⛪✝️መልክአ ኤዶም✝️⛪
፩፤ ለዝክረ ስምኪ በአምኃ፡፡
እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
የሰላም እመቤት ነሽና ሰላምታ ላንቺ ይገባል፡፡ እያልኩ በጠዋትና በማታ የምስጋና እጅ መንሻ አቀርብልሻለሁ፡፡
ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
በገነት መካከል የተተከልሽ ድንኳን ነሽ እኮን የኔ የአገልጋይሽ ኃጢአት ከሰማይ ኮከብ ይልቅ የበዛ ስለሆነ የካህናት አለቃ የኢየሱስ ክርስቶስ እናት ነሽና ተገቢውን ንስሐ ሰጭኝ፡፡
፪፤ ለዝክረ ስምኪ ሀሊብ፤
እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
እንደወተት አንጀትን ለሚያርስ ልብን፤ ለሚያቀዘቅዝ የመልካም ወተት ስም አጠራርሽ ሰላምታ ይገባል እያልኩ ሰላም እላለሁ፡፡
ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
ርግብየ ርግብየ እያለ የሚያመሰግንሽ የጥበበኛው ሰሎሞን ርግብ ነሽና ድንቁርና ረኃብ እንዳይጸናብኝ እህል ጥበብን መግቢኝ ከብዙ በጎ በጎ ሥራዎች አንዱ መስጠት ነውና፡፡
፫፤ ልብኪ የዋህ፡፡
እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
ኀጥእን ለጥፋት የማይመኝ ቂም በቀልን የማያውቅ ልብሽ ፍጹም የዋህ ነው እኮን፡፡
ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
ስለዚህም ይቅርታ ልማድሽ ነውና ይቅር በይኝ፡፡ በልቤ ውስጥ ያለውን ምኑን ስንቱን እነግርሻለሁ? ኅዘኔን ጭንቀቴንም አንች ታውቂዋለሽና፡፡
፬፤ ከመ ከማኪ ማርያም፡፡
እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
ከነቢያት ከጻድቃን ከሰማዕታትም ወገን ቢሆን ከቶ እንዳች የምወደው ማንም የለ፡፡
ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
አንቺን መጠጊያ ስለአደረግሁ በአንቺ ከመታመን በቀር ሥራየ ኃጢአት ብቻ ሆኗልና ለእርዳታየ ፈጥነሽ ድረሽልኝ፡፡
፭፤ ኢትኅድግኒ ዐቂበ፡፡
እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
በምሄድበት ጎዳና በማድርበትም ቦታ ሁሉ በመዓልትም በሌሊትም ጥበቃሽ አይለየኝ፡፡
ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
ነፍሳትን ሁሉ የምትመግቢ ነሽና የልብስና የምግብ ችግር ባለ ዘመኔ ሁሉ አታሳይኝ፤ ረኅብና ብርድ ጸሎትን ያስረሳሉና፡፡
፮፤ ኅበ ሖርኩ ሑሪ፡፡
እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
አሁንም በሄድኩበት መንገድ ሂጅ፤ በአደርኩበትም በዚያ ቸርነትሽ ጠባቂ ይሁነኝ፡፡
ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
በማንኛውም ወገን ንግግሬን አሳምሪ ቀኝ እጅሽን በራሴ ላይ አኑሪ፡፡ የሚፃረሩኝን ተፃረሪ ክፉ ምክራቸውንም አንድ በአንድ ዘርዝሪ፡፡
፯፤ ንዒ ማርያም፡፡
እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
ከኃጢያት ሁሉ መተዳደፍ በማየ ንስሐ ንጹሕ እምኃጢአት ታደርጊኝ ዘንድ በረድኤት ወደኔ ቅረቢ እያንዳንዳችንንም በሥላሴ ስም ባርኪን፡፡
ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
