ደብረ ዘይት ሚዲያ


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Din


ቤተክርስቲያን ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Din
Statistika
Postlar filtri




ሆሳዕና በደብራችን በደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ቡሌ ሆራ (ሀ/ማርያም










በነፍሳችሁ ጨው ይኑርባችሁ፥ እርስ በርሳችሁም ተስማሙ" ማር 9 : 50፡፡

☞ጨው የተባሉ፦
1. ክርስቶስ
2.ቅዱሳን (እመቤታችን ፤ መላእክት ፣ ጻድቃን ሰማዕታት....)
3. ሐዋርያት (ካህናት)

4. ምእመናን ናቸው፡፡

➊ ጨው ምግብ ያጣፍጣል፦ የጨው ዋና ጠባይ ራሱ የሚበላ ሳይሆን ሌሎች ምግቦች በእርሱ አጣፋጭነት እንዲበሉ እንዲፈለጉ እንዲወደዱ ማድረግ ነው (በጨው ደንደስ በርበሬ ተወደስ፦ እንዲሉ አበው፡፡)፤

• 👉ክርስቶስም ጻድቅሆኖ ሳለ ለእራሱ ጽድቅ ሳይሆን ለእኛ ጽድቅ በኃጢአታችን ሞቶ የእኛን ሕይወት አጣፍጦታል፡፡
(ፄው ዘአጥዐሞ ለልሱሕ)
• ጨው ሲያጣፍጥ ሟሙቶ ነው ጌታችንም ሊያጣፍጠን በመስቀል ድቅቅ ብሎ ነው (ኢሳ 53 ፥5 ስለ በደላችን ደቀቀ)፡፡
👉ቅዱሳንም ተጋድለው ተንከራተው ነው

• ካህናትም በምእመናን ሕይወት ውስጥ ሟሙተው ሕይወታችንን ያጣፍጣሉ

• ምእመናንንም በሌሎች ሰዎች ሕይወት የበጎ አርአያ ሆነው፤ በምጽዋትና በጾም በበጎ ምግባር ሟሙተው የሌሎችን ሕይወት ያጣፍጣሉ

➋ጨው ከሁለት ኢለመንቶች (Elements, Sodium Na እና Chlorine Cl) የተሠራ ውሕድ ነው 👉(Table salt)
• ♥ክርስቶስም ከሁለት አካል እንድ አካል፤ ከሁለት ባህርይ አንድ ባህርይ መሆኑን ያመለክታል፤ ይህም ማለት የቃልና የሥጋ ተዋሕዶ ማለት ነው (ዮሐ 1፡14)፡፡
👉ቅዱሳንም ከሥጋ ከመንፈስ ናቸው

• ካህናትም የሁለት ነገሮች ተዋሕዶ ናቸው ፦ የሥጋና የነፍስ ፤ የውኃና የመንፈስ፤የክርስትናና የክህነት ውጤቶች ናቸው
• ምእመናንም ክህነት ባይኖራቸውም ከእናት ከአባት ፤ "ከውሃና ከመንፈስ" የተወለዱ ናቸው፡፡

➌ጨው ርካሽ ነው፦ በቀላል ዋጋ ይገኛል፦
• ♥ክርስቶስም ያለ ዋጋ ተገኝቶልናል፤ ለፍቅሩ ለቸርነቱ የምንከፍለው ምንም የለንም፤ ለመክፈልም ዓቅሙ የለንም፡፡

👉የቅዱሳን ቃል ኪዳንም እንዲሁ ነው ....አይከፈልም
..... ለቅዱሳንም ሳንከፍላቸው ይማልዱልናል

• ካህናት ያለ ዋጋ ይገኛሉ፤ ለቡራኬያቸው አንከፍልም፤ ለጸሎታቸው አንከፍልም፤ ለቅዳሴው ለማኅሌቱ አንከፍልም...በነጻ!

