🌿
ወዳጄ ሆይ!🔥
የመከራው እሳትና የጽናት በረከት 🔥በህይወትህ ፈተናና መከራ በሚበዛበት ጊዜ ከእሳቱ ለመሸሽ
አትሞክር፤ ይልቁንም ወደ እሳቱ ግባ! ከእሳቱ ውጭ ሆነህ በሩቁ አትቁም። ምክንያቱም በዚያ በፈተናና በድሃነት እሳት ውስጥ ሆነህ ከጸናህ፣ እሳቱ ያጠራሃል እንጂ አያቃጥልህም፤ ድሃነትና መከራም ካንተ ዘንድ ይርቃል። ከፈተናውና ከእሳቱ ርቀህ ልቀመጥ ብትል ግን፣ ፈተናው ድንገት ይደርስብሃል፣ ፈጥኖም ይይዝሃል። ከፈተና እሳትና ከድሃነት ከሚታገሉ ቅዱሳን ሰዎች ርቀህ አትቁም!
🛡️
የእውነተኛ እምነትና የጽናት ፍሬዲያብሎስ ለገንዘብና ለንብረት ባለመስገዳቸው ምክንያት ሰዎችን ወደ ድሃነትና ወደ ፈተና እሳት ሲጥላቸው ስታይ፣ እሳቱን ፈርተህ አትሸሽ! ይልቁንም ወደ እሳቱ ገብተው እንደ ወርቅ ከሚጠሩት ወገኖች አንዱ ሁን እንጂ፣ እሳቱን አብዝተው ወደሚጥሉትና ሰዎችን ወደሚፈትኑት ወገን አትሁንም።
ይህንን ያደረግህ እንደሆነ፡
👉ከሚቃጠሉትና ከሚጠፉት ወገን ሳይሆን፣
👉ከእሳቱ ቃጠሎ አምልጠው ከሚድኑትና ከሚከብሩት ወገን ትሆናለህ!
💎
የገንዘብ ፍቅርን ማሸነፍና ሰላምወዳጄ ሆይ! ለገንዘብ አለመገዛትና የገንዘብ ፍቅርን ከአእምሮ ማራቅ፣ እንዲሁም በድሃነትና በፈተና ውስጥ ካሉት ቅዱሳን ጋር አንድነትን መፍጠር— በውነት ያለ ሐሰት ታላቅ ጤና፣ ሰላም እና እውነተኛ ዕረፍት ነው!
በዓለም ያሉ ባለጠጎች ሳይሆኑ፣ እውነተኛ ባለጠጎች የሚባሉት የገንዘብ ፍቅርን በእግራቸው ሥር የረገጡት ናቸው!
🔥
የሦስቱ ደቂቅ ድንቅ አርአያነት፡በባቢሎን የነበሩት ሦስቱ ደቂቅ (ሲድራቅ፣ ሚሳቅ፣ አብደናጎ) የንጉሱን ትእዛዝ አንቀበልም፣ ለጣኦትም አንሰግድም ብለው በእምነታቸው በመጽናታቸው— ከንጉሡ ይልቅ እጅግ የተከበሩና የታወቁ ሆኑ!
✨
አንተም ወዳጄ ሆይ!የነዚህን አበው አርአያነት ተከተል! በፈተናና በመከራ ውስጥ ብታልፍ እንኳ በእምነትህ ፅና፤ የዓለምን ከንቱ ሀብትና ንብረት ረግጠህ እውነተኛውን ሰማያዊ ክብር አትርፍ! 🕊️✨
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ❣️
✍️ / ዑራኤል