🔷 የዶክተር ጀይላን ጓደኛ
የመካ ገጠመኜ ትውስታ
ዛሬ ጀማደ ሳኒ 21/1444 በተከረው ከተማ መካ ሐረም ላይ ከዐስር ሶላት በኋላ አንድ ከጎኔ የሰገደ እድሜው 70ዎቹ አካባቢ የሆነ ፂሙ ነጭ ሆኖ በጣም ደስ የሚል ዐረብ ስሙ ኩንያው አቡ አሕመድ ስሙ ሙሐመድ የሆነ ስው ሞቅ ባለ ፈገግታ ሰላም አለኝ ። እኔም በተመሳሳይ መለስኩለት ።
ቀጥሎ ከየት ሀገር ነህ አለኝ ከኢትዮዽያ አልኩት ። ከመጀመሪያው በበለጠ ፈገግታ ከዋና ከተማው ወይስ ከገጠሩ አለኝ እኔም ገጠር ተወልጄ ከተማ ነው ያደኩት አልኩት ። ቀጠለና ከየትኛው አቅጣጫ አለኝ ከደቡብ አልኩት ።
ወሬው ሞቅ ብሎ ቀጠለ ደቡብን አላውቀውም ወራቤን ነው የማውቀው አለኝ ‼። እኔም ወራቤ እኮ በደቡብ ነው ያለው አልኩት ። ጊዜ ማጥፋት የፈለገ አይመስልም ዶክትር ጀይላንን ታውቀዋለህ ወይ አለኝ ። እኔም በማወቅ ደረጃ አውቀዋለሁ ግን እቃረነዋለሁ አልኩት ። ያ ፈገግታ ደመና ወረሰው ።
ለምን አለኝ ከአሕባሽና ሱፍይ ጋር ስለተደመረ አልኩት ። በቃ አታውቀውም ማለት ነው ። እሱ እኮ የሐበሻ ሙፍቲ ነው አለኝ ‼ ። ደግሞም ከጃሚዓ ተመርቋል አለኝ ። እኔም ያውም በዶክተርነት ከዐቂዳ ፋካሊቲ ነው አልኩት ።
ቀጠለና አንተ ማንን ነው የምትከተለው አለኝ ? እኔም ሰለፎችን ነው አልኩት ። በጣም በሚገርም መልኩ የሰለፎች መዝሀብ ማን ነው የደነገገው አለኝ ? ሰለፎች የራሳቸው መመሪያ የላቸውም መመሪያቸው ቁርኣንና ሐዲስ ነው አልኩት ። በሙሉ ድፍረት አይደለም እናንተ ሰለፎችን ሙሸሪዕ አድረጋችኋል በዚህም ሙሽሪኮች ናችሁ አለኝ ።‼
እኔም ልቆጣጠረው የማልችለው ስሜት እየታገለኝ እንደምንም ራሴን ተቆጣጥሬ ያንተ መዝሀብ ምንድነው አልኩት ።
በቀላሉ የኢኽዋነል ሙስሊሚን መዝሀብ ነው አለኝ ።‼ ከዛ ቀጠለና አላህ ሙስሊሞች ብሎ ጠርቶናል ብሎ የቁርኣን አንቀፆችን ደረደረ ። እኔም በዐለም ላይ ያሉ ሙስሊሞች ሁሉ እስልምናቸው አንድ አይነት ነው ወይ አልኩት ? እሱም በሙሉ ድፍረት አው አለኝ ።‼
እሺ አሁን እዚህ ካዕባ ጋር ሆነው ከአላህ ውጪ ሙታኖችን የሚጠሩ አሉ የእነርሱ እስልምናና ያንተ እስልምና አንድ አይነት ነው ወይ አልኩት ? እሱም አይ የእነሱ ሽርክ ነው አለኝ ። ካፊሮች ናቸው ወይስ ሙስሊሞች ናቸው አልኩት ? እሱም እኔ ማንንም አላከፍርም አለኝ ። እሺ ሙስሊሞች ናቸው ማለት ነዋ አልኩት ። አው ጃሂሎች ናቸው እናስተምራቸዋለን አለኝ ።
በጣም ቆንጆ የጥያቄዬን መልስ ስጠኝ ያንተ እስልምናና የእነርሱ እስልምና አንድ ነው ወይ አልኩት ? ግግም ብሎ አላህ ሙስሊሞች ብሎናል አለኝ ። አው ግን ምን አይነት ሙስሊም አልኩት ? ይህ የናንተ ቢዳዓ ነው አላህ የዚህ አይነት የዚህ አይነት አላለም አለኝ ።
እኔም የኛ ቢዳዓ አይደለም የአላህ ትእዛዝ ነው ምክንያቱም አላህና መልእክተኛው እኛን የሙሀጂሮችንና የአንሷሮችን መንገድ እንድንከተል አዘውናል ብየው የሚከተለውን የቁርኣንና ሐዲስ መረጃ አመጣሁለት : –
وَالسَّابِقُونَ الْأَوَّلُونَ مِنَ الْمُهَاجِرِينَ وَالْأَنصَارِ وَالَّذِينَ اتَّبَعُوهُم بِإِحْسَانٍ رَّضِيَ اللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا عَنْهُ وَأَعَدَّ لَهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي تَحْتَهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا ۚ ذَٰلِكَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ
