Variety Ethiopia


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


𝙫𝙖𝙧𝙞𝙚𝙩𝙮
💥አስደናቂ እውነታዎች
💥ቴክኖሎጂ
💥ታዋቂ ሰዎች እና አስገራሚ ታሪኮቻቸው
ሁሉንም በአንድ !!
✅ ማስታወቂያ
✅ ሃሳብ
✅ ጥያቄ
በ 👉 @variety_Ethiopiabot ያስቀምጡልን
ስለ ክሪፕቶ @variety_Ethiopiacrypto ይጎብኙ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


አስደናቂ የዓለም እውነታዎች

እንስሳት፡-
በምድር ላይ ትልቁ እንስሳ የሰማያዊ ዓሣ ነባሪ ልብ፣  እስከ 400 ኪ.ግ (ወደ 880 ፓውንድ) ሊመዝን ይችላል፣ እና የልብ ምቱ በውሃ ውስጥ ከ2 ማይል ርቀት ላይ መስማት ይቻላል።

ተክሎች፡-
ሸምበቆ በምድር ላይ በፍጥነት የሚያድግ ተክል ነው።
አንዳንድ ዝርያዎች በአንድ ቀን ውስጥ እስከ 91 ሴ.ሜ (35 ኢንች) ያድጋሉ።

የሰው ልጅ አጥንት፡-
የተወለድከው 300 የሚያህሉ አጥንቶች ይዘህ ነው፡ ነገር ግን አዋቂ ስትሆን 206 ብቻ ነው ያለህ።

የአማዞን የዝናብ ደን፡
"የምድር ሳንባ" ተብሎ የሚጠራው አማዞን 20% የሚሆነውን የዓለም የኦክስጂን መጠን ያመርታል።

ዛፎች እና ግንኙነታቸው፡-
አንዳንድ ዛፎች እርስ በርሳቸው ሊግባቡ ይችላሉ። "ማይኮርራይዝል ኔትወርኮች" በመባል በሚታወቀው የፈንገስ ኔትወርክ አማካኝነት ዛፎች ንጥረ ምግቦችን ይጋራሉ አልፎ ተርፎም በተባይ በሽታ ሲጠቁ የጭንቀት ሲግናል ይልካሉ።

@variety_ethiopia


ዛሬ ዓለም አቀፍ የምግብ ቀን ነው።
ረሃብን ከሀገራችን ያጥፋልን!

@variety_ethiopia


የ 8 ጊዜ Ballon d'or አሸናፊው ሜሲ ሙሉ ስሙ Lionel Andrés Messi Cuccittini ነው።

@variety_ethiopia


🏆Champions League × 4

🏆LaLiga ×10
 
🏆Copa
del Rey× 7

🏆Club
World Cup× 3

🏆European
Super Cup× 3

🏆Supercopa
de España ×8

🏆Ligue 1 ×2
 
🏆Trophée des Champions ×1

INTER MIAMI

🏆Leagues
Cup ×1

🏆Copa
América ×1

🏆U-20
World Cup ×1

🏆Beijing
Olympic Games
Gold Medal ×1

🏆FIFA
World Cup ×1

🏆Finalissima ×1


👉ከስፔን አርጀንቲናን መምረጡ
ሜሲ የስፔን እና የትውልድ ሀገሩ አርጀንቲና ፓስፖርት ያለው ሲሆን ከስፔን ብሄራዊ ቡድን ጋር የመጫወት ዕድል ሰጥተውት ሳይቀበለው ቀርቷል። ምንም እንኳን ብዙ የልጅነት አመታትን በስፔን ቢያሳልፍም እራሱን እንደ አርጀንቲናዊ ስለሚቆጥር አልተበለም ነበር።

👉የባርሴሎና ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ
ሜሲ በሁሉም ወድድሮች የባርሴሎና የምንግዜም ኮከብ ግብ አግቢ የሆነው እ.ኤ.አ. በ 2012 ገና በ 24 ዓመቱ ነበር።

👉ከፍተኛው የኤልክላሲኮ ባለ ጎል እና አሲስት
ሊዮኔል ሜሲ በኤል ክላሲኮ (ሪያል ማድሪድ vs ባርሴሎና) ታሪክ ብዙ ጎል በማስቆጠር እና አሲስት በማድረግ ሪከርዱ በእጁ ነው።

