ቃቢል
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
5፥27 በእነርሱም ላይ የአደምን ሁለት ልጆች ወሬ ቁርባንን ባቀረቡ እና አሏህ ከአንደኛቸው ተቀብሎ ከሌላው ባልተቀበለ ጊዜ የኾነውን በእውነት አንብብላቸው፡፡ وَاتْلُ عَلَيْهِمْ نَبَأَ ابْنَيْ آدَمَ بِالْحَقِّ إِذْ قَرَّبَا قُرْبَانًا فَتُقُبِّلَ مِنْ أَحَدِهِمَا وَلَمْ يُتَقَبَّلْ مِنَ الْآخَرِ
በባይብል በግልጽ እና በማያሻማ መልኩ አዳም ከሚስቱ ከሔዋን ጋር ተራክቦ በመፈጸም የበኵር ልጅ ቃየን ፀንሳ ወለደች፦
ዘፍጥረት 4፥1 አዳምም ሚስቱን ሔዋንን አወቀ፤ ፀነሰችም፥ ቃየንንም ወለደች። እርስዋም፦ “ወንድ ልጅ ከያህዌህ አገኘሁ” አለች። וְהָ֣אָדָ֔ם יָדַ֖ע אֶת־חַוָּ֣ה אִשְׁתֹּ֑ו וַתַּ֙הַר֙ וַתֵּ֣לֶד אֶת־קַ֔יִן וַתֹּ֕אמֶר קָנִ֥יתִי אִ֖ישׁ אֶת־יְהוָֽה׃
እዚህ አንቀጽ "ቃየን" ለሚለው የገባው ቃል "ካዬን" קַיִן ሲሆን "የተገኘ" ማለት ነው፥ "አገኘሁ" ለሚለው የገባው ቃል "ካኒቲ" קָנִ֥יתִי ሲሆን "ካዬን" קַיִן የሚለው የስም መደብ ሆነ "ካኒቲ" קָנִ֥יתִי የሚለው የሥም መደብ ሥርወ ቃሉ "ካና" קָנָה ነው።
ይህ ሆኖ ሳለ “ወንድ ልጅ ከያህዌህ አገኘሁ” ያለችውን በታርገም ዮናታን ላይ "ወንድ ልጅ ከጌታ መልአክ አገኘሁ” በማለት ያስቀምጣል፦
ታርገም ዮናታን ዘፍጥረት 4፥1 አዳምም መልአኩን የፈለገችው ሚስቱን ሔዋንን አወቀ፤ ፀነሰችም፥ ቃየንንም ወለደች። እርስዋም፦ “ወንድ ልጅ ከጌታ መልአክ አገኘሁ” አለች። וְאָדָם יְדַע יַת חַוָה אִיתְּתֵיהּ דַהֲוָה חֲמֵידַת לְמַלְאָכָא וְאַעֲדִיאַת וִילֵידַת יַת קַיִן וַאֲמָרַת קָנִיתִי לְגַבְרָא יַת מַלְאָכָא דַיְיָ
"መልአኩን የፈለገችው ሚስቱን" የሚለውን አስምርበት! ሔዋን ልጁን ያገኘችው ከአዳም ሳይሆን ከምትፈልገው ከመልአኩ ሰለሆነ "ወንድ ልጅ ከጌታ መልአክ አገኘሁ" አለች። ሳጥናኤል የተባለው የጌታ መልአክ ሥጋ ሆኖ ያ ሥጋ እባብ ሲሆን በዔድን ገነት ውስጥ የሔዋንን ክብረ ንጽሕና ወስዶ አስረገዛት፦
ታርገም ዮናታን ዘፍጥረት 3፥6 የሞት መልአክን ሳማኤልን አየችው እና ፈራች፥ እሷ ግን ዛፉ ለመብላት ጥሩ እንደ ሆነ አውቃለች። וְחָמַת אִתְּתָא יַת סַמָאֵל מַלְאָךְ מוֹתָא וּדְחִילַת וְיַדְעַת אֲרוּם טַב אִילָנָא לְמֵיכַל וַאֲרוּם אָסוּ הוּא
"ሳማኤል" סַמָּאֵל ማለት "የአምላክ መርዝ" ማለት ሲሆን ይህ የሞት መልአክ ሳማኤልን ሔዋንን ያፀነሰ የቃየን አባት ተብሎ የሚታመን በእባብ ሥጋ የተሠገወ መልአክ ነው። ሔዋን ከእባቡ ጋር ማግጣ ቃየንን የወለደችውን የሚሉት ይህንን ዳራ ይዘው ነው፦
1ኛ ዮሐንስ 3፥12 ከክፉው እንደ ነበረ ወንድሙንም እንደ ገደለ እንደ ቃየል አይደለም።
"ቃየል ከክፉው ሰይጣን ነበረ" ማለት አንዳንድ በኋላ የአይሁድ መጻሕፍት "የቃየን አባት ራሱ ዲያብሎስ ነው" ይላሉ፦
"የቃየንን ኃጢአተኛነት የአይሁድ ትውፊት በሰፊው አብራርቷል አስምሮበታል፥ እርሱ ከክፉው ነበረ። ነፍሰ ገዳይ የዲያብሎስ ልጅ ነበር(ቁ. 10)፥ ከዲያብሎስ የመጀመሪያ ሥራዎቹ አንዱ ለአዳም ሞት ማምጣት ነበር(ዮሐ 8፥44 ላይ ያለውን ማስታወሻ ተመልከት!)። አንዳንድ በኋላ የአይሁድ መጻሕፍት "የቃየን አባት ራሱ ዲያብሎስ ነው" ይላሉ"።
