Perspective


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


እይታ በአንድ ሰው ልምዶች ፣ እምነቶችና ስሜቶች ተጽዕኖ የሚደረግበት ግላዊ አመለካከት ነው ። ግለሰቦች ሁኔታዎችን እንዴት እንደሚገነዘቡ እና እንደሚተረጉሙ ይቀርፃል ፣ ይህም ብዙውን ጊዜ በተመሳሳይ ጉዳይ ላይ የተለያዩ አመለካከቶችን ያስከትላል ። ይህም የግለሰብ እይታ ተቀባይነት ካገኘ የሀገር ብሎም የዓለም ይሆናል ::
መጽሐፍ ፣ ስዕል ፣ ሙዚቃ ...
https://t.me/weperspective

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


ከአንቂ መጻሕፍት ገፆች dan repost
የ 1953 ቱ መፈንቅለ መንግስት ትክክለኛ ገጽታ

በይላቅ ኃይለማርያም

ዋጋ - 300 ብር ብቻ

ለማዘዝ inbox 👉 @thesunmon


ከአንቂ መጻሕፍት ገፆች dan repost
እነዚህ የውጪ መጽሐፎች የሚያስፈልጓችሁ ካላችሁ በደንብ ተመልከቷቸው ::

ዋጋቸው እያንዳንዱ የሚሸጠው 300 ብር ነው ::

ኦርደር ለማድረግ

Link - @thesunmon
Call - 0949006262


ከአንቂ መጻሕፍት ገፆች dan repost
Constitutional Law: A Contemporary Approach ( 2d Ed . 2011 )
Gregory E. Maggs & Peter J. Smith,

Abstract

The second edition of the textbook, which is suitable either for a one- or two-semester course, strives to make constitutional law easily teachable and readily accessible for students. The authors have selected the cases very carefully and provided fuller versions of the opinions so that students get a good sense of the Court's reasoning. Text boxes call the students' attention to important aspects of each opinion, and the book is filled with introductions, points for discussion, hypotheticals, and executive summaries. The authors present a diversity of views on every subject, and, reflecting some of their own disagreements, the authors have written point-counterpoint discussions on many disputed questions.

We have only 1 Copy

To Order - @thesunmon
0949006262


ከአንቂ መጻሕፍት ገፆች dan repost
Heroic Leadership
Leading with Integrity and Honor

Price - 350

To Order - @thesunmon


ከአንቂ መጻሕፍት ገፆች dan repost
The Theories Of Human Nature
Classical and contemporary reading

By :- Donald C . Abel

Only 1# Copy

For Order -

link 👉 @thesumon

Call 👉 0949006262


ከአንቂ መጻሕፍት ገፆች dan repost
The Theories Of Human Nature
Classical and contemporary reading

By :- Donald C . Abel

Only 1# Copy

For Order -

link 👉 @thesumon

Call 👉 0949006262


ከአንቂ መጻሕፍት ገፆች dan repost
እነዚህ በ INTERNATIONAL POLITICS ላይ የተጻፉ መጽሐፎች የምትፈልጉ ካላችሁ መሸጫቸው እጅግ ቅናሽ ነው በ ቴሌግራም Order ለማድረግ ይህን @thesunmon ሊንክ ተጠቀሙ ::


የሕይወት እምሻው ወጎች/ Hiwot Emishaw dan repost
Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
‹‹ስለ እራቁት ነው እንዴ ?››
------
መቼ’ለታ እንደነገርኳችሁ አዳዲሶቹ መፅሐፎቼን ለመሸጥና ከአንባቢዎቼ ጋር ለመገናኘት ዛሬ ከሰአት በኋላ ሚሊኒየም አዳራሽ ተቀምጫለሁ፡፡


ብዙ ዓይነት ሰው አገኘሁ፤ ብዙ መፅሐፍት ሸጥኩ፤ ብዙ ሳቅኩ፡፡



ከሁሉ የገረሙኝን ምልልሶች መርጬ ላጋራችሁ፡፡

ለማስታወስ ያህል የቡና ቁርስ እና ለእርቃን ሩብ ጉዳይ የተባሉትን ሁለት መፅሐፎቼን ጠረጴዛ ላይ ደርድሬ ከአላፊ አግዳሚው ወደ እኔ የሚመጣውን ሰው ሰላም እያልኩ እያስተናገድኩ ነው፡፡


ሁለት ጠና ያሉ ዘናጭ ሴቶች ተጠጉኝ፡፡


አንደኛዋ ተገዳ የቆመች በሚመስል አኳኋን ከልቧ ሳትሆን ዙሪያ ገባውን ስታማትር ሌላኛዋ ለእርቃን ሩብ ጉዳይን አነሳችና፣
‹‹ሰላም›› አለችኝ፡፡
‹‹ሰላም›› መለስኩ፡፡
‹‹የራስሽ ታሪክ ነው ይሄ?››
‹‹አይደለም››
‹‹አናቃቂ ትምህርት ነው?››
‹‹ አይ አይደለም››
‹‹ታዲያ ምንድነው?››
‹‹አጫጭር ታሪኮች ናቸው፡፡ ልቦለድ››
‹‹ማለት?››
‹‹የፈጠራ ጽሁፍ››
‹‹ስንት ነው ዋጋው?››
‹‹ሶስት መቶ›››
‹‹አይቀንስም?››
‹‹ውይ እናትዬ አይቀንስም››
‹‹በይ እሺ በርቺ››
‹‹አመሰግናለሁ››