👉በአንድ ዓመት 91 ግብ ያስቆጠረ
እ.ኤ.አ. በ 2012 ሜሲ በአንድ የውድድር አመት ብዙ ጎል በማስቆጠር ሪከርዱን የሰበረ ሲሆን ይህም ቀደም ሲል በጌርድ ሙለር በ 1972 በ 85 ተይዞ ነበር።

👉የአርጀንቲና ከፍተኛ አግቢ
ሜሲ ለክለቡ እና ለሀገሩ አስደናቂ 365 በላይ አሲስቶችን አድርጓል።
ለአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን (106 ኢንተርናሽናል ጎሎች) የምንግዜም መሪ ነው(በተጨማሪ ትላንት 3 ጎልና 2 አሲስት)።


👉80% ግቦቹ በግራ እግር ተቆጠሩ
በግራ እግሩ 660 በላይ ጎሎችን ሲያስቆጥር በቀኝ እግሩ 16% ጎሎችን እና 26 የጭንቅላት ኳሶችን አስቆጥሯል።

#GOAT 🐐
#Messi
@variety_ethiopia


የእግርኳሱ ንጉስ ሜሲ አስደናቂ እውነታዎች

👉ቤተሰቦቹ ደሃ ነበሩ
አባቱ በብረት ፋብሪካ ውስጥ ይሠራ ነበር, እናቱ ደግሞ የትርፍ ሰዓት ጽዳት ሰራተኛ ነበረች።

👉ሜሲ ቼ ጉቬራ
ሜሲ ሰኔ 24 ቀን 1987 በሮዛሪዮ ፣ አርጀንቲና ተወለደ። ሜሲ የትውልድ ቦታውን እና የትውልድ ወሩን ከአርጀንቲና አብዮታዊ ቼ ጉቬራ ጋር ይጋራል።

👉የእድገት ሆርሞን እጥረት ነበረበት
ሜሲ በልጅነቱ እንደሌሎች ወንዶች ልጆች በጣም ጤናማ እና ጠንካራ አልነበረም።
የዕድገት ሆርሞን እጥረት እንዳለበት በምርመራ ተረጋገጠ በ11 አመቱ መደበኛ እድገቱን እያቆመ ሄደ። የህክምናው ወጪበወር 900 ዶላር ስለነበር ወላጆቹ  መሸፈን አልቻሉም ነበር። በ 13 አመቱ የሜሲ ተሰጥኦ የ FC ባርሴሎናን ትኩረት ስቦ ነበር እና የወጣት አካዳሚያቸውን ላ ማሲያ ከተቀላቀለ የህክምና ወጪውን ለመሸፈን ጥያቄ አቀረቡ። ሜሲ ከዚያ በኋላ ባርሴሎና እግርኳስ ክለብ ነበር ያሳከመው።


አንዳንዶች ፤ " አሁን ባለው ስርዓት በከፍተኛ ጫና ውስጥ ወድቀው ነው እየሰሩ ያሉት ፤ በተለያዩ ጉዳዮች አለመግባባት ውስጥም እንደነበሩ ብዙ ጊዜ በሚዲያ ይሰማ ነበር ፤ ለመናገር እንኳን እድል የላቸውም ፤ ባገኙት አጋጣሚ ግን በገደምዳሜው ስሜታቸውን ስለ ሀገራቸው ይናገሩ ነበር ፤ አሁንም ቦታውን ሲለቁ ስለዚህ ስርዓት ብዙ የሚናገሩት ይኖር ይሆናል " የሚል አስተያየት ሰጥተዋል።

አንዳንዶች፤ " በዚህ ልክ ትልቅ የስልጣን እርከን ይዘው ህዝብን ግራ የሚያጋባ ድፍንፍን ያለ ፅሁፍ በገጻቸው መጋራቱ ሳያንስ እውነትም እሳቸው መሆናቸውን በግልጽ አለማብራራታቸው ትክክል አይደለም ፤ ችግር ካለም እውነታውን ለህዝብ ማሳወቅ አለባቸው እንዲህ የዘፈን ግጥም ከሚያስቀምጡ " ብለዋል።