التوبة ( 100)
" ከስደተኞቹና ከረዳቶቹም ሲኾኑ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች እነዚያም በበጎ ሥራ የተከተሏቸው አላህ ከእነሱ ወዷል ከእርሱም ወደዋል ፡፡ በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ነዋሪዎች ሲኾኑ ለእነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል ፡፡ ይህ ታላቅ ዕድል ነው "፡፡
« وَمَن يُشَاقِقِ الرَّسُولَ مِن بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُ الْهُدَىٰ وَيَتَّبِعْ غَيْرَ سَبِيلِ الْمُؤْمِنِينَ نُوَلِّهِ مَا تَوَلَّىٰ وَنُصْلِهِ جَهَنَّمَ ۖ وَسَاءَتْ مَصِيرًا »
النساء ( 115 )
" ቅኑም መንገድ ለእርሱ ከተገለጸ በኋላ መልክተኛውን የሚጨቃጨቅና ከምእምኖቹ መንገድ ሌላ የኾነን የሚከተል ሰው (በዚህ ዓለም) በተሾመበት (ጥመት) ላይ እንሾመዋለን ፤ ገሀነምንም እናገባዋለን ፡፡ መመለሻይቱም ከፋች ! "
ከምእምኖች መንገድ ሌላ የተባለው ከሶሓቦች መንገድ ሌላ ለማለት ነው የነኛ ሰለፎች ሶሓቦች ናቸው ። የዶክተር ጓደኛ ግን ሰለፉ ሐሰነል በና ነው ።!!!
ሌላኛው እነ አቡበከርና ዑመርን መከተል ግዴታ መሆኑ ከሚያመላክቱ ሐዲሶች ውስጥ የሚከተለውን አንድ ሐዲስ ማየት በቂ ነው : –
عن العرباض بن سارية رضي الله عنه،
قال: صلى بنا رسول الله – صلى الله عليه وسلم–
" الصبح ذات يوم، ثم أقبل علينا، فوعظنا موعظة بليغة، ذرفت منها العيون، ووجلت منها القلوب، فقال قائل: يا رسول الله، كأن هذه موعظة مودع، فأوصنا،
فقال :
«
أُوصِيكُمْ بِتَقْوَى اللَّهِ، وَالسَّمْعِ وَالطَّاعَةِ، وَإِنْ كَانَ عَبْدًا حَبَشِيًّا، فَإِنَّهُ مَنْ يَعِشْ مِنْكُمْ بَعْدِي فَسَيَرَى اخْتِلَافًا كَثِيرًا، فَعَلَيْكُمْ بِسُنَّتِي وَسُنَّةِ الْخُلَفَاءِ الرَّاشِدِينَ الْمَهْدِيِّينَ، تَمَسَّكُوا بِهَا، وَعَضُّوا عَلَيْهَا بِالنَّوَاجِذِ، وَإِيَّاكُمْ وَمُحْدَثَاتِ الْأُمُورِ، فَإِنَّ كُلَّ مُحْدَثَةٍ بِدْعَةٌ، وَكُلَّ بِدْعَةٍ ضَلَالَةٌ».
أخرجه الإمام أحمد وأبو داود وغيرهما
ቀጥዬ የነብዩ ሱና ትክክለኛ እስልምና መሆኑን ታምናለህ ወይ አልኩት? አው አለኝ ። የኹለፋዎቹስ አልኩት ? ይህ የናንተ ተፍሲር ነው የሰለፎች መዝሀብ እሱ አይደለም አለኝ ።
ሰለፍ ማለት ምን ማለት ነው አልኩት ሊመልስልኝ ፈቃደኛ አልነበረም ። በጣም በሚያስጠላ መልኩ እናንተ ሰለፎችን ነው የምትገዙት በአላህ ዲን ላይ ደንጋጊ አደረጋችኋቸው አለኝ ።
እኔም አንተ የምትፈልገው ሙስሊሞችን ከአቡበከር ፣ ዑመር ፣ ዑስማንና ዐልይ ረዲየላሁ ዐንሁም መንገድ አውጥተህ ወደ ሐሰነል በናና ሰይድ ቁጥብ ፍልስፍና ማስገባት ነው ብዬው ተለያየን ።
ይህ ነው የዶክተር ጀይላን ጓደኛና ኢትዮዽያ ላይ ያሉ ሙስሊሞች ዶክተር ጀይላንን እንዲከተሉ የሚጣራው ጉደኛ
አላህ ሐቅን አውቀን የምንከተለውና ባጢልን አውቀን የምንርቀው ያድርገን ።
ከተወሰነ ጭማሪ ጋር በድጋሚ የተለቀቀ ።
https://t.me/bahruteka