ሄዱ፡፡


አንዲት ወጣትና ቀጭን ልጅ ደግሞ ከሩቅ ስትበር መጣችና ልክ ጠጋ ብላ ስታየኝ
‹‹ውይ…ሜሪ ፈለቀን መስሽኝ ነበር››
‹‹አ…አይደለሁም››
‹‹አንቺ ማነው ስምሽ?››
‹‹ሕይወት››
‹‹እንደ ሜሪ ፈለቀ አይነት ነው የምትጽፊው …?››
‹‹እ….››
‹‹ሜሪ ፈለቀ የለችም እዚህ?››
‹‹እኔንጃ…አላየኋትም…እዚያ ጋር አዘጋጆቹ አሉ እነሱን ጠይቂያቸው››

በመጣችበት ፍጥነት ጥላኝ ሄደች፡፡


አራት ምርጥ ሽቷቸው ከእነሱ ቀድሞ የደረሰ ሂጃብ ያደረጉ ቆነጃጅት ተጠጉኝ፡፡


‹‹ለእርቃን ሩብ ጉዳይ…ስለ እራቁት ምናምን ነው እንዴ?›› አንደኛዋ ጠየቀችኝ፡፡
‹‹እ….›› አልኩ የምላት ግር ብሎኝ፡፡
‹‹ይሄኛውስ ስለምንድነው?…›› (የቡና ቁርስን አንስታ)
‹‹አጫጭር ታሪኮች ናቸው››
‹‹ሁለቱም ያንድ ሰው ናቸው?››
‹‹ አዎ…እኔ ነኝ የጻፍኳቸው››
‹‹እንዴ…አንቺ ነሽ ደራሲዋ?›› (ፊቷ እያበራ)
‹‹አዎ…››

ማሻላህ! (ሁለቱ ባንድነት)

‹‹ሴትንማ ማበረታታት አለብን እንግዛ››
‹‹ግዴለም ይሄ ራሱ ለእኔ በቂዬ ነው›› (አፍሬ)
‹‹እንዴ…እንገዛለን…የቡና ቁርሱ ስንት ነው?››

ሶስት የቡና ቁርስ ገዝተውኝ ከነመልካም ጠረናቸው ሄዱ፡፡



ደግሞ አንድ ተለቅ ያለ ሰውዬ መጣ፡፡
‹‹እንዴት ዋልሽ?› (ሁለቱንም መፅሐፍት አንስቶ እያየ)
‹‹ይመስገን ደህና››
‹‹ ምን ሆኛለሁ አለሽ?››
‹‹እ››
‹‹ምን ሆኛለሁ የሚለው መፅሐፍ…የትእግስት ዋልተንጉስ››
‹‹እ…አይ የራሴን ብቻ ነው የያዝኩት…››
‹‹እሺ…የዮሃንስ ሞላ አዲስ የግጥም መጽሐፍስ…?››
‹‹እሱንም አልያዝኩም…ሁሉም ደራሲ የራሱን ብቻ ነው የያዘው..ዮሃንስ ግን ያውልህ›› (ፊት ለፊቴ እየጠቆምኩ)

ግራ እንደተጋባ መፅሐፎቹን ቦታቸው መልሶ ወደ ዮሃንስ ሳይሆን ወደ አንሶላ መሸጫው ሄደ፡፡
ሰውየው ምን ሆኗል?

ደግሞ ሌላ ደልደል ያለ ሰውዬ ሰላም ብሎኝ ከተጠጋኝ በኋላ ፣


‹‹ስለምንድነው…ለምን መጻፍ ፈለግሽ…ማሳተም አይከብድም ወይ…ከዚህ በምታገኚው ገቢ ነው ኑሮሽን የምትገፊው….ለምን ስነልቦና ላይ አትፅፊም›› ብሎ በጥያቄ ጎረፍ ከመታኝ በኋላ የቱን ሊገዛ ይሆን ብዬ ስጠብቅ፣

‹‹በይ እሺ…እኔ እንኳን ፊልም እንጂ ንባብ ላይ እስከዚህም ነኝ›› ብሎኝ እብስ አለ፡፡


የሆነው ሆኖ የያዝኩትን መጽሐፍ ሁሉ ገዝታችሁ ለደገፋችሁኝ፣ ላበረታችሁኝ እና ላዝናናችሁኝ አንባቢዎቼ ሁሉ ቁና ሙሉ ምስጋና!
አልቋል ብዬ ለመለስኳችሁ ይቅርታ፤ ሁለቱም መፅሐፍ አሁንም ጃፋር ጋር ስለሚገኝ እዚያ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ቸር ይግጠመን !

8 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.