ሌሎች አስተያየት ሰጪዎች ደግሞ " የ6 ዓመት የስልጣን ዘመናቸው ሲያበቃ ይህን አይነት ነገር በገጻቸው መፃፋቸው የህዝብ ተቀባይነት ለማግኘት ነው እስከዛሬ በሀገሪቱ ብዙ ነገር ብዙ ግፍ ሲፈጠር ባላየ ሲያልፉ ነበር ፤ አንዳንዱን ደግሞ እየመረጡ ሲናገሩ ነበር ፤ ለምን አሁን ? በዚህ ስልጣን እንደማይቀጥሉ ስለሚያውቁ ነው ፤ ስልጣንም መልቀቅ ከነበረባቸው ቀድሞ ተናግሮ እንጂ አሁን ላይ ይህን አጀንዳ ለህዝብ መስጠት ትክክል አይደለም ፤ ጊዜያቸው አብቅቷል ይሰናበታሉ ፤ እሱንም ስለሚያውቁ ነው " ሲሉ ፅፈዋል።

በኢትዮጵያ የፕሬዜዳንት ስልጣን ዘመን 6 ዓመት ሲሆን ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ወደ ስልጣን የመጡት ጥቅምት 15 ቀን 2011 ዓ/ም ላይ ነበር።

ሌሎች ደግሞ " እንዲያው በደፈናው ድምዳሜ ላይ ከመድረስ የእሳቸውን ሙሉ ሀሳብ በትዕግስት ጠብቆ መስማት ይገባል " ብለዋል።

ከዚህ ባለፈ ግን ለመሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥ የፕሬዝዳንትነት የስልጣን ድርሻው ምንድነው ? ፕሬዝዳንት የሚኮነው እንዴት ነው ? ምን ምን ይሰራል በዝርዝር ? ሲሉ የጠየቁ አሉ።

ለዚህ ምላሽ ይሆን ዘንድ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ህገ መንግስቱ ስለ ፕሬዜዳንቱ የሚለውን ከዚህ በታች አቅርቧል።

የኢፌዲሪ ህገ መንግስት ስለ ሪፐብሊኩ ፕሬዝዳንት ስልጣንና ተግባር ምን ይላል ?

(የኢፌዴሪ ህገ መንግስት)

ምዕራፍ ሰባት
ስለ ሪፐብሊኩ ኘሬዚዳንት
አንቀጽ 69
ስለ ኘሬዚዳንቱ

ኘሬዚዳንቱ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ርዕሰ ብሔር ነው፡፡

አንቀጽ 70
የፕሬዜዳንቱ አሰያየም
1. ለፕሬዜዳንትነት ዕጩ የማቅረብ ሥልጣን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው።
2. የቀረበው ዕጩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና በፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ በሁለት ሦስተኛ ድምጽ ከተደገፈ ፕሬዜዳንት ይሆናል።
3. የምክር ቤት አባል ፕሬዜዳንት ሆኖ ከተመረጠ የተወከለበትን ምክር ቤት ወንበር ይለቃል።
4. የፕሬዜዳንቱ የሥራ ዘመን 6 ዓመት ነው። አንድ ሰው ከሁለት ጊዜ በላይ ለፕሬዜዳንትነት ሊመረጥ አይችልም።

አንቀጽ 71
የኘሬዚዳንቱ ሥልጣንና ተግባር
1. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽኑን ምክር ቤት ዓመታዊ የጋራ ስብሰበባ ይከፍታል፡፡
2. በዚህ ሕገ መንግሥት መሰረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያጸደቃቸው ሕጐችና ዓለምአቀፍ ስምምነቶች በነጋሪት ጋዜጣ ያውጀል፡፡
3. ሀገሪቷን በውጭ ሀገሮች የሚወክሉትን አምባሳደሮችና ሌሎች መልክተኞች በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት ይሾማል፡፡
4. የውጭ ሀገር አምሳደሮችንና የልዩ መልዕክተኞችን የሹመት ደብዳቤ ይቀበላል፡፡
5. በሕግ መሰረት ኒሻኖች እና ሽልማቶችን ይሰጣል፡፡
6. በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በሕግ በተወሰነው መሰረት ከፍተኛ የውትድርና ማዕረጐችን ይሰጣል፡፡
7. በሕግ መሰረት ይቅርታ ያደርጋል፡፡
-TikvahEthiopia

@variety_ethiopia


#ኢትዮጵያ

ዛሬ በኢትዮጵያ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ትልቅ መነጋገሪያ የሆነው በፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ X ኦፊሻል ገጽ ላይ የሰፈረው ፅሁፍ ነው።

