Postlar filtri


ፋሽስታዊ ሀይሉ ዛሬ በራያ በተለምዶ ጥሙጋ በሚባል አካባቢ ከ40 አመታት በላይ በመርጌታነት ያገለግሉ የቤተክርስቲያኒቱን ሙህር (አይነ ስውር ናቸው) ጨምሮ ከእርሳቸው ጋር የነበሩ 4 ዲያቆናትን በአደባባይ ረሽኗል!! እንደነዚህ ያሉ iconic ሰዎችን መረሸን የአገዛዙን ጥልቅ ፍላጎት የሚያስረዳ ነው!!


የአገዛዙ ታጣቂ ዛሬ በጎንደር የተለያዩ ቀጠናዎች በመድፍና በዙ 23 የታገዙ ውጊያዎች የከፈተ ቢሆንም የጎንደር ፋኖዎች የአጠፋ ምላሽ እየሰጡ ይገኛል!! አገዛዙ ግንባሮችን በማብዛት ሰፊ ቀጠና ላይ ውጊያ ለማድረግ እየሞከረ ነው፤ ውጤቱን በቅርቡ የምናየው ይሆናል!! በአሁን ጥቃት ለየት የሚለው ነገር አገዛዙ በደረሰባቸው ቦታዎች ሁሉ የግልና የመንግስት ንብረቶችን በተቀናጀ ሁኔታ ለመዝረፍ ሙከራ እያደረገ ነው። ዛሬ 3 የአርሶ አደር ትራክተሮችን ጭኖ ለመውሰድ ሲሞክር በፋኖ ሀይል ተመትቶ ጥሎ ሸሽቷል


የአገዛዙ ታጣቂ አርባያ ከተማ ገባ ተብሎ በአገዛዙ ሚዲያ በሰበር ሲራገብ ውሏል! አሁን ከመሼ እንደሚደርሱኝ መረጃዎች ከሆነ ወደዚያ የገባው የፋሽስቱ ታጣቂ ከጥቅም ውጭ ተደርጓል! የተረፈው ከተማዋን ለቆ ፈርጥጧል!
ፋኖ 💪


በድርጅት ያልታቀፉ የፋኖ አደረጃጀቶች ምን ያህል ጊዜ ብንጠብቃቸው ድርጅት ይመሰርታሉ!? አልያም በተቋቋመው ይገባሉ!?
እኛ እንዴት እናግዛቸው ጎበዝ!? ወይ ፍጠሩ ወይ ተቀላቀሉ? እናሸንፋለን! እናቸንፋለን አይነት ነገር አታውሩ! አንድ ቀን በሄደ ቁጥር የህዝቡ መከራ ይብሳል!!


ጥያቄ?
ፋኖ አገዛዙ በሚዘውረው ፓርላማ አሸባሪ ተብሎ ተፈርጇል? ወይስ?


እንኳን ለመላው የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ቀን አድዋ 129ኛ የመታሰቢያ ቀን አደረሳችሁ!


''ዘመቻ አርበኛ ኮሎኔል ታደሰ እሸቴ
በአድዋ ዕለት በይፋ ተጀምሯል!!''
የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር

መንገኝነት ይወደም
ምክንያታዊነት ይቅደም


ጥያቄ?
ዛሬ የጦር መሀንዲሱ ኮ/ል ታደሰ እሸቴ በጋይንት ግንባር እንደተሰዋ እየሰማን ነው፤ ከወራት በፊት በስልክ አዋርቻቸው አውቃለሁ! በቅርብ አውቃቸዋለሁ እያልኳችሁ ነው!! እንግዲህ ስለ ኮሎኔል ጀግንነትና ለአማራ ህዝብ የከፈሉትን መስዋዕትነት ልነግራችሁ አልችልም። ታሪክ በራሱ ማህደር ይመዘግበዋል።
ጥያቄየ እርሳቸው ውድ ህይወታቸውን የከፈሉበትን ድርጅት ትግል ጠላፊ ነው እያልን እንዴት እንማው ነው?

Guys be rational!