• ምእመናን ሲመጸውቱ ፤ ሲረዱ፣ የታመመና የታሰረ ሲጠይቁ አይከፈላቸውም...ደግ ሆነው ግን በነጻ ያለ ዋጋ ደግ ሆነው ይኖራሉ፡፡

➍ጨው ምግብ እንዳይበላሽ መጠበቂያ (Preservative) ነው፡፡
• ♥ክርስቶስም በኃጢአትና በበደል ከርፍተን ሸተን የነበርነውን የሁላችንን ክፉ ሽታ በመስቀል ጠርቆ አስወግዶ እንዳንበላሽ እንደገና ሠርቶናል፤ ወደፊትም እንዳንበድል በመስቀሉ/በመከራው በውስጣችን ይኖራል፤ መከራ መስቀሉ ይመዘምዘናል፡፡

👉ቅዱሳንም ሕይወታችን እንዳይበላሽ በአርአያነታቸው ይጠብቁናል

• ካህናትም በኃጢአት ውስጥ ሆነን እንዳንበላሽ በንስሐ ይጠብቁናል፡፡
• ምእመናን ሌሎችን መክረው ፤ በንስሐ ለሌሎች ምሳሌ ሆነው ሌሎችን እንዳይበላሹ ወደ በጎ ምግባር ይመልሳሉ፡፡

➎ጨው ፈውስ/መድኃኒት ነው፤ ቁስል ያደርቃል፡
• ♥ክርስቶስም መድኃኒታችን ነው፤ በመስቀል ስለ እኛ ቆስሎ የእኛን ቁስል አድርቆ ፈውሶናል (ኢሳ 53) ፡፡
👉ቅዱሳንም በምልጃቸው በቃል ኪዳናቸው ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቁናል
• ካህናትም በምክር በአገልግሎት በማስታረቅ በንስሐ መድኃኒት ሆነው ወደ እግዚአብሔር ያቀርቡናል፡፡
• ምእመናን በሕይወታቸው፤ በደግነታቸው፤ በምጽዋታቸውና በጾማቸው ሌሎችን ኢአማንያንን ጭምር ይፈውሳሉ ፡፡

☞"ጨው መልካም ነው፤ ጨው ግን አልጫ ቢሆን በምን ታጣፍጡታላችሁ? በነፍሳችሁ ጨው ይኑርባችሁ፥ እርስ በርሳችሁም ተስማሙ" ማር 9 : 50፡፡

ጨው ሆነን አልጫ የሆነውን ዓለም ለማጣፈጥ ያብቃን🙏

መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው

ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, Subscribe እና Share ያድርጉ :-
ዩቱብ
https://www.youtube.com/@12Samual

ቴሌግራም
https://t.me/tsidq

tiktok
https://vm.tiktok.com/ZMBYPbBMJ/




ቸር አገልጋይ ማነው✞

ቸር አገልጋይ ማነው ለንጉሥ የታመነ
መክሊቱን ያልቀበረ አትርፎ የከበረ (፪)

ባለ አምስቱ መክሊት መልካም ያደረገው
በመውጣት በመውረድ አትርፎ መጥቶ ነው
በጥቂቱ ታምኖ በብዙ የተሾመው
ባለ አምስቱ መክሊት ሊቀ ጳጳሱ ነው
አዝ= = = = =
ሳይሰለች የተጋ ባለሁለት መክሊት
የታመነ እረኛ በፍቅርና በእምነት
ግባ የተባለው ወደ ጌታው ደስታ
አጥምቆ ያቆርባል ካህኑ የጌታ
አዝ= = = = =
ለሚበልጠው ጸጋ ተጠርቶ የነበረ
መክሊቱን ደብቆ ቆፍሮ የቀበረ
ሰነፍ ባርያ ተብሎ ወደ ፍርድ ተጣለ
ማኔ ቴቄል ፋሬስ በአምላክ ፊት ቀለለ
አዝ= = = = =
ፈቃድህን ማድረግ ነፍሱ ለምትወደው
ወንጌልህን መግለፅ የየዕለት ግብሩ ነው
ህግህ ለዘለላም ተጽፎ ይኖራል
በታላቅ ጉባኤ ጽድቅህ ይነገራል

