አንዳንዴ ለካ አሉኝ ያሉት ነገር የለም ፤ አለኝ ያሉት ራስም እንደዛው።
ጋሻ ያልናቸውም ይብሱኑ ጦር ሆነው ይወጉናል። ተራራ አድርገን የካብናቸውም ከብናኝ ዐልፈው እናያለን ።ምርጫ ያሳጡናል።
ግን አለኝ ብለን ያልጠራነው እግዚአብሔር አላችሁኝ ብሎ ይመጣል። ስላልጠራነው ሳይታዘበን መጥፎም ሳይናገረን ይመጣል።
እንደሚያስፈልገን ፤ ችግር ውስጥ እንደሆንን አውቆ ይመጣል !!! አለኝ ያልነው ቢኖር እራሱ እንደዛ እንሰከማይስተካከል ድረስ ያስተካክለውል።
ነገር ግን ብዙዎቻችን የሱ መምጫ ሊደርስ ሲል እንቆማለን ፥ ቀጣይ ምዕራፍ የሌለው ይመስለናል ፥ የቀረችንን ትንሽ ጉልበት እንኳን መጠቀም አንፈልግም ፤ ያቅተናል። ምን አልባት ትንሽ ብንሄድ ፤ ትንሽ ብናደርግ ፤ ትንሽ ብንታገስ ፥ ትልቅ እናገኝ ነበር።
@unsaid_thoughtt