እንደኔ ያሉትን ኃጥአኖች በጸሎትሽ ወደ ንስሐ እንዲመለሱ መንፈሳዊ ጥበብን ግልጭላቸው፤ ጻድቃንንም በምግባራቸው በትሩፋታቸው ጸንተው እንዲቆዩ ጠብቂያቸው፡፡
፰፤ ንዒ ማርያም፡፡
እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
ጸሎቴን ተቀብለሽ ወደላይ ወደሰማይ ታሳርጊ ዘንድ ከላይ ከሰማይ ዳርቻ ፈጥነሽ ወደኔ ነይ፡፡
ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
ዘወትር የርኅራኄሽን ጠል በኔ ላይ አርከፍክፊ፡፡ የምድር ብልጽግና ግን ኃላፊ ጠፊ በመሆኑ በቸርነትሽ ጽድቅን ታተርፊልኝ ዘንድ የተገባ ነው፡፡
፱፤ ንዒ ማርያም ሆይ፤
እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
የአዳም ልብሱ ግርማ ሞገሱ የሄኖክ የራስ ወርቅ አንች ነሽ እኮን፡፡
ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
ብልህ አዋቂ የሆነ ከልጅነቱ ጀምሮ አንቺን ያፈቅራል፤ ሰነፍ ልበ ቢስ ግን በከንቱ ይጠላሻል፤ ዳሩ ግን በመከረው የተንኮል ምክር ወጥመድ እሱ ራሱ ይጠመድ፡፡
፲፤ ንዒ ማርያም፤
እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
ዘር ያልወደቀባት ገበሬ ያልጣረባት የቅዱስ ቁርባንን አዝመራ ያፈራሽ ገራህት ሆይ፤ ከትጉሃን መላእክት ጋር ወደኔ ፈጥነሽ ነይ፡፡
ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
ዓለም እኮ የወደዳትን መልሳ ታጠፋዋለች፡፡ በወጥመዷም አስገብታ ብዙውን ሕዝበ በመርዟ እንደገደለች ይህን ሥራዋን የሚያውቅባት ከቶ እንደምን ያለ ብልህና ዐዋቂ ይሆን ስለሆነም በመጥመዷ እንዳታጠምደኝ መረቧን በጣጥሰሽ ጣይልኝ፡፡
፲፩፤ ንዒ ማርያም፡፡
እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
ለዕውራን ብርሃናቸው ለተጠሙትም የወይን ምንጫቸው ሆይ፤ ወደኔ ፈጥነሽ ነይ፡፡
ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
ኦ ወዮ ትተይኝ ይሆን? ኦ ወዮ ትንቂኝ ይሆን? እንግዲያ የልቤን ኅዘን ለማን እነግረው ይሆን፡፡
፲፪፤ ንዒ ማርያም፡፡
እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
የመለኮቱ የእሳት ግለት ያላቀጠለሽ የእግዚአብሔር ማደሪያ ነሽና ፈጥነሽ ወደኔ ነይ፡፡
ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
በየዘመኑ በየዕለቱም ሁሉ ማሪኝ ይቅር በይኝ አንቺ ከማርሽኝ ይቅር ካልሽኝ ማነው እሱ የሚፈርድብኝ በሥጋና በነፍስ የሚፈርድ ልጅሽ ነውና
፲፫፤ እስእለኪ፡፡
እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
የሰማይና የምድር ንጉሥ እናት ነሽና ኃጢአቴን ሁሉ ፈጽመሽ ለማጥፋት ፈጥነሽ ወደኔ ትመጭ ዘንድ እማልድሻለሁ፡፡
ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
የሥጋና የነፍስን ችግር ሁሉ ከኔ ላይ አስወግጅ፡፡ ይልቁንም ወዲያና ወዲህ በማለት ቀኑ በከንቱ እንዳይመሽብኝ በቁም ነገር ሥራ ላይ እገኝ ዘንድ፤ እኔ በደለኛው አገልጋይሽ እማልድሻለሁ፡፡
፲፬፤ አተከዝኩኪ፡፡
እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
