎችን በስልክ በማነጋገር ስለጉዳዩ ባደረገው ማጣራት የሕክምና ባለሙያዎቹ እንደገቡና ሕክምና እየሰጡ እንደሆነ በመግለጽ ከአንዳንድ ምእመናን ግን በደረሰን መረጃ በአዳራሽ አስገብቶ የመስበክ ሁኔታዎች መኖራቸውን ፣ በተለይም ወቅቱ የዐቢይ ጾም በመሆኑ ሁሉም አባቶች በሥርዓተ ቅዳሴ አገልግሎት ስለሚያሳልፉ ምእመናኑ ከእንደዚህ ዓይነት ድርጊት ራሳቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን እንዲጠብቁ አሳስበዋል።
በሕክምና እንዲሁም በሌሎች ሃይማኖት ነክ ባልሆኑ ሥራዎች ገብቶ እንደዚህ ዓይነቱን የሃይማኖት ተግባር ማከናወን በሕግም የሚያስጠይቅ መሆኑ የሚታወቅ ነው።
ዘገባው የዋሕዶ ሚዲያ ማእከል ነው።