ምናልባት የሆነ ቀን ላይ ከራሴ ጋር ወይም ከመንጋ ጋር ሁኜ ፤ ሆን ብዬ ወይም ሳላስበው አምቼሽ/ቼክ ይሆናል። (እስከኖርን ድረስ) የምላስ ወለምታ አይቀርም። አምቼሽ /ክ ከሆነ ይቅር ትዪኝ/ለኝ ዘንድ እመኛለሁ። በእርግጥ አላህ በሀሜት የተዘፈቀን ሰው የሚምረው የታማው አካል በይቅርታ ሲያልፈው እንደሆነ አውቂያለሁ። ይህንን መልዕክት በመዝገብ ዝርዝር ውስጥ ላሉ ሰዎች ሁሉ ልክያለሁ። ከኔ ለማስታወሻነት የተሰጠ ስጦታ ሳይሆን የሰማያትና የምድር መለኮት በእጁ የሆነውን ፈጣሪ በመፍራት ያደረግሁት ነው። ይቅር ካልከኝ /ሽኝ መልዕክቱን ደግመክ/ሽ ላክልኝ/ላኪልኝ ። የይቅርታ ጥሪ ነውና ነፍሳችንን ንፁህ እናድርገው። ይቅር በሉኝ። ድንገተኛ ሞት እጅግ በዝቷ። ለአላህ ስል ይቅር ብዬሻለሁ/ካለው። ለዚህም አላህ ምስክሬ ነው። ከረመዷን በፊት የይቅርታና የንፁህነት ጥሪ አድርጉት። ዳግም እስክንገናኝ ሰላም ሁኑ።