በነገራችን ላይ ብዙ ኢትዮጵያዊያን የሚዲያ ሰዎች ስለዩክሬንና ራሺያ ጦርነት ውጤት የተዛባ መረጃ ለህዝቡ እያጋሩ ይገኛሉ!! የተሳሳተ መረጃ ለህዝብ ማድረስ የተዛባ የፖለቲካ አመለካከት እንዲኖረው ያደርጋል!
እውነቱ ዩክሬይን ጦርነቱን ልታሸንፍ ጫፍ ደርሳ ነበር፤ ለራሺያ አምላክ ትራንፕ የሚባል ሙሴ ላከላቸው እንጂ!!
ይሄን ምርመራ በፅሞና ብታነቡ ስለሁኔታው በቂ ግንዛቤ ይኖራችኋል!!
ይሔን 👇
https://understandingwar.org/backgrounder/russias-weakness-offers-leverage

አንብቡት


ለምትሰሩት እያንዳንዱ ሀፂያት ሰይጣንን ተጠያቂ ማድረግ አቁሙ!!


የመጨረሻው መጀመሪያ!
የአማራ ህዝብ ብሩህ ተስፋ ወይም ድቅድቅ ጨለማ ከፊቱ ይጠብቀዋል!! የአባቶቻችን ልጆች በመሆን አይበገሬነታችን አስመስክረናል!! በፊታችን የሚቆም ክንዳችን የሚቋቋም ሀይል እንደሌለ እሙን ነው። ግን.....
1) ወጥ የሆነ የፖለቲካና የሚሊታሪ አደረጃጀት መፍጠረን አልቻልነም። ለምን?

2) አይናችን ከዋናው ጠላታችን እያነሳን ወደ እርስ በእርስ የጎንዮሽ ፍትጊያ እየተገባ ነው። ለምን?

3) ወታደሩ አንድ አቋም እያለው ለምን መሪዎቹ ተለያዩ? የሚዲያ ሰዎች ለምን ጎራ ለየን?

4) የሀይል አሰላለፍ ግምገማ ተደርጎ እንዴ alliance መፍጠር ተሳነን?

5) ዲያስፖራው ለምን ለሚጨፈጨፈው የአማራ ህዝብ ድምፅ መሆኑን አቆመ?

ወዘተ

ተወቃሾቹ እኛው ነን!! አንተም ጭምር

9.8k 0 5 13 104

እስቲ ያነበባችሁ ብቻ መልሱልኝ!!
አባታችን ፕሮፌሰር አስራት በወቅቱ ተቀባይነት ያጡት ለምን ነበር? ምንስ ተብሎ ነበር ፕሮፖጋንዳ የሚሰራባቸው!?


በገፋንበት እጃችን ዋጋውን እናገኝ ይሆናል!


በሰጠነው ጥቆማ መሰረት በአንዳንድ አካባቢዎች በፋኖ ስምና በአገዛዙ ስምሪት ተሰጥቷቸው የማዘርፉ፣ የሚያግቱና የሚረሽኑ ላይ ፋኖ እርምጃ መውሰድ ጀምሯል፤ ከባህርዳር ወደ ደብረታቦር መስመር ልዩ ስሙ አለም ሳጋ በሚባል ቦታ ተጓዦችን ለመዝረፍ ሙከራ ባደረጉት ላይ በተወሰደ እርምጃ ከ5 በላይ የሚሆኑ ተደምስሰዋል! ሁለቱ እጅ ሰጥተዋል!! ይህ በሁሉም የአማራ ግዛት ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል!

ፋኖ 💪


የአማራን እርስቶች ለህውሃት አስረክቦ እርቅ ለማድረግ ፕሪቶሪያ፣ ናይሮቪ እና ሀላላ ኬላ ላይ የተወያዩት ኦነግና ህውሃት ውጥናቸው በፋኖ ብርቱ ትግል ከሽፏል!! ከአማራ ልዩ ሀይል በመጀመር ሁሉንም የአማራ አደረጃጀቶች ትጥቅ በማስፈታት እርስቶቹን ያለከልካይ ለወያኔ ማስረከብ ቅዤት እንደሆነ ሲረዱ ዛሬ እርስ በእርሳቸው ለግድያ የሚፈላለጉ ሆኑ!! ይህ በአንድ ቀን [ምርጫ ቦርድና የአምገነኑ የመከላከያ ውይይት] የሚሉትን ተመልከቱ!!