መዝሙር
ዲያቆን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ

ማቴ፳፭፥፲፬-፴፩






ሐዋ 4-12 መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።


ዮሐ 8-12 ደግሞም ኢየሱስ፡— እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው።




* ከንብ ጋራ ኑሮ****
       ** በዳንኤል ክብረት*
      ትዳር ከንብ ጋር መኖር ነው።ንብ ሁለት ጠባይ አላት።አንዱ ያስደስታል ሌላኛው ያስከፋል አንዱ ጤና ይሆናል ሌላኛው ግን ያማል አንዱ ይጣፍጣል ሌላው ግን ይመራል።አንዱን ይቆርጡታል ሌላውን ግን ይከላከሉታል።ትዳርም እንዲሁ ነው።ሁለት ጠባይ አለው አንደኛው ያስቃል አንዱ ያሳቅቃል አንዱ ያስደስታል ሌላው ያሳዝናል።አንዱ ግቡ ግቡ ሌላው ውጡ ውጡ ያሰኛል።አንዱ ይናደፋል አንዱ ይጣፍጣል አንዱ ጤና ሌላው ህመም ይሰጣል።አንደኛው ግን ያለ ሌላው አይገኝም።ይኼን ለመድሀኒት ለብርዝ ለጠጅ የምናደርገውን ማር የምትሰጠው ንብ ናት የምትናደፈው።ያቺ ስትናደፍ ፊት የምታሳብጠው ውስጥን የምትመርዘው የምትጠዘጥዘው ንብ ናት ማሩን የምትሰጠው።በትዳርም ውስጥ ሁለቱም አሉ።ጭቅጭቁ ንዝንዙ ጠቡ ኩርፊያው አንዱ ለሌላው የግድ መታዘዙ አንዱ የሌላው አገልጋይ መሆኑ አንዱ ያለ ሌላው ለመወሰን አለመቻሉ የሌላውን ጠባይ የሌላውን ዐመል የግድ መታገሱ ከሚታገሱት ሰው ጋር አብሮ መኖሩ ይኼ ነው የንቧ ንድፊያ።
     ትዳር ከንብ ጋር መኖር ነው።ለማሩ ስንል ንድፊያውን መታገስ ቆይተህ ደግሞ ንድፊያውን መልመድ።ገበሬ ቀፎ ሰቅሎ ንብ ሲያንብ ንብ እንደምትናደፍ ሳያውቅ ቀርቶ አይደለም።የማትናደፍ ንብ ከፈለገ በየደጁ ቆሻሻ ፍለጋ የምትጓዝው ዝንብ ነበረችለት።ዝንብ ምን ጠባይዋ ሸጋ ቢሆን ጠብ የሚላት ግን ሌላ ነገር ነው።ይህን ያውቃል ገበሬው።እያወቀም ንብ ያንባል።ማነብ ብቻ ሳይሆን ከንብ ጋር እንዴት መኖር እንደሚችልም ያውቃል።ንብ ትናደፍለች ግን እንዳትናደፍ ማድረግ ይቻላል።የምትወደውና የማትወደው ሽታ አለ ስትቀርብህ ምን ማድረግ እና  ምን አለማድረግ እንዳለብህ ገበሬው ያውቃል።
   ትዳርም እንዲህ ነው።አኗኗሩን ነው ማወቅ የንቧን ንድፈያ የመቀነሻውን መንገድ ነው ማወቅ የማሩን አቆራረጥ መንገድ ነው ማወቅ።ደግሞምኮ አስገራሚው ገበሬው የሚንከባከበው ይህቺኑ የምትናደፈውን ንብ መሆኑ ነው።የምትቀስመው አበባ ትፈልጋለች ንፁህ አካባቢ ትፈልጋለች ከጉንዳንና ከአውሬ ነፃ የሆነ ቀፎ ትፈልጋለች።ግን ትናደፋለች ደግሞም ማር ትሰጣለች።
    ትዳር አስደሳች ነገር ብቻ ሳይሆን አስመራሪ አንገብጋቢ አስጠሊታ ጨጓራ አንዳጁ አንጀት ቆራጭ ልብ አቃጣይ ክፍል ሊኖረው ይችላል ይናደፋል ግን ደግሞ ክብካቤም ይፈልጋል።ንፁህ ልብ ታማኝ ህሊና ቻይ አንጀት ታጋሽ ሆድ ጠቢብ አእምሮ ቀና መንፈስ አሳላፊ ልቡና ይፈልጋል።ለምን ቢሉ? ማር ይሰጣልና።
    አንዳንዶች ቤት ካለችው ወይም ካለው ንብ ይልቅ ውጭ ያለችውን ወይም ያለውን ዝንብ ሲፈልጉ ሲያደንቁ ይሰማል።መቼም ከቀፎ ውጭ ምን እንደሚኖር የታወቀ ነው።ንብ ትናደፋለች ብሎ ንብ የማያነባ ገበሬ ስንፍናውን እንጂ የንቢቱን ክፋት ማንም አይረዳለትም።ጥበብ አልባ መሆኑን ትዕግስት አልባ መሆኑን ተሸናፊነቱን እየተናገረ እንጂ የንቧን ጠባይ እየተናገረ አለመሆኑን ሁሉም ያውቅለታል።የትዳር ችግር ብቻ የሚያወራ በትዳር ተመርሮ ከቀፎው ውጭ የሚሄድም ስንፍናውንና ዐቅመ ቢስነቱን እንጂ የቀፎውን ችግር እየተናገረ አይምሰለው።ቀፎ ውስጥ ማረ የምትሰራው ንብ እንዳለች ሁሉም ያውቃልና።ሌላው ቀርቶ ውጭ ያለችው ዝንብም ይኼንን ታውቃለች።
     አንዳንዶች ከንብ ጋር የመኖር ጥበብ ሲያንሳቸው የማትናደፍ ንብ ፍለጋ ይኳትናሉ።የማትናደፍ ንብ መፈለግ" ከመረቁ አውጡልኝ ከስጋው ጦመኛ ነኝ" እንደማለት ነው።ወይም የማትዞር መሬት እንደመፈለግ።
     የማትናደፍ ንብ ከፈለግክ ከዝንብ ጋር ተጋባ።






