/// የዲያቢሎስ ሹመኛ///
ሰው እየመሰለ የሰይጣንን ስራ
በውል ተፈራርሞ ስንት አለ የሚሰራ
አጋንት የሾመው የዲያቢሎስ ጭፍራ
ሰው መስሎ የቆመ የሳጥናኤል አውራ
ውድድር ሲከብደው በሰላም አውድማ
የክፋት ሊቅ ተንታኝ ሐሳቡ የገማ!!!
ሰይጣንን የሚያስንቅ በተንኮል አዙሪት
የምቀኝነት ጥግ የሲኦል ውርስ ስሪት
በደም የሰከረ የቀትር ዛር ክምር
በሰውኛ ቋንቋ ስድብ የሚቀምር
ሰው መሳይ ዲያቢሎስ በውሸት ከርፍቶ
በህፃናት ለቅሶ ወዝቷል ሆዱን ሞልቶ!!!
ሰው እየመሰለ የሰይጣንን ስራ
በውል ተፈራርሞ ስንት አለ የሚሰራ
አጋንት የሾመው የዲያቢሎስ ጭፍራ
ሰው መስሎ የቆመ የሳጥናኤል አውራ
ውድድር ሲከብደው በሰላም አውድማ
የክፋት ሊቅ ተንታኝ ሐሳቡ የገማ!!!
ሰይጣንን የሚያስንቅ በተንኮል አዙሪት
የምቀኝነት ጥግ የሲኦል ውርስ ስሪት
በደም የሰከረ የቀትር ዛር ክምር
በሰውኛ ቋንቋ ስድብ የሚቀምር
ሰው መሳይ ዲያቢሎስ በውሸት ከርፍቶ
በህፃናት ለቅሶ ወዝቷል ሆዱን ሞልቶ!!!