ፅሁፉ ላይ የማህሙድን ዘፈን ' ዝምታ ነው መልሴ 'ን በማንሳት " የሰው ልጅ ሆዱ ሲከፋው ጊዜም እንደ ሰው ሲገፋው: መሄጃ መውጫ ሲጠፋው ዝምታ ብቻ ነው ተስፋው " የሚለው ግጥም ተጋርቷል። መጨረሻ ላይ " ለአንድ አመት ሞከርኩ " የሚልም ሰፍሯል።

ፅሁፉ ስለምን ጉዳይ እንደሆነ ፤ ለምንስ ይህንን ግጥም ነጥሎ እንደተጻፈ በግልጽ የሚያብራራው ነገር የለም።

ያም ሆኖ ግን ፅሁፉን ላይ በርካቶች የየራሳቸውን አስተያየት እየሰጡ ይገኛሉ።


While we patiently wait for Google to approve the latest Telegram update, let’s take a break for some nostalgia 👨‍🦳

Here’s my eldest daughter instructing me on how to launch Telegram in the summer of 2013. She’s the real brain behind this whole thing, folks

-Pavel Durov




#DV2026

የ2026 የአሜሪካ ዳይቨርሲቲ ቪዛ DV ለማመልከት https://dvprogram.state.gov/ ይጠቀሙ።
ምንም አይነት ክፍያ አያስፈልጋችሁም።
ከአንድ ጊዜ በላይ እንዳትሞሉ በተጨማሪ ፎቷችሁ ከጀርባ ነጭ background ይኑረው።


#DV2026

የ 2026 የአሜሪካ ዳይቨርሲቲ ቪዛ (Diversity visa) ማመልከቻ ከዛሬ ጀምሮ እስከ Nov. 5/24 ድረስ ማመልከት ትችላላችሁ።

@variety_ethiopia


1⃣ Capability ላይ በመመስረት በሦስት የከፈልነው ሲሆን

2⃣ደግሞ በFunctionality ላይ በመመስረት 4 ዓይነቶችን የምናነሳ ይሆናል
እነዚህንና ምሳሌዎችን ካነሳን በኋላ እንዴት መጠቀም እንደምትችሉና የተለያዩ ነገሮችን በai ማከናወን እንደምትችሉ (ለምሳሌ እዚህ ቻናል ላይ ያለው ሎጎ በai የተሠራ ነው) እናያለን።

ይህ ፖስት 5 👍 ካገኘ የምንቀጥል ይሆናል።

@variety_ethiopia
@variety_ethiopia


የቀጠለ...
አሁን ላይ አንዳንድ ሳይንቲስቶች በአቅም ላይ በመመስረት (based on capability)፡ ከላይ ከጠቀስኳቸው ከሁለቱ በተጨማሪ የወደፊቱንም በማሰብ በ3ተኛነት የሚቀበሉት አለ

3. Super AI
ይህ በሁሉም ረገድ የሰውን ልጅ የማሰብ ችሎታ የሚበልጠው የወደፊቱ AI ነው - በፈጠራ፣ በማህበራዊ እና በሳይንሳዊ በሁሉም ተግባራት ውስጥ ከሰዎች ሊበልጥ የሚችል የAI አይነት ነው።
በእርግጥ ገና አልተሳካም ነገር ግን ብዙ ጊዜ በሳይንስ ልብ ወለድ እንደሚጻፈው AI ከሰዎች ቁጥጥር ውጪ ራሱን የቻለ ውሳኔ የማድረግ ችሎታ ያለው እንዲሆን የሚያደርግ የAI አይነት ነው።
ይቀጥላል...