👉👉ወደ እስራኤል የምልከው ሰው የለኝም

ይህን ቃል የተናገረው እራሱ እግዚአብሔር ነው

ሰው የሚያስፈልገው ለሰው ብቻ አይደለም ለእግዚአብሔርም አስፈላጊ ነው ከሀያ ሁለተ ስነፍጥረት መላእክትን ጨምሮ እንደሰው ያለ? የእግዚአብሔር መልክ ያለው ክቡር ፍጥረት የለም

የመላእክት መልክ ይህን ይመስላል የሚል በጽሁፍ ደረጃ የተቀመጠ የለም የመላእክት መልክ የሚነገረው በምሳሌ ነው
ለምሳሌ የእንስሳት መልክ ያላቸው አርባዕቱ እንስሳ የሚባሉ መላእክት አሉ በሌላ ቦታ ደግሞ ከእግዚአብሔር ሲላኩ ሽማግሌም ወጣትም መስለው ሊገለጹ ይችላሉ መላእክት እንደፍጥረትነታቸው ውሱን ናቸው ነገር ግን ምን እንደሚመስሉ ምን እንደሚህሉ ዝርዝር ጉዳይ የተጻፈ የለም የሚያውቅ የለም።

የሰው ልጅ ፈጣሪውን እግዚአብሔር ይመስላል እግዚአብሔርን እንደሚመስል በምን ይታወቃሉ እራሱ እግዚአብሔር ነገረን

ዘፍጥረት 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁶ እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ።
²⁷ እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።
²⁸ እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው። ብሎ በግልጽ ነግሮናል።

👉በእራሱ መልክ እና አርአያ የፈጠረው የሰው ልጅ መልኩን ይዞ ከእግዚአብሔር ኮበለለ ግብሩን ለወጠ እንስሳትን መሰለ ሌላ አምላክ ፍለጋ ሄደ ሁሉም በየቤቱ ጣዖት አቆመ ጣዖት ሲባል ግድ ምስል መሆን የለበትም ዘረኝነቱ ፍቅረንዋዩ ሱሱ አመንዝራነቱ ስርቆቱ ምንደኝነቱ ሁሉ ጣዖት ነው

በዚህም እግዚአብሔርም አዘነ ወደ ሰው የምልከው ሰው የለኝም አለ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የሰጠውን ክብር እና ስልጣን ምን ያህል ታላቅ እንደሆነ ያሳያል