ሥፍር ቁጥር በሌለው የዚህን ዓለም ፍለጋ በመከተል እኔ ኃጥኡ ጎስቋላው አገልጋይሽ አሳዘንኩሽ ይሆን፡፡
ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
ታዲያ ከቀድሞ ጀምሮ ቂም በቀልን ይቅር ማለት ልማድሽ ነውና ይቅር በይኝ መሐሪዋ እናት ሆይ፤ አረጋጊኝ እንጂ አትተይኝ፡፡
፲፭፤ አተከዝኩኪ፡፡
እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
በመሴሰንና የዝሙት ሥራ በመሥራት ሐሰት በመናገር አሳዘንኩሽ ይሆን፡፡
ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
ነገር ግን አንቺን በፍጹም ልብ መውደድ ቀላል አይመስለኝም ሰባ ስምንት ነፍሳትን የበላ በላዔ ሰብእ በጥርኝ ውሃ ገነት ለመግባት በቅቷልና፡፡
፲፮፤ ኦ ርኅርኅተ ኅሊና፡፡
ርኅሩኋ እመቤቴ ሆይ፤
አደፍ ጉድፍ ሳይኖርብሽ በድንግልና ጸንተሽ ያለሽ የአንች ፍቅር እሳት ሆኖ አንጀትን ያቃጥላል እኮን፡፡
ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
ሁል ጊዜ በጎ በጎ ነገርን አድርጊልኝ፡፡ እንደ ሥራየ ሞት ይገባኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ንስሐ የምገባበት ጥቂት ጊዜ ታገሽኝ፡፡
፲፯፤ እለ ትወርዱ ታሕተ፡፡
እናንተ በዚህ ዓለም እያላችሁ ወደላይ ወደታች የምትወጡና የምትወርዱ ሁሉ የእመቤታችን ፍቅር ከቶ ቀላል አይምሰላችሁ፡፡ በየጊዜው ስሟን እየጠራ በእመቤታችን ፍቅር የተማመነ በአማላጅነቷም ጥላ ሥር የተጠለለ ዘማዊ ወይም ሴሰኛም ቢሆን፤ ፍጹም ድንግል ይሆናልና፡፡
፲፰፤ ተአምረኪ ብዙኃ፡፡
እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
የእግዚአብሔር ማደሪያ እንደ መሆንሽ ብዙ የሆነ ልዩ ልዩ ተአምራትሽን በጆሮየ ሰምቻለሁ በዓይኔም አይቻለሁ፡፡
ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
እኔን ከርታታውን አውታታውን በዚህ ዓለም የሚያረጋጋኝ የሚያጽናናኝ አጥቻለሁና፡፡ ርኅሩኋ እናት ሆይ፤ እስኪ ቀረብ ብለሽ የማጽናኛ ቃል አሰሚኝ፡፡
፲፱፤ ተአምረኪ ብዙኅ፡፡
እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
ፍጻሜ የሌለው የብዙ ብዙ የሆነ ተአምርሽ በደመናና በጉም አምሳል በዓለም ላይ ተሠራጨ፡፡
ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
የሮማው ጳውሎስ የመዛነቢያው ድንኳን ነሽ እኮን እኔም ንስሐ ሳልገባ እንዳልሞት ዕድሜ ትጨምሪልኝ ዘንድ ሰሎሜ ባዘለችው ልጅሽ እማፀንሻለሁ፡፡
፳፤ ናዛዚትየ፡፡
እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
ከኅዘን የምታረጋጊኝ እርጅናዬን በወጥትነት የምትለውጭልኘ ዘመን የማይቆጠርለት ሕፃን በማኅፀንሽ አደረ እኮን፡፡
ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
ተስፋ ለቆረጡት ተስፋቸው ነሽና ጸሎትንና ዕጣንን እንዲሁም ቅዱስ ቁርባንን በማቅረብ ጊዜ እኔ አገልጋይሽን ለማጽናናት በዚህ ቦታ ተገኝ፡፡
፳፩፤ ስምኪ ድንግል፡፡
እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
ስምሽ ኃጥኣንን ያጸድቃል ሰነፎችንም ብልህና ትጉህ ያደርጋል፡፡