ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
እኔ የአእምሮ ድኃ የሆንኩ አገልጋይሽ ብቻ ቀርቻለሁና፡፡ ብዙውን የልቤን ኅዘን ነግሬሽ ከኅዘኔ ታረጋጊኝ ዘንድ ፈጥነሽ ወደኔ ነይ፡፡
፳፪፤ ንዴተ ሥጋ ወነፍስ፡፡
እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
የሥጋና የነፍስ ችግር እዳይደርስብኝ ዕንቁ ስምሽን ከክብር መዝገብ ወይም ሣጥን ወስጄ ገንዘብ አደረግሁ፡፡
ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
የገጽሽን ጸዳል ለማየት እፈልጋለሁ እኮን፤ ድንግል ሆይ፤ ፈጥነሽ ድረሽልኝ፤ ድንግል ሆይ፤ ገስግሰሽ ድረሽልኝ ሰውነቴ አንችን ጠጠምታለችና፡፡
፳፫፤ አፈወ ሃይማኖት፡፡
እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
በዚያ የቁርጥ ፍርድ በሚሰጥባት ዕለት ሁሉን ወደ ሕይወት ጎዳና የምትስቢ መዓዛሽ የጣፈጠ የሃይማኖት ሽቱ ነሽ እኮን፡፡
ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
ጻድቃን በትሩፋቸው፤ በተጋድሎአቸው ያገኙሽ መንግሥተ ሰማይ ነሽ እኮን፤ የፍቅርሽ ፄና መዓዛ፤ እንደ ነጭ ዕጣን መዓዛ ሸተተኝ፤ በፍቅርሽ ወይን ጠዕምም ልቡናየ ይደሰታል፡፡
፳፬፤ አበዊነ ቅዱሳን፡፡
እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
ቅዱሳን አባቶቻችን አንቺን መረጡ መድኃኒታቸው የሆንሽ አንቺንም መልካም ፍሬ አፈሩ፡፡ (አስገኙ)
ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
ለደካማው የመጠጊያ ተራራ ነሽና ጻድቅስ በበጎ ሥራው ይድናል እንደኔ ያለው ኃጥእ ግን መሸሻው መጠጊያው ከአንቺ በቀር ወዴት ነው፡፡
፳፭፤ ለመልክእኪ፡፡
እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
መጻሕፍት እደተናገሩት ወይም እንደሚያስረዱት የእግዚአብሔርን ሥነ ራእይ ለሚመስለው ሥነ መልክእሽ ሰላምታ ይገባል፡፡
ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
የሳሙኤል የሽቱ ሙዳይ አንቺ ነሽ እኮን፤ የሚወዱሽ የሚያከብሩሽም ሁሉ በረከትሽን ያግኙ፤ የሚጠሉሽ የሚመቀኙሽ ግን ፈጥነው ይጥፉ፡፡
፳፮፤ ስብሐት ለኪ፡፡
የአብ ሙሽራው ማርያም ሆይ ላንቺ ሰላምታ ይገባል፡፡ የወልድ እናቱ ማርያም ሆይ ላንቺ ሰላምታ ይገባሻል፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ንጽሕት አዳራሽ ማርያም ሆይ ሰላምታ ላንቺ ይገባሻል፤ ወርቅና ብር ኃላፊ ጠፊ ነው፤ ስለዚህም ከዚህ ዓለም ብልጽግና ይልቅ አንቺን መውደድ እመርጣለሁና፡፡ ቸርነትሽን አታርቂብኝ፡፡
፳፯፤ እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
አሁንም በመዓልትና በሌሊት ጠብቂኝ፤ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ሠውሪኝ ለዘላለሙ አሜን አሜን አሜን
ለመቀላቀል
👉 @weludebirhane