በዚያን ጊዜ ኢሳይያስ እኔ አለሁኝ አለ

ነቢዩ ጎዶሎ ችግር ነበረበት እግዚአብሔር አይ አንተ ጎዶሎ ችግር አለብህ አልፈልግም አላለውም ጎዶሎውን አስተካክሎ ላከው ይላል

ዛሬም እግዚአብሔር እንደትናንቱ ሰው የለኝም እያለ የሚጣራ ይመስላል።

ምክንያቱም የተላከው ሁሉ ዘረኛ ምንደኛ ጥቅመኛ ሆነ በተለይ ትልልቅ በሚባሉት ይብሳል ክርስቶስ በዘመነ ሥጋዌው ቤቴ የጸሎት ቤት እንጂ የንግድ ማዕከል አይደለም ብሎ በተደጋጋሚ አስተምሯል ዛሬ ቢመጣ ምን ብሎ የሚያስተምር ይመስላችኋል ቤቴ የጸሎት ቤት እንጂ የዘረኞች መሰባሰቢያ የዘረኞች የሌቦች ዋሻ አይደለም ብሎ የሚያስተምር ይመስለኛል ምክንያቱም ቅድመሁኔታዎቹ ይናገራሉ

እግዚአብሔር ሰው የለኝም እያለ ሲጠራ እኔ አለሁኝ በሉ

ችግሩን ጎዶሎውን አስተካክሎ ሙሉ ሰው የማድረግ ድርሻው የእግዚአብሔር ነው ነገር ግን እንደ ነቢዩ ኢሳይያስ እግዚአብሔር ሲጣራ አቤት ማለት ያስፈልጋል።

👉ብዙ ጊዜ አንዳንድ ሰዎች ችግሩ ፈተናው ጠንከር ሲልባቸው እግዚአብሔር የተዋቸው አስመስለው ሲናገሩ እንሰማለን እነሱ እግዚአብሔርን ተውት እንጂ እሱማ አልተዋቸውም እሱ ቢተዋቸውማ? ሕይወት የለም እስትንፋስ አየር የለም ሁሉ ነገር ያቆማል እጅና እግርም አይታዘዝም የሰውነት ክፍላችን እያንዳንዱ ስራ ላይ ከሆነ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር መሆኑን እናውቃለን

እግዚአብሔርማ “ባናምነው፥ እርሱ የታመነ ሆኖ ይኖራል፤ ራሱን ሊክድ አይችልም ተብሎ ተነግሮለታል ”2ኛ ጢሞ 2፥13

እግዚአብሔር ዛሬም ነገም ለዘላለም የታመነ ነው ለሁላችንም ታማኝ ልብ ያድለን 🙏🙏🙏🙏🙏🙏

አባ ገብረ ማርያም

ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, Subscribe እና Share ያድርጉ :-
ዩቱብ
https://www.youtube.com/@12Samual

ቴሌግራም
https://t.me/tsidq

tiktok
https://vm.tiktok.com/ZMBYPbBMJ/


በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ
እንዳይጠፋ አንድያ ልጁ እስኪሰጠን ድረስ ዓለሙ እንዲሁ ወዶዋልና ዮሐ 3-16)


ብዙ ሰው ብዙ ጊዜ ቃለ እግዚአብሔር ብማርም በተማርኩት ፍሬ ማፍራት አቅቶኛል ወደ ቤተ እግዚአብሔር መመላለስ እንጂ መመለስ አቅቶኛል መለወጥ ካልቻልኩ መማሩ ቢቀርብኝስ ሲሉ ይስተዋላል

ለእንዲህ አይነት ሰዎች አፈ በረከት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲ በማለት ይመክራል
አንተ ሰው

"ቃለ እግዚአብሔርን ተማር! "
ባትለወጥም ዝም ብለህ ተማር፤
ኹልጊዜ ተማር ፤
ላትስተካከል ትችላለህ፤ ላትለወጥ ትችላለህ፤ ግን ተማር!
ቢያንስ ቢያንስ ጥሩ ሰው እንኳን ባትኾን ራስህን ለመውቀስ የምትችልበት ዓቅም ታገኛለህ ።
ካልተማርክ ግን ራስህን እንኳን መውቀስ የምትችልበት ዓቅም አታገኝም ፡፡
ስለዚህ ተማር ! ስትማር ቢያንስ ኃጢአት እንኳን ስትሠራ ራስህን
እየወቀስክ ትሠራለህ ፡፡
ይህች የንስሐ በር ትኾንልሃለች ፡፡ አንድ ቀን ወደ ንስሐ ትመራሃለች ።

ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, Subscribe እና Share ያድርጉ :-
ዩቱብ
https://www.youtube.com/@12Samual

ቴሌግራም
https://t.me/tsidq

tiktok
https://vm.tiktok.com/ZMBYPbBMJ/

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.