እንዲህ በሚቀያየሩ ሁኔታዎች ውስጥ የአማራ ህዝብ መከራ እንዳይራዘም ፋኖ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አንድነቱን አጠናክሮ አሸናፊ ሀይል ሁኖ የሚወጣበትን እድል መፍጠር ይኖርበታል!! እንዲህ እየተነታረከ የሚቀጥል ከሆነ ህዝቡን ከባድ ዋጋ ያስከፍለዋል!!
ልብ በሉ
ሁለቱ የአማራ ጠላቶች እርስ በእርሳቸው ከገጠሙ ሜዳው የአማራ ቀየ ነው የሚሆነው!!


ዛሬ በቤተ አማራ ወራሪውና ጨፍጫፊው የአብይ አህመድ ታጣቂ በሚገባ ተመትቷል፤ ትናንት የጀመረው ውጊያ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል። ፋኖ በትንሽ መስዋትነት እጅግ የገዘፈ ድል ተቀዳጅቷል!! በዚህ የደነበረው አገዛዙ በመሰረተ ልማቶች ላይ የድሮን ጥቃት በመፈፀም ህፃናትን ጨምሮ በርካታ ንፁሓንን ጨፍጭፏል!


ሰላም እንዴት አመሻችሁ!! በርካቶቻችሁ የክልሉን ውሎ የተመለከ መረጃ እንዳደርሳችሁ ጠይቃችሁኛል። ይሁን እንጂ እኔ በዚህ ወደ እናንተ የማደርሰው መረጃ የእናንተው ነውና እንደከዚህ ቀደሙ በአዲሱ እንጀምራለን!! ነገር ግን በተጠናከረ መንገድ መረጃ ማድረስ ያልቻልነው በአገዛዙ የሳይቨር ጥቃት ምክንያት እንጂ እኛ ሰልችተን የህዝባችን ግፍና መከራ ረስተን አለመሆኑ ይታወቅልን!!

ከዛሬ ጀምሮ በዚች አድራሻ መረጃ፣ ጥቆማና አስተያየት አድርሱ!
@VMg_offical


ህዝባዊ ድጋፋን ማጣት ሊያመጡ የሚችሉ ክስተቶች!

1) ለአንድነት ቆራጥ ሁኖ መገኘትና በአጭር ጊዜ የመቀራረብ ነገሮችን ህዝቡ ካላየ
2) ፋኖ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች [በፋኖ ስም የሚዘርፉ፤ በአገዛዙ ተደራጅተው የሚዘርፉ፣ የሚገሉ እና የሚያግቱ] ሀይሎችን እርምጃ ወስዶ ህዝቡ እፎይታ አግኝቶ በነፃነት መንቀሳቀስ ካልቻለ

3) የጎንዮሽ መገፋፋትን [አንዳንድ ቦታዎች ታይተዋል] በስፋት የሚታዩ ከሆነ

4) እንደፋኖ የሚጠበቅበትን የፖለቲካ፣ የፕሮፓጋንዳ እና ወታደራዊ ስራዎችን በተሻለ ፍጥነት የማይከውን ከሆነ

ወዘተ


ከአራቱም የአማራ አካባቢዎች ጎንደር ብቻ ለምንድን ነው የዝርፊያ፣ እገታና ግድያ የተበራከተው!? ከጎንደር ከተማ ተነስተን ወደ ሁሉም አቅጣጫ ብንጓዝ፤ ከባህርዳር ተነስተን ደብረታቦር ጋይንት አቅጣጫ ብንጓዝ የመዘረፍ ዕድልህ እጅግ ከፍተኛ ነው። እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው ንፁሓን ተጓዦች በታጣቂ ይረሸናሉ!! እንዴት ሁሉም ጎንደር ቦታ እንዲህ የምድር ሲዖል ሊሆን ቻለ?


ብሔርተኛ ነን ባዮች ግን ስለብሔርተኝነት ምንም የማያውቁ ደናቁርቶች ለአማራ ብሔርተኝነት ትልቅ እንቅፋት ናቸው፤ የተገኘውን ሁሉ ማኘክ አደጋ ይኖረዋል!!

ስለምን እንደሆን የምትረዱኝ ይመስለኛል!!

11k 0 0 14 61
20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.