The NIV Cultural Backgrounds Study Bible 1st John 3፥12
"የተወለደው ልጅ ቃየን የእባቡ ልጅ ነው" የሚል ትርክት ከጥንት ጀምሮ የመጣው በዚህ ምክንያት ነው፦
"ነገር ግን ሔዋን ከወደቀች በኋላ ሰይጣን በእባቡ ተመስሎ ወደ እርስዋ ቀረበ፥ እናም የአንድነታቸው ፍሬ ቃየን ነበር። በአምላክ ፊት ያመፁ የክፉ ትውልድ ሁሉ አባት ሲሆን በአምላክ ላይ ተነሳ። ቃየን በሱራፌል መገለጡ የተገለጠ የመልአኩ ሳማኤል ዘር ነው፥ በተወለደ ጊዜ ከሔዋን፦ "ወንድ ልጅ ከጌታ መልአክ አገኘሁ" የሚል ድምፅ ተሰምቷል፥ ቃየንን ሔዋን ባረገዘች ጊዜ አዳም ከእርሷ ጋር አልነበረም"።
Legends of the Jews 1:3
የፊሊጶስ ወንጌል ይህንን ዳራ እና ፍሰት ይዞ "ቃየን በዝሙት ተወለደ፥ የእባቡ ልጅ ነበረ" ይለናል፦
የፊሊጶስ ወንጌል 61፥5 ዝሙት መጀመርያው ተጀመረ፥ ከዚያ ግዲያ ቀጠለ። ቃየን በዝሙት ተወለደ፥ የእባቡ ልጅ ነበረ። እርሱ ልክ እንደ አባቱ ነፍሰ ገዳይ ሆነ።
በሁለተኛ ክፍለ ዘመን የተገኘው የፊሊጶስ ወንጌል ቅጂ በቫሊንቲንዮስ የተዘጋጀ ሲሆን "ቃየልን ሔዋን ከእባቡ የፀነሳችውን በዝሙት ነው" የሚለውን እሳቤ ኢራኒየስ ዘሊዮን"Irenaeus of Lyon" በማውገዝ ቫሊንቲንዮስ የሚለውን እንዲህ ያቀርብልናል፦
"ቀድሞ ራሱን እባብ አባት ብሎ የሚጠራው ውሸታም ነበረ፥ እናም ወንድ እና የመጀመሪያዋ ሴት ከዚህ በፊት ሲኖሩ ይህቺ ሴት ሔዋን ዝሙት በመፈጸም ኃጢአት ሠርታለች"።
Against Heresies (St. Irenaeus) Book I(1) Chapter 30 Number 7
በቫሊንቲንዮሳውያን ዘንድ ዲያብሎስ ከመጀመሪያ ከሔዋን ጋር ኃጢአትን አድርጓል ተብሎ ይታመናል፦
1ኛ ዮሐንስ 3፥8 ኃጢአትን የሚያደርግ ከዲያብሎስ ነው፥ ዲያብሎስ ከመጀመሪያ ኃጢአትን ያደርጋልና።
በክርስትና እና በአይሁድ እሳቤ የመላእክት ጋብቻ የሚባል ቅሰጣዊ ትምህርት አለ። ይህንን ሊንክ ያስፈንጥሩ፦
https://t.me/Wahidcom/1849ወደ ዲኑል ኢሥላም ስንመጣ "ቃቢል" قَابِيْل ማለት "ቃየን"Cain" ማለት ሲሆን የአደም እና የሐዋእ የበኵር ልጅ ነው፥ "ሃቢል" هَابِيل ማለት "አቤል"Abel" ማለት ሲሆን ሁለተኛው የአደም እና የሐዋእ ልጅ ነው። "ነበእ" نَبَأ ማለት "ወሬ" ማለት ሲሆን ለነቢይ የሚወርድለት "ግልጠተ መለኮት ነው፥ "ነቢይ" نَبِيّ አሏህ የሩቅ ወሬ የሚተርክለት ሰው ነው። አምላካችን አሏህ አላፊ የሆነውን የአደምን ሁለት ልጆች የሩቅ ወሬ በተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ላይ እንዲህ ሲል ይተርካል፦
5፥27 በእነርሱም ላይ የአደምን ሁለት ልጆች ወሬ ቁርባንን ባቀረቡ እና አሏህ ከአንደኛቸው ተቀብሎ ከሌላው ባልተቀበለ ጊዜ የኾነውን በእውነት አንብብላቸው፡፡ وَاتْلُ عَلَيْهِمْ نَبَأَ ابْنَيْ آدَمَ بِالْحَقِّ إِذْ قَرَّبَا قُرْبَانًا فَتُقُبِّلَ مِنْ أَحَدِهِمَا وَلَمْ يُتَقَبَّلْ مِنَ الْآخَرِ
"የአደምን ሁለት ልጆች" የሚለው ይሰመርበት! ይህ አንቀጽ ቃቢል የአደም ልጅ መሆኑን ፍንትው እና ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፥ ስለዚህ ቃቢል የኢብሊሥ ልጅ ሳይሆን የአደም ልጅ ነው። በእናታችን ሐዋእ ላይ የቀጠፉትን ቀጣፊዎች አምላካችን አሏህ የእጃቸውን ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።
✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcomወሠላሙ ዐለይኩም