ጽሑፉ እንዲቀጥል react በማድረግ ሀሳባችሁን ግለጹልኝ 🙏

@variety_ethiopia


አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI)
AI የሰውን የማሰብ ሂደቶችን በማሽኖች በተለይም በኮምፒተር ሲስተሞች ማስመሰልን ያመለክታል።
ይህ እንደ መማር (በተሞክሮ ላይ በመመስረት አፈፃፀሙን የማሻሻል ችሎታ) ፣ ማመዛዘን (መደምደሚያ የማድረግ ችሎታ) እና ራስን ማስተካከልን ያጠቃልላል።
AI በሁለት ዋና ዋና ዓይነቶች ሊከፈል ይችላል-


1. Narrow AI፡ እንደ ምናባዊ ረዳቶች ወይም የምክር ስርዓቶች ለተወሰኑ ተግባራት(specific tasks)የተነደፈ ነው።



2. General AI፡ አንድ ሰው ሊያደርገው የሚችለውን ማንኛውንም የአእምሮ ስራ የመረዳት እና የመማር ችሎታ ያለው የAI ቲዎሬቲካል ቅርጽ ነው።

AI ቴክኖሎጂዎች የማሽን መማርን፣ የተፈጥሮ ቋንቋን ማቀነባበር እና ሮቦቲክስን እና ሌሎችንም ያካትታሉ።

@variety_ethiopia


ሰላም የVariety Ethiopia ቤተሰቦች !

ከዚህ በኋላ የcrypto ጉዳዮችን በዚህኛው ቻናል አንለቅም።
ስለክሪፕቶ የምናወራበት VARIETY CRYPTO ተብሎ የተሰየመ አዲስ ቻናል ከፍተናል የቻናሉን members ለማሳደግ በመቀላቀልና ሼር በማድረግ እንድትተባበሩን እንጠይቃችኋለን 🙏
ስለክሪፕቶ ትኩስ መረጃዎችን የምታገኙባቸውን ወሳኝ ገጾች የጠቆምን ሲሆን ገብታችሁ check አድርጓቸው።
በተጨማሪ ይሄኛው ቻናል ከክሪፕቶ ውጪ ሌሎች ይዘቶቹን ሰፋ በማድረግ የሚቀጥል ይሆናል።
የቻናሉ ሊንክ
https://t.me/variety_ethiopiacrypto


ተጠናቋል።


CATS🐈  አዲስ መረጃ አጋርተዋል

በመተግበሪያው ቴክኒካል ችግሮች ምክንያት snapshot  ጊዜውን ለተጨማሪ 3 ቀናት አራዝሟል።

የመጨረሻው snapshot ወደ ኦክቶበር 3 ተራዝሟል።
ይህ ደግሞ መስፈርቶቹን ለማሟላት ተጨማሪ ጊዜ ይሰጣችኋል።

በባይቢት ተቀማጭ አድራሻ ላይ ያለው የP.S ችግር ተፈቷል፣አሁን CATS token በባይቢት ማገናፕት ትችላላችሁ ብለዋል።

#cats እንደሚታወቀው በታስክ ነው token የሚሰጡት ስለዚ ዛሬ ብትጀምሩ ከቆዩት ጋር ብዙም የcoin ልዩነት አይኖራችሁም ስለዚህ በዚህ 2 እና 3 ቀን በቀን አንዴ ገብታችሁ ብትሠሩ ምንም አትከስሩም።

ጀምሩት
http://t.me/catsgang_bot/join?startapp=fLJvKLDKc3ttDTGdImEVZ

@variety_ethiopia


ለምንድነው ያልመረጣችሁት ?

👍 ማገናኘት አልቻልኩበትም
🔥ማገናኘት አልፈለኩም


ጎግል የቀድሞ ተመራማሪውን ኖአም ሻዚርን በ2.7 ቢሊዮን ዶላር ውል በድጋሚ ቀጥሮበታል ሲል ዎል ስትሪት ጆርናል ዘግቧል።  ሻዚር ከ21 ዓመታት በኋላ ጎግልን በ2021 ለቆ የወጣው ኩባንያው የሰራውን ቻትቦት ለመክፈት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ነው።  ከዚያም ሻዚር ከአንዳንድ ሰዎች ጋር ሆኖ Character.AI መስርቷል.

Character.AI ባለፈው አመት በ 1 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ተገምቶአል.  የጉግል ስምምነት የ Character.AI ቴክኖሎጂን ማተቃለል እና ሻዚርን የጂሚኒ ቻትቦትን ጨምሮ የ AI ፕሮጄክቶቹን እንዲመራ ማድረግን ያካትታል።  ይህ እርምጃ ትላልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ከፍተኛ የAI ተሰጥኦዎችን ለመቅጠር የሚያደርጉትን ተመሳሳይ ጥረት ያሳያል።

$2.7B አስባቹታል 🤑

-Techdrop insights

@variety